ሱረቱ Al-Baqara البقرة
286 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓمٓ
Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ ፤ ላም፤ ሚም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ ٱلْكِتَٰبُ لَا رَيْبَ فِيهِ هُدًى لِّلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy2. ይህ መጽሐፍ (ቁርኣን) (ከአላህ የተወረደ ለመሆኑ) ምንም ጥርጥር የለበትም:: አላህን ለሚፈሩም ሁሉ መመሪያ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِٱلْغَيْبِ وَيُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَمِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ يُنفِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy3. ለእነዚያ በሩቁ ነገር ለሚያምኑት፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው ለሚሰግዱት፤ ከሰጠናቸዉ ሲሳይም ለሚለግሱ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ وَبِٱلْـَٔاخِرَةِ هُمْ يُوقِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4. ለእነዚያም ወደ አንተ በተወረደው መጽሐፍና ካንተ በፊትም በተወረዱት መጽሐፍት ሁሉ ለሚያምኑ፤ በመጨረሻው ቀን መኖርም ለሚያረጋግጡ ሰዎች ሁሉ (መመሪያ ነው)፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ عَلَىٰ هُدًى مِّن رَّبِّهِمْ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy5. እነዚያ (የተጠቀሱትን ባህሪያት የሚላበሱ ሰዎች ሁሉ) በጌታቸው መመሪያ ላይ በትክክል የሚጓዙ ናቸው:: ፍላጎታቸውን ያገኙትም እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ سَوَآءٌ عَلَيْهِمْ ءَأَنذَرْتَهُمْ أَمْ لَمْ تُنذِرْهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ (በአላህ ፤ በአንተ መልዕክተኛነትና በአላህ አናቅጽ) የካዱት ሰዎች ብታስጠነቅቃቸዉም ባታስጠነቅቃቸዉም ለእነርሱ ሁሉም እኩል ነው:: (ምንም ለውጥ አያመጣም) አያምኑምና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَتَمَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَعَلَىٰ سَمْعِهِمْ وَعَلَىٰٓ أَبْصَٰرِهِمْ غِشَٰوَةٌ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy7. አላህ እነዚያ እውነትን እያወቁ የካዱ ሰዎችን በልቦቻቸው እና በመስሚያቸው ላይ አትሞባቸዋል:: በዓይኖቻቸው ላይም መሸፈኛ አለ:: ለእነርሱም በጀሀነም ውስጥ ከባድ ቅጣት አለባቸው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَقُولُ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَبِٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَمَا هُم بِمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy8. ከሰዎች መካከል ለይስሙላ «በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ ክፍሎች አሉ:: እነርሱ ግን (የሚዋሹ እንጂ) ትክክለኛ አማኞች አይደሉም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُخَٰدِعُونَ ٱللَّهَ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَمَا يَخْدَعُونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy9. አላህንና እነዚያን በትክክል በአላህ ያመኑትን ሰዎች ያታልላሉ:: ነገር ግን በዚህ ተግባራቸው ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላን ማንንም አያታልሉም:: እነርሱ ግን ይህ መሆኑን በትክክል አያውቁም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ فَزَادَهُمُ ٱللَّهُ مَرَضًا وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَكْذِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy10. በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሽታ ሰርጿል:: አላህም ሌላን በሽታ ጨመረባቸው:: ለእነርሱም ይዋሹ በነበሩበት ምክንያት አሳማሚ ቅጣት አለባቸው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا نَحْنُ مُصْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy11. በምድር ላይ ሁከትን አትፍጠሩ በተባሉ ጊዜ እኛ እኮ አስተካካዮች ነን ይላሉ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَآ إِنَّهُمْ هُمُ ٱلْمُفْسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ:: አጥፊዎች እነርሱ ብቻ ናቸው:: ግን እነርሱ ይህንን አይገነዘቡም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ ءَامِنُوا۟ كَمَآ ءَامَنَ ٱلنَّاسُ قَالُوٓا۟ أَنُؤْمِنُ كَمَآ ءَامَنَ ٱلسُّفَهَآءُ أَلَآ إِنَّهُمْ هُمُ ٱلسُّفَهَآءُ وَلَٰكِن لَّا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy13, «ሰዎቹ እንዳመኑት ሁሉ እናንተም እመኑ» በተባሉ ጊዜ «ቂሎቹ እንዳመኑት እናምናለንን?» ይላሉ። (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ። ቂሎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው:: እነርሱ ግን ይህንን አያውቁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا لَقُوا۟ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَوْا۟ إِلَىٰ شَيَٰطِينِهِمْ قَالُوٓا۟ إِنَّا مَعَكُمْ إِنَّمَا نَحْنُ مُسْتَهْزِءُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. ከእነዚያ በአላህ በትክክል ካመኑት ሰዎች ጋር በተገናኙ ጊዜ «እኛም (ልክ እንደ እናንተው) አምነናል» ይላሉ። ወደ ሰይጣኖቻቸው ባገለሉ ጊዜ ደግሞ «እኛ እኮ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን» ይላሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ يَسْتَهْزِئُ بِهِمْ وَيَمُدُّهُمْ فِى طُغْيَٰنِهِمْ يَعْمَهُونَ
Amharic Translation - Africa Academy15. አላህ በእነርሱ ይሳለቅባቸዋል:: በአመጻቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ ያቆያቸዋል፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱشْتَرَوُا۟ ٱلضَّلَٰلَةَ بِٱلْهُدَىٰ فَمَا رَبِحَت تِّجَٰرَتُهُمْ وَمَا كَانُوا۟ مُهْتَدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy16. እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት የገዙ (የለወጡ) ሰዎች ናቸው:: እናም ንግዳቸው ትርፋማ አይደለም:: ቅኑን መንገድም አልተከተሉም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَثَلُهُمْ كَمَثَلِ ٱلَّذِى ٱسْتَوْقَدَ نَارًا فَلَمَّآ أَضَآءَتْ مَا حَوْلَهُۥ ذَهَبَ ٱللَّهُ بِنُورِهِمْ وَتَرَكَهُمْ فِى ظُلُمَٰتٍ لَّا يُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy17. የእነርሱ ንፍቅና ምሳሌ ልክ እንደዚያ እሳትን እንዳነደደና ከዚያ በዙሪያው ያለውን ሁሉ ባበራችለት ጊዜ አላህ ብርሃናቸውን እንደወሰደባቸው እና በጨለማዎች ውስጥ የማያዩ ሆነው እንደተዋቸው ብጤ ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
صُمٌّۢ بُكْمٌ عُمْىٌ فَهُمْ لَا يَرْجِعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy18. እነርሱ (ሓቅን የማይሰሙ) ደንቆሮዎች፤ (ሓቅን የማይናገሩ) ዲዳዎች፤ (ሓቅን የማያዩ) እውሮች ናቸው:: ስለዚህ እነርሱ (ከስህተት) አይመለሱም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوْ كَصَيِّبٍ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فِيهِ ظُلُمَٰتٌ وَرَعْدٌ وَبَرْقٌ يَجْعَلُونَ أَصَٰبِعَهُمْ فِىٓ ءَاذَانِهِم مِّنَ ٱلصَّوَٰعِقِ حَذَرَ ٱلْمَوْتِ وَٱللَّهُ مُحِيطٌۢ بِٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy19. ወይም (ምሳሌያቸው) ከሰማይ እንደወረደ ዝናብ (ባለቤቶች) ነው:: በእርሱ (በደመናው) ውስጥ ጨለማዎች፤ ነጎድጓድና ብልጭታ ያሉበት ሲሆን ከመብረቆቹ ሊመጣ ከሚችል ጥቃት ሞትን በመፍራት ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ እንደሚያደርጉ ሰዎች ቢጤ ነው:: አላህ ከሓዲያንን (በእውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَكَادُ ٱلْبَرْقُ يَخْطَفُ أَبْصَٰرَهُمْ كُلَّمَآ أَضَآءَ لَهُم مَّشَوْا۟ فِيهِ وَإِذَآ أَظْلَمَ عَلَيْهِمْ قَامُوا۟ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَذَهَبَ بِسَمْعِهِمْ وَأَبْصَٰرِهِمْ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy20 ብልጭታው ዓይኖቻቸውን ሊነጥቅ ይቀርባል:: ለእነርሱ ባበራላቸው ቁጥር በውስጡ ይሄዳሉ:: በእነርሱም ላይ ባጨለመባቸው ጊዜ ደግሞ ይቆማሉ:: አላህ በፈለገ ኖሮ መስሚያዎቻቸውንና ማያዎቻቸውን ይወስድባቸው ነበር:: አላህ በነገሮች ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱعْبُدُوا۟ رَبَّكُمُ ٱلَّذِى خَلَقَكُمْ وَٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy21. እናንተ ሰዎች ሆይ! ያን እናንተንና እነዚያን ከናንተ በፊት የነበሩትን የፈጠረውን ጌታችሁን (አላህን) በብቸኝነት ተገዙት:: ቅጣትን ልትጠነቀቁ ዘንድ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلْأَرْضَ فِرَٰشًا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءً وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَخْرَجَ بِهِۦ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ رِزْقًا لَّكُمْ فَلَا تَجْعَلُوا۟ لِلَّهِ أَندَادًا وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy22. እርሱ (አላህ) ያ ለእናንተ ምድርን ምንጣፍ፤ ሰማይን ጣራ ያደረገ ጌታ ነው::ከሰማይ ዳመና ውሃን ያወረደና ከዚያ በውሃው ከፍሬዎች ሁሉ ለእናንተ ሲሳይን ያወጣላችሁ ነው:: እናም (ብቸኛ ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትሆኑ ለአላህ (በአምልኮ) አጋሮችን አታድርጉ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن كُنتُمْ فِى رَيْبٍ مِّمَّا نَزَّلْنَا عَلَىٰ عَبْدِنَا فَأْتُوا۟ بِسُورَةٍ مِّن مِّثْلِهِۦ وَٱدْعُوا۟ شُهَدَآءَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy23. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) በአገልጋያችን (በሙሐመድ) ላይ ባወረድነው (ቁርኣን) በመጠራጠር ላይ ከሆናችሁም ከእርሱ ጋር ሊወዳደር የሚችል አንድ ምዕራፍ እንኳን እስቲ አምጡ:: እውነተኞች እንደሆናችሁ ከአላህ ሌላ ረዳቶቻችሁንም ሁሉ ጥሩ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِن لَّمْ تَفْعَلُوا۟ وَلَن تَفْعَلُوا۟ فَٱتَّقُوا۟ ٱلنَّارَ ٱلَّتِى وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ أُعِدَّتْ لِلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy24. (ይህንን) ባትሰሩ ግን በርግጥም አትሰሩትምና (አትፈጽሙትምና) ከዚያች መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች ከሆነው ከገሀነም እሳት ራሳችሁን ጠብቁ:: ለከሓዲያን ሁሉ ተደግሳለችና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ كُلَّمَا رُزِقُوا۟ مِنْهَا مِن ثَمَرَةٍ رِّزْقًا قَالُوا۟ هَٰذَا ٱلَّذِى رُزِقْنَا مِن قَبْلُ وَأُتُوا۟ بِهِۦ مُتَشَٰبِهًا وَلَهُمْ فِيهَآ أَزْوَٰجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَهُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑትንና መልካም ተግባራትን የሰሩትን ሰዎች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መሆኑን አብስራቸው:: በእርሷም ፍራፍሬ በተለገሱ ቁጥር (ፍሬዎቿ ስለሚመሳሰሉ) «ይህማ ያ ከአሁን በፊት የተመገብነው ነው።» ይላሉ:: (እርሱ ተመሳሳይ ሆኖ ይሰጣቸዋል) ለእነርሱም በውስጧ ንጹህ ሚስቶች አሏቸው:: እነርሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَسْتَحْىِۦٓ أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ فَيَعْلَمُونَ أَنَّهُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَيَقُولُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلًا يُضِلُّ بِهِۦ كَثِيرًا وَيَهْدِى بِهِۦ كَثِيرًا وَمَا يُضِلُّ بِهِۦٓ إِلَّا ٱلْفَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy26. አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝም ትሁን ከሷም በላይ የሆነን ነገር ምሳሌ ከማድረግ አያፍርም። እነዚያማ ያመኑት ምሳሌው ከጌታቸው የተነገረ እውነት መሆኑን ያውቃሉ:: እነዚያ የካዱ ግን «አላህ በዚህ አባባል ምንን ምሳሌ ፈልጎበት ነው?» ይላሉ:: አላህ በምሳሌው ብዙዎችን ያሳስታል:: በእርሱም ብዙዎችን ያቀናል:: በእርሱም አመጸኞችን እንጂ ሌላን አያሳስትም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَنقُضُونَ عَهْدَ ٱللَّهِ مِنۢ بَعْدِ مِيثَٰقِهِۦ وَيَقْطَعُونَ مَآ أَمَرَ ٱللَّهُ بِهِۦٓ أَن يُوصَلَ وَيُفْسِدُونَ فِى ٱلْأَرْضِ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْخَٰسِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኃላ የሚያፈርሱ፤ እንዲቀጠልም አላህ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ፤ በምድር ላይ ሁከት የሚፈጥሩ ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَيْفَ تَكْفُرُونَ بِٱللَّهِ وَكُنتُمْ أَمْوَٰتًا فَأَحْيَٰكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy28. (እናንተ ከሓዲያን ሆይ!) ሙታን የነበራችሁትን ሕያው ያደረጋችሁ፤ ከዚያም የሚገድላችሁ፤ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁና ከዚያም ወደ እርሱ የምትመለሱ ስትሆኑ እንዴት በአላህ ትክዳላችሁ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy29. አላህ ያ በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ለእናንተ ጥቅም ሲል የፈጠረ ጌታ ነው:: ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበና ሰባት ሰማያት አደረጋቸው:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّى جَاعِلٌ فِى ٱلْأَرْضِ خَلِيفَةً قَالُوٓا۟ أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ ٱلدِّمَآءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ قَالَ إِنِّىٓ أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ለመላዕክት «እኔ በምድር ላይ (ምትክ) ወኪል ላደርግ ነው።» ባለ ጊዜ (የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ)። «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ፤ የምናሞግስህ ስንሆን በምድር ውስጥ የሚያጠፉትንና ደሞችንም የሚያፈሱትን ታደርጋለህን?» አሉ:: አላህም «እኔ እናንተ የማታውቁትን ነገር ሁሉ አውቃለሁ» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَعَلَّمَ ءَادَمَ ٱلْأَسْمَآءَ كُلَّهَا ثُمَّ عَرَضَهُمْ عَلَى ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ فَقَالَ أَنۢبِـُٔونِى بِأَسْمَآءِ هَٰٓؤُلَآءِ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy31. ለአደምም ስሞችን ሁሉ አስተማረው:: ከዚያም በመላዕክት ላይ (ተሰያሚዎቹን) አቀረባቸው። «እውነተኞች ከሆናችሁ የእነዚህን ተሰያሚዎች መጠሪያ ንገሩኝ?» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ سُبْحَٰنَكَ لَا عِلْمَ لَنَآ إِلَّا مَا عَلَّمْتَنَآ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy32. እነርሱም «ጥራት ይገባህ አንተ ካስተማርከን ነገር በስተቀር እኛ ምንም እውቀት የለንም:: አንተ ብቸኛው ጥበበኛና አዋቂው ነህና›› አሉ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰٓـَٔادَمُ أَنۢبِئْهُم بِأَسْمَآئِهِمْ فَلَمَّآ أَنۢبَأَهُم بِأَسْمَآئِهِمْ قَالَ أَلَمْ أَقُل لَّكُمْ إِنِّىٓ أَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَأَعْلَمُ مَا تُبْدُونَ وَمَا كُنتُمْ تَكْتُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy33. አላህም «አደም ሆይ! ስሞቻቸውን ንገራቸው።» አለው። ከዚያም ስሞቻቸውን በነገራቸው ጊዜ «እኔ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ምስጢር አውቃለሁ። የምትገልጹትንና ያንንም ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ አውቃለሁ አላልኳችሁምን?» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَٰٓئِكَةِ ٱسْجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوٓا۟ إِلَّآ إِبْلِيسَ أَبَىٰ وَٱسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትን «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ከዲያብሎስ በቀር መላዕክት ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ። እርሱማ እምቢ አለ። ኮራም። ከከሓዲያንም ሆነ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقُلْنَا يَٰٓـَٔادَمُ ٱسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ ٱلْجَنَّةَ وَكُلَا مِنْهَا رَغَدًا حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy35. «አደም ሆይ! አንተና ሚስትህ በገነት ውስጥ ተቀመጡ:: በእርሷም ዉስጥ በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ:: ግን ከበደለኞች ትሆናላችሁና ይህችን ዛፍ አትቅረቡ።» አልናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَزَلَّهُمَا ٱلشَّيْطَٰنُ عَنْهَا فَأَخْرَجَهُمَا مِمَّا كَانَا فِيهِ وَقُلْنَا ٱهْبِطُوا۟ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ وَلَكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy36. ሰይጣንም ከእርሷ አሳሳታቸው። ከነበሩበትም ገነት አወጣቸው። «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ሁላችሁም (ወደ ምድር) ውረዱ። ለእናንተም በምድር ላይ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።» አልናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَتَلَقَّىٰٓ ءَادَمُ مِن رَّبِّهِۦ كَلِمَٰتٍ فَتَابَ عَلَيْهِ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy37. ከዚያም አደም ከጌታው የመታረቂያ ቃል ተማረ:: ጌታዉም ተማጽኖውን ተቀበለው:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْنَا ٱهْبِطُوا۟ مِنْهَا جَمِيعًا فَإِمَّا يَأْتِيَنَّكُم مِّنِّى هُدًى فَمَن تَبِعَ هُدَاىَ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy38. «ሁላችሁም (አደም፣ ሐዋና ሰይጣን) በአንድ ሆናችሁ ከገነት ወደ (ምድር) ውረዱ አልናቸውም። ከዚያም ከእኔ የሆነ መመሪያ ቢመጣላችሁ መመሪያዬን የተከተሉ በእነርሱ ላይ ስጋትም ትካዜም የለባቸውም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَكَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَآ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy39. «እነዚያም በመልዕክተኞቻችን የካዱና በራዕያችን ያስተባበሉ ሁሉ ግን እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ የእሳት (ገሀነም) ጓዶች ናቸው።» (አልናቸው።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتِىَ ٱلَّتِىٓ أَنْعَمْتُ عَلَيْكُمْ وَأَوْفُوا۟ بِعَهْدِىٓ أُوفِ بِعَهْدِكُمْ وَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ
Amharic Translation - Africa Academy40. እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ያችን በእናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬን አስታውሱ:: ቃል ኪዳኔንም ሙሉ:: እኔም ቃልኪዳናችሁን እሞላላችኋለሁና። እኔንም ብቻ ፍሩኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَءَامِنُوا۟ بِمَآ أَنزَلْتُ مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَكُمْ وَلَا تَكُونُوٓا۟ أَوَّلَ كَافِرٍۭ بِهِۦ وَلَا تَشْتَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِى ثَمَنًا قَلِيلًا وَإِيَّٰىَ فَٱتَّقُونِ
Amharic Translation - Africa Academy41. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከናንተ ጋር ያለውን መጽሐፍ እውቅና የሚሰጥ ሆኖ ባወረድኩት (ቁርኣን) እመኑ:: በእርሱም የመጀመሪያ ከሓዲያን አትሁኑ:: በአንቃጾቼ ጥቂት ገንዘብ አትለውጡ:: እኔንም ብቻ ፍሩኝ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَلْبِسُوا۟ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُوا۟ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy42. እውነቱን ከውሸት ጋር አትቀላቅሉ:: እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱرْكَعُوا۟ مَعَ ٱلرَّٰكِعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy43. ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ:: ዘካንም ለተገቢው አካል ስጡ:: ለጌታችሁም ከአጎንባሾች ጋር አጎንብሱ:: (ከሰጋጆች ጋር ስገዱ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَتَأْمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلْبِرِّ وَتَنسَوْنَ أَنفُسَكُمْ وَأَنتُمْ تَتْلُونَ ٱلْكِتَٰبَ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy44. እናንተ መጽሐፍን የምታነቡ ሆናችሁና ሰዎችን በበጎ ስራ እያዘዛችሁ ራሳችሁን በመልካም ምግባር ከማነጽ ትዘነጋላችሁን? አታስተውሉምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱسْتَعِينُوا۟ بِٱلصَّبْرِ وَٱلصَّلَوٰةِ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى ٱلْخَٰشِعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy45.በመታገስና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷ (ሶላት) በፈሪዎች ላይ እንጂ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَٰقُوا۟ رَبِّهِمْ وَأَنَّهُمْ إِلَيْهِ رَٰجِعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy46. እነዚያ ከጌታቸው ጋር እንደሚገናኙና ወደ እርሱ ተመላሾች መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتِىَ ٱلَّتِىٓ أَنْعَمْتُ عَلَيْكُمْ وَأَنِّى فَضَّلْتُكُمْ عَلَى ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy50. የእስራኤል ልጆች ሆይ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬንና እኔም በዓለማት ላይ ያበለጥኳችሁ (አባቶቻችሁን በጊዜያቸው ከነበሩት ዓለማት ያበለጥኩዋቸው) መኾኔን አስታውሱ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتَّقُوا۟ يَوْمًا لَّا تَجْزِى نَفْسٌ عَن نَّفْسٍ شَيْـًٔا وَلَا يُقْبَلُ مِنْهَا شَفَٰعَةٌ وَلَا يُؤْخَذُ مِنْهَا عَدْلٌ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy48. ማንኛዋም ነፍስ ከሌላዋ ነፍስ ምንንም የማትመነዳበትን፤ ከእርሷም ምልጃን የማይቀበሉባትን፤ ከእርሷም ቤዛ የማይያዝባትንና እነርሱም በየትኛዉም አካል የማይረዱበትን ቀን ቅጣት ፍሩ (ተጠንቀቁ)፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ نَجَّيْنَٰكُم مِّنْ ءَالِ فِرْعَوْنَ يَسُومُونَكُمْ سُوٓءَ ٱلْعَذَابِ يُذَبِّحُونَ أَبْنَآءَكُمْ وَيَسْتَحْيُونَ نِسَآءَكُمْ وَفِى ذَٰلِكُم بَلَآءٌ مِّن رَّبِّكُمْ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy49. ከፈርዖን ቤተሰቦች (ከጎሳዎቹ) ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱና ሴቶቻችሁን የሚተዉ ሲሆኑ ከእነርሱ ባዳንናችሁ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። ያ ክስተት ከጌታችሁ ለእናንተ ታላቅ ፈተና ነበር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ فَرَقْنَا بِكُمُ ٱلْبَحْرَ فَأَنجَيْنَٰكُمْ وَأَغْرَقْنَآ ءَالَ فِرْعَوْنَ وَأَنتُمْ تَنظُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy50. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) በእናንተ ምክንያት ባህሩን በከፈልን ጊዜ የሆነውን ታሪክም አስታውሱ:: ወዲያውኑም አዳንናችሁ:: የፈርዖንንም ቤተሰቦች ዓይናችሁ እያየ አሰመጥናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ وَٰعَدْنَا مُوسَىٰٓ أَرْبَعِينَ لَيْلَةً ثُمَّ ٱتَّخَذْتُمُ ٱلْعِجْلَ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَأَنتُمْ ظَٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ የአርባ ሌሊትን ቀጠሮ ከእኛ በወሰደበት ጊዜ (የሆነውን ታሪክ ለህዝቦችህ አስታውስ):: ከዚያም ከእርሱ (መሄድ) በኋላ እናንተ ራሳችሁን በዳዩች ስትሆኑ ወይፈንን አምላክ አደረጋችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ عَفَوْنَا عَنكُم مِّنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy52. (ቢሆንም) ከዚያ በኋላ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ምህረትን አደርግን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْفُرْقَانَ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy53. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ወደ ትክክለኛው መንገድ) ትመሩ ዘንድ ለሙሳ እውነትንና ውሸትን የሚለይን መጽሐፍ በሰጠነው ጊዜ (የዋልንላችሁን ውለታ አስታውሱ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦ يَٰقَوْمِ إِنَّكُمْ ظَلَمْتُمْ أَنفُسَكُم بِٱتِّخَاذِكُمُ ٱلْعِجْلَ فَتُوبُوٓا۟ إِلَىٰ بَارِئِكُمْ فَٱقْتُلُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ عِندَ بَارِئِكُمْ فَتَابَ عَلَيْكُمْ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy54. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለሕዝቦቹ (እንዲህ) ባለም ጊዜ የዋልነውን ውለታ አስታውሱ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን አምላክ በማድረጋችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ:: በመሆኑም ወደ ፈጣሪያችሁ ተመለሱ:: ከመካከላችሁ ወንጀለኛ ወገኖቻችሁን ግደሉ:: ይሃችሁ ድርጊት በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለእንናተ በላጭ ነው። በእናንተም ላይ ምህረቱን አወረደ:: እነሆ እርሱ (አላህ) ጸጸትን ተቀባይ ምህረተኛ አዛኝ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قُلْتُمْ يَٰمُوسَىٰ لَن نُّؤْمِنَ لَكَ حَتَّىٰ نَرَى ٱللَّهَ جَهْرَةً فَأَخَذَتْكُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ وَأَنتُمْ تَنظُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy55. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ሙሳ ሆይ! አላህን በይፋ እስከምናይ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም።» ባላችሁ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። እናንተም በዓይናችሁ እየተመለከታችሁ መብረቅ መታችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ بَعَثْنَٰكُم مِّنۢ بَعْدِ مَوْتِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy56. ከዚያም ታመሰግኑ ዘንድ ከሞታችሁ በኋላ አስነሳናችሁ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَظَلَّلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْمَنَّ وَٱلسَّلْوَىٰ كُلُوا۟ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقْنَٰكُمْ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِن كَانُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy57. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) በናንተ ላይ ዳመናን አጠለልን:: እንደ ነጭ ማር ያለ «መንን» እና ድርጭትን ለምግብነት አወረድን:: «ከሰጠናችሁም ጣፋጮችን።» ብሉ አልን:: እኛን አልበደሉንም:: ነፍሶቻቸውን ግን ይበድሉ ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قُلْنَا ٱدْخُلُوا۟ هَٰذِهِ ٱلْقَرْيَةَ فَكُلُوا۟ مِنْهَا حَيْثُ شِئْتُمْ رَغَدًا وَٱدْخُلُوا۟ ٱلْبَابَ سُجَّدًا وَقُولُوا۟ حِطَّةٌ نَّغْفِرْ لَكُمْ خَطَٰيَٰكُمْ وَسَنَزِيدُ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy58. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ወደዚህች ከተማ ግቡ። ከእርሷም ከፈለጋችሁት ስፍራ የፈለጋችሁት መልኩ ተመገቡ:: በሩንም አጎንበሳችሁ ግቡ:: ‹ጥያቄያችንም የኃጢአቶቻችን መሰረዝ ነው።› በሉ:: ኃጢአቶቻችሁን እንምራለን ለበጎ ሰሪዎችም ምንዳ እንጨምርላቸዋለን።» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውሱ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَبَدَّلَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ قَوْلًا غَيْرَ ٱلَّذِى قِيلَ لَهُمْ فَأَنزَلْنَا عَلَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ رِجْزًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ بِمَا كَانُوا۟ يَفْسُقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy59. እነዚያም እራሳቸውን የበደሉት እነርሱ ከተባሉት ሌላን ቃል ለወጡ። በነዚያም በበደሉት ላይ ያመጹ በመሆናቸው ምክንያት መቅሰፍትን ከሰማይ አወረድንባቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذِ ٱسْتَسْقَىٰ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦ فَقُلْنَا ٱضْرِب بِّعَصَاكَ ٱلْحَجَرَ فَٱنفَجَرَتْ مِنْهُ ٱثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا قَدْ عَلِمَ كُلُّ أُنَاسٍ مَّشْرَبَهُمْ كُلُوا۟ وَٱشْرَبُوا۟ مِن رِّزْقِ ٱللَّهِ وَلَا تَعْثَوْا۟ فِى ٱلْأَرْضِ مُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy60. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለሕዝቦቹ የመጠጥ ውሃን በፈለገ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ:: «ድንጋዩን በዘንግህ ምታው።» አልነው:: መታዉም ከእርሱም አስራ ሁለት ምንጮች ፈለቁ (ፈነዱ)፤ ሰዎቹ ሁሉ በትክክል መጠጫቸውን አወቁ:: «ከአላህ ሲሳይ ብሉ፤ ጠጡም፤ አመጸኞችም ሆናችሁ በምድር ላይ አታበላሹ።» (አልናቸው)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قُلْتُمْ يَٰمُوسَىٰ لَن نَّصْبِرَ عَلَىٰ طَعَامٍ وَٰحِدٍ فَٱدْعُ لَنَا رَبَّكَ يُخْرِجْ لَنَا مِمَّا تُنۢبِتُ ٱلْأَرْضُ مِنۢ بَقْلِهَا وَقِثَّآئِهَا وَفُومِهَا وَعَدَسِهَا وَبَصَلِهَا قَالَ أَتَسْتَبْدِلُونَ ٱلَّذِى هُوَ أَدْنَىٰ بِٱلَّذِى هُوَ خَيْرٌ ٱهْبِطُوا۟ مِصْرًا فَإِنَّ لَكُم مَّا سَأَلْتُمْ وَضُرِبَتْ عَلَيْهِمُ ٱلذِّلَّةُ وَٱلْمَسْكَنَةُ وَبَآءُو بِغَضَبٍ مِّنَ ٱللَّهِ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَانُوا۟ يَكْفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَيَقْتُلُونَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَوا۟ وَّكَانُوا۟ يَعْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy61. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ሙሳ ሆይ! በአንድ ዓይነት ምግብ ላይ በፍጹም አንታገስም:: ስለዚህ ጌታህ ከእነዚያ ምድር ከምታበቅላቸው ከቅጠላ ቅጠሏ፤ ከዱባዋ፤ ከስንዴዋ፤ ከምስሯና ከሽንኩርቷ ያወጣልን ዘንድ ለምንልን።» (ባላችሁም ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ):: ሙሳም «ያንን ዝቅተኛ የሆነውን በዚያ ከፍተኛና በላጭ በሆነው ነገር ልትተኩ ትፈልጋላችሁን? ወደ ከተማ ውረዱ:: የጠየቃችሁትን ነገር ታገኛላችሁና።» አላቸው። ውርደትና ድህነት ተጣለባቸው:: በአላህም ቁጣ ተመለሱ:: ይህ እነርሱ በአላህ ተዐምራት ይክዱና ነብያትንም ያለ አግባብ ይገድሉ ስለነበሩ፤ በኃጢአትም ላይ በመዘፈቃቸውና እንዲሁም ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَٱلَّذِينَ هَادُوا۟ وَٱلنَّصَٰرَىٰ وَٱلصَّٰبِـِٔينَ مَنْ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَعَمِلَ صَٰلِحًا فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy62. እነዚያ በአላህ ያመኑ፣ እነዚያ አይሁዳውያን፣ ክርስቲያኖችና ሳቢያኖችም ሁሉ ከእነርሱ መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመኑና መልካምን ስራ የሰሩ ሁሉ በእነርሱ ላይ (ምንም ይደርስብናል ብለው) ፍርሀት የለባቸዉም። (ምንም ነገር ያመልጠናል ብለው) አያዝኑምም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَٰقَكُمْ وَرَفَعْنَا فَوْقَكُمُ ٱلطُّورَ خُذُوا۟ مَآ ءَاتَيْنَٰكُم بِقُوَّةٍ وَٱذْكُرُوا۟ مَا فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy63. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከበላያችሁ የጡርን ተራራ ያነሳን ሆነን « (ከእሳት ቅጣት) ትጠበቁ ዘንድ የሰጠናችሁን በርትታችሁ ያዙ:: በውስጡ ያለውን ነገር አስታውሱ።» ብለን የጠበቀ ቃል ኪዳናችሁን በያዝንበት ጊዜ የሆነውን ታሪክ (ልብ በሉ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ تَوَلَّيْتُم مِّنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ فَلَوْلَا فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُۥ لَكُنتُم مِّنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy64. ከዚያም ከዚህ በኋላ ቃልኪዳኑን ተዋችሁ:: በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ በትክክል ከጠፊ ህዝቦች በሆናችሁ ነበር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ عَلِمْتُمُ ٱلَّذِينَ ٱعْتَدَوْا۟ مِنكُمْ فِى ٱلسَّبْتِ فَقُلْنَا لَهُمْ كُونُوا۟ قِرَدَةً خَٰسِـِٔينَ
Amharic Translation - Africa Academy65. እነዚያም ከናንተ መካከል በቅዳሜ ቀን አሳን በማጥመድ ወሰን ያለፉትንና ለእነርሱም «ወራዳዎች ዝንጆሮዎች ሁኑ።» ያልናቸውን ሕዝቦች ታሪክ በእርግጥ አወቃችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَجَعَلْنَٰهَا نَكَٰلًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهَا وَمَا خَلْفَهَا وَمَوْعِظَةً لِّلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy66. የመንደሯን ሰዎች ቅጣትም ለእነዚያ በጊዜያቸው ለነበሩትና ለእነዚያም ከበኋላቸው ለሚመጡት ሕዝቦች መቀጣጫ ለፈራሂያንም (ትምህርት) አደረግናት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تَذْبَحُوا۟ بَقَرَةً قَالُوٓا۟ أَتَتَّخِذُنَا هُزُوًا قَالَ أَعُوذُ بِٱللَّهِ أَنْ أَكُونَ مِنَ ٱلْجَٰهِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy67. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለህዝቦቹ «አላህ ላም እንድታርዱ ያዛችኋል» ባለም ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። እነርሱም ለሙሳ «መሳለቂያ ታደርገናለህን?» አሉት። እሱም «ከተሳላቂዎች ከመሆን በአላህ እጠበቃለሁ» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ ٱدْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا هِىَ قَالَ إِنَّهُۥ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ لَّا فَارِضٌ وَلَا بِكْرٌ عَوَانٌۢ بَيْنَ ذَٰلِكَ فَٱفْعَلُوا۟ مَا تُؤْمَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy68. እነርሱም «እስቲ ጌታህን ጠይቅልን:: እርሷ ምን እንደሆነች (እድሜዋን) ያብራራልን ዘንድ» አሉ:: እርሱም «‹እርሷ በውልም ያላረጀች ጥጃም ያልሆነች በዚህ መካከል ልከኛ የሆነች ጊደር ናት።› ይላችኋል። የታዘዛችሁትንም ስሩ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ ٱدْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا لَوْنُهَا قَالَ إِنَّهُۥ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ صَفْرَآءُ فَاقِعٌ لَّوْنُهَا تَسُرُّ ٱلنَّٰظِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy69. እነርሱም “እስቲ ጌታህን እንደገና ጠይቅልን:: መልኳ ምን እንደሚመስል ይገልጽልን ዘንድ” አሉ:: እርሱም “መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳልቻ ላም ናት ይላችኋል” አላቸው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ ٱدْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا هِىَ إِنَّ ٱلْبَقَرَ تَشَٰبَهَ عَلَيْنَا وَإِنَّآ إِن شَآءَ ٱللَّهُ لَمُهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy70. ጌታህን ጠይቅልን :: እርሷ ምን እንደሆነች ይግለጽልን:: ምክንያቱም ላሞቹ በሙሉ በእኛ ላይ ተመሳሰሉብን:: እኛም አላህ የሻ እንደሆነ በእርግጥ (ትክክለኛውን አቅጣጫ የምንይዝ) ተመሪዎች ነን” አሉ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِنَّهُۥ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ لَّا ذَلُولٌ تُثِيرُ ٱلْأَرْضَ وَلَا تَسْقِى ٱلْحَرْثَ مُسَلَّمَةٌ لَّا شِيَةَ فِيهَا قَالُوا۟ ٱلْـَٰٔنَ جِئْتَ بِٱلْحَقِّ فَذَبَحُوهَا وَمَا كَادُوا۟ يَفْعَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy71. እርሱም: «‹እርሷ ያልተገራች ምድርን በማረስ የማታስነሳ፤ እርሻንም የማታጠጣ፤ ከነውር ሁሉ ነፃ የሆነች፤ ጸያፍ ምልክት የሌለባት ናት።› ይላችኋል አላቸው።» እነርሱም «አሁን ገና በትክክል መጣህ።» አሉ:: ከዚያ ትዕዛዙን ላለመፈጸም የቀረቡ ሆነው ላሟን አረዷት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَتَلْتُمْ نَفْسًا فَٱدَّٰرَْٰٔتُمْ فِيهَا وَٱللَّهُ مُخْرِجٌ مَّا كُنتُمْ تَكْتُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy72. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ነፍስ በገደላችሁና በእርሷም ጉዳይ በተከራከራችሁ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ:: አላህ ያን በውስጣችሁ ትደብቁት የነበራችሁትን ሚስጢር ሁሉ ገላጭ ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقُلْنَا ٱضْرِبُوهُ بِبَعْضِهَا كَذَٰلِكَ يُحْىِ ٱللَّهُ ٱلْمَوْتَىٰ وَيُرِيكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy73. (የሙቱን በድን) «በታረደችው ላም ከፊል አካል ምቱት አልን »:: (እናም መቱትና ተነሳ:: የገደለው ማን እንደሆነ ነገራቸውና እንደገና ሞተ::) ሰዎች ሆይ! ልክ እንደዚሁ ትገነዘቡና ታውቁ ዘንድ ሙታንን ህያው በማድረግ ተዓምራቶቹን ያሳያችኋል፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ قَسَتْ قُلُوبُكُم مِّنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ فَهِىَ كَٱلْحِجَارَةِ أَوْ أَشَدُّ قَسْوَةً وَإِنَّ مِنَ ٱلْحِجَارَةِ لَمَا يَتَفَجَّرُ مِنْهُ ٱلْأَنْهَٰرُ وَإِنَّ مِنْهَا لَمَا يَشَّقَّقُ فَيَخْرُجُ مِنْهُ ٱلْمَآءُ وَإِنَّ مِنْهَا لَمَا يَهْبِطُ مِنْ خَشْيَةِ ٱللَّهِ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy74. ከዚያም ልቦቻቸው ከዚህ (ትዕይንት) በኋላ ደረቁ:: እርሷም በድርቅና እንደ አለት ድንጋዩች ወይም ከእርሱ ይበልጥ የበረቱ ናቸው:: ምክንያቱም ከድንጋዩች መካከል ጅረቶች (ወንዞች) የሚፈሱበት፤ ከእነርሱም የሚሰነጥቅና ከእርሱ ውሃ ምንጭ የሚወጣው፤ ከእነርሱም አላህን ከመፍራቱ የተነሳ ወደ ታች የሚወርድ አለና:: አላህ ከምትሰሩት ነገር ሁሉ ከአንዱም ዘንጊ አይደለም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا۟ لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَٰمَ ٱللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُۥ مِنۢ بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy75. ከ(አይሁድ) መካከል የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም እውነቱን ከተረዱ በኋላ ሆን ብለው እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ቡድኖች እያሉ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا لَقُوا۟ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَا بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ قَالُوٓا۟ أَتُحَدِّثُونَهُم بِمَا فَتَحَ ٱللَّهُ عَلَيْكُمْ لِيُحَآجُّوكُم بِهِۦ عِندَ رَبِّكُمْ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy76. እነዚያም ያመኑትን ሙስሊሞችን ባገኙ ጊዜ “እኛም እንደናንተው አምነናል” ይላሉ:: እርስ በርሳቸው ብቻ በተገናኙ ጊዜ ግን “አላህ በእናንተ ላይ የገለጸላችሁን ነገር በጌታችሁ ዘንድ እርሱን መረጃ እንዲያቀርቡባችሁ ትነግሯቸዋላችሁን? አታስተውሉምን?” ይባባላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَا يَعْلَمُونَ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعْلِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy77. አላህ የሚደብቁትንም ሆነ የሚገልጹትን ነገር ሁሉ የሚያውቅ ጌታ መሆኑን አያውቁምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنْهُمْ أُمِّيُّونَ لَا يَعْلَمُونَ ٱلْكِتَٰبَ إِلَّآ أَمَانِىَّ وَإِنْ هُمْ إِلَّا يَظُنُّونَ
Amharic Translation - Africa Academy78. ከእነርሱም መካከል መጽሐፍን የማያውቁ መሃይማን አሉ:: ግን ከንቱ ምኞቶችን ይመኛሉ:: እነርሱም መጠራጠርን እንጂ ትክክለኛ እውቀት የላቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًا قَلِيلًا فَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy79. እነዚያ መጽሐፍን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያ በእርሱ ጥቂት ዋጋን ሊገዙበት ብለው: «ይህ ከአላህ ዘንድ የወረደ ነው» ለሚሉ ሁሉ ወዮላቸው። እነርሱ ከዚያ እጆቻቸው ከፃፉት ወንጀል ወዮላቸው:: እነርሱ ከዚያ ከሚሰሩት ኃጢአት ወዮላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ لَن تَمَسَّنَا ٱلنَّارُ إِلَّآ أَيَّامًا مَّعْدُودَةً قُلْ أَتَّخَذْتُمْ عِندَ ٱللَّهِ عَهْدًا فَلَن يُخْلِفَ ٱللَّهُ عَهْدَهُۥٓ أَمْ تَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy80. (አይሁዶች) “የገሀነም እሳት ለተቆጠሩ ውስን ቀናት ብቻ እንጂ ፈጽሞ አትነካንም” አሉ። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) “በዚህ ጉዳይ ከአላህ ዘንድ ቃል ኪዳን ይዛችኋልን? ይህ ከሆነ አላህም ኪዳኑን አያፈርስም:: ወይስ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?” በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلَىٰ مَن كَسَبَ سَيِّئَةً وَأَحَٰطَتْ بِهِۦ خَطِيٓـَٔتُهُۥ فَأُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy81. እንዴታ እነዚያ መጥፎን ተግባር የሰሩና በኃጢአትም የተከበቡ ሁሉ በእርግጥ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በውስጧ ለዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy82. እነዚያም ያመኑና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ የገነት ጓዶች ናቸው። እነርሱም በውስጧ ለዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَٰقَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ لَا تَعْبُدُونَ إِلَّا ٱللَّهَ وَبِٱلْوَٰلِدَيْنِ إِحْسَانًا وَذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَقُولُوا۟ لِلنَّاسِ حُسْنًا وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ ثُمَّ تَوَلَّيْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا مِّنكُمْ وَأَنتُم مُّعْرِضُونَ
Amharic Translation - Africa Academy83. (የኢስራኢል-ልጆችን) “አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ:: ለወላጆችም በጎን ስራ ስሩ:: ለዝምድና ባለቤቶች፤ ለየቲሞችና ለሚስኪኖችም በጎን ዋሉ:: ለሰዎችም ሁሉ መልካምን ብቻ ተናገሩ :: ሶላትን ደንቡን ጠብቃች ስገዱ:: ዘካን ለተገቢው ስጡ” በማለት ጥብቅ ቃልኪዳን በያዝንባቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: ከዚያም ከእናንተ ጥቂቶቹ ሲቀሩ ሸሻችሁ:: እናንተ (ቃልኪዳንንም) የምትተው ናችሁ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَٰقَكُمْ لَا تَسْفِكُونَ دِمَآءَكُمْ وَلَا تُخْرِجُونَ أَنفُسَكُم مِّن دِيَٰرِكُمْ ثُمَّ أَقْرَرْتُمْ وَأَنتُمْ تَشْهَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy84. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) የሕዝቦቻችሁን ደም አታፍስሱ:: ወገኖቻችሁን ከመኖሪያ አገሮቻቸው አታስወጡ በማለት የጠበቀ ቃልኪዳናችሁን በያዝንባችሁ ጊዜ (የሆነውን) አስታውሱ:: ከዚያም በቃል ኪዳኑ ትክክለኛነት አጸናችሁ::እናንተም በዚሁም ትመሰክራላችሁ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ أَنتُمْ هَٰٓؤُلَآءِ تَقْتُلُونَ أَنفُسَكُمْ وَتُخْرِجُونَ فَرِيقًا مِّنكُم مِّن دِيَٰرِهِمْ تَظَٰهَرُونَ عَلَيْهِم بِٱلْإِثْمِ وَٱلْعُدْوَٰنِ وَإِن يَأْتُوكُمْ أُسَٰرَىٰ تُفَٰدُوهُمْ وَهُوَ مُحَرَّمٌ عَلَيْكُمْ إِخْرَاجُهُمْ أَفَتُؤْمِنُونَ بِبَعْضِ ٱلْكِتَٰبِ وَتَكْفُرُونَ بِبَعْضٍ فَمَا جَزَآءُ مَن يَفْعَلُ ذَٰلِكَ مِنكُمْ إِلَّا خِزْىٌ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يُرَدُّونَ إِلَىٰٓ أَشَدِّ ٱلْعَذَابِ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy85. ከዚያም ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ የምትገድሉ፤ ከናንተም መካከል የሆኑ ሕዝቦችን በኃጢአትና በመበደል ላይ በመተባበር ከአገሮቻቸው የምታስወጡ እናንተው ራሳችሁ ናችሁ:: ምርኮኞች ሆነው ወደ እናንተ ሲመጡም ቤዛ ትሆኗቸዋላችሁ:: እነርሱን ከመኖሪያ ክልላቸው ማባረሩ በእናንተ ላይ የተከለከለ ነው:: በመጽሐፉ በከፊሉ አምናችሁ በሌላው ትክዳላችሁን? ከእናንተ መካከል ይህንን ጸያፍ ተግባር የሚሰራ ሰው ሁሉ ቅጣቱ በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት አንጂ ሌላ አይደለም:: በትንሳኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ። አላህ ከምትሰሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱشْتَرَوُا۟ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا بِٱلْـَٔاخِرَةِ فَلَا يُخَفَّفُ عَنْهُمُ ٱلْعَذَابُ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy86. እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት በመጨረሻይቱ ዓለም የለወጡ ናቸው። ከእነርሱ ላይም ቅጣቱ ምንጊዜም አይቀለልላቸዉም:: እርዳታም ከማንም አያገኙም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ وَقَفَّيْنَا مِنۢ بَعْدِهِۦ بِٱلرُّسُلِ وَءَاتَيْنَا عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ ٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَيَّدْنَٰهُ بِرُوحِ ٱلْقُدُسِ أَفَكُلَّمَا جَآءَكُمْ رَسُولٌۢ بِمَا لَا تَهْوَىٰٓ أَنفُسُكُمُ ٱسْتَكْبَرْتُمْ فَفَرِيقًا كَذَّبْتُمْ وَفَرِيقًا تَقْتُلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy87. ለሙሳ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: ከርሱ በኋላም ሌሎች መልዕክተኞችን ልከናል:: የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተዐምራትን ሰጠነው:: ቅዱስ መንፈስ (ጅብሪል) በሚባለው መላአክ አበረታነው:: ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልዕክተኛው በመጣላችሁ ቁጥር እነርሱን ከመከተል ይልቅ በትዕቢት ከፊሉን አስተባበላችሁ:: ከፊሉን ደግሞ ትገድላላችሁን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ قُلُوبُنَا غُلْفٌۢ بَل لَّعَنَهُمُ ٱللَّهُ بِكُفْرِهِمْ فَقَلِيلًا مَّا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy88. “ልቦቻችን ድፍኖች ናቸው” አሉ:: (እውነታው ግን ይህ አይደለም)። አላህ በክህደታቸው ምክንያት ረገማቸው። በመሆኑም ጥቂትን እንጂ አያምኑም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا جَآءَهُمْ كِتَٰبٌ مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ مُصَدِّقٌ لِّمَا مَعَهُمْ وَكَانُوا۟ مِن قَبْلُ يَسْتَفْتِحُونَ عَلَى ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَلَمَّا جَآءَهُم مَّا عَرَفُوا۟ كَفَرُوا۟ بِهِۦ فَلَعْنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy89. ከእነርሱ ጋር ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭ የሆነ መጽሐፍ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ ከመምጣቱ በፊት በእነዚያ በካዱት ላይ ይረዱበት የነበሩ ሲሆኑ ያ ቀድሞውኑ ያውቁት የነበረ ነገር በመጣላቸው ጊዜ በእርሱ ካዱ:: እናም የአላህ እርግማን በካሐዲያን ላይ ይሁን፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بِئْسَمَا ٱشْتَرَوْا۟ بِهِۦٓ أَنفُسَهُمْ أَن يَكْفُرُوا۟ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بَغْيًا أَن يُنَزِّلَ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ فَبَآءُو بِغَضَبٍ عَلَىٰ غَضَبٍ وَلِلْكَٰفِرِينَ عَذَابٌ مُّهِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy90. ነፍሶቻቸውን የሸጡበት (የለወጡበት) ነገር ከፋ! ይኸዉም አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ችሮታውን ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው:: እናም የአላህን ቁጣ በተደጋጋሚ አትርፈዋል:: ለካሐዲያንም አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ ءَامِنُوا۟ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُوا۟ نُؤْمِنُ بِمَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا وَيَكْفُرُونَ بِمَا وَرَآءَهُۥ وَهُوَ ٱلْحَقُّ مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَهُمْ قُلْ فَلِمَ تَقْتُلُونَ أَنۢبِيَآءَ ٱللَّهِ مِن قَبْلُ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy91. «አላህ ባወረደው እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በእኛ ላይ በተወረደው መጽሐፍ ብቻ እናምናለን» ይላሉ:: ከእርሱ ኋላ የመጣው ቁርኣን ምንም እንኳን ከእነርሱ ጋር ላለው መጽሐፍ አረጋጋጭና ትክክለኛ የሆነ ቢሆንም ይክዳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነብያትን ለምን ገደላችሁ?» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ جَآءَكُم مُّوسَىٰ بِٱلْبَيِّنَٰتِ ثُمَّ ٱتَّخَذْتُمُ ٱلْعِجْلَ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَأَنتُمْ ظَٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy92. ሙሳ በግልጽ መረጃ ታጅቦ ወደ እናንተ መጥቶ ነበር:: ግን እርሱ በሌለበት ወይፈንን አምላክ አደረጋችሁ:: አጥፊዎች ነበራችሁ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَٰقَكُمْ وَرَفَعْنَا فَوْقَكُمُ ٱلطُّورَ خُذُوا۟ مَآ ءَاتَيْنَٰكُم بِقُوَّةٍ وَٱسْمَعُوا۟ قَالُوا۟ سَمِعْنَا وَعَصَيْنَا وَأُشْرِبُوا۟ فِى قُلُوبِهِمُ ٱلْعِجْلَ بِكُفْرِهِمْ قُلْ بِئْسَمَا يَأْمُرُكُم بِهِۦٓ إِيمَٰنُكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy93. የጡርን ጋራ ከበላያችሁ በማንሳት (በተውራት ሕግ እንደትሰሩ) ቃል ኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: «የሰጠናችሁን በጽናት ያዙ:: ያልነውንም ስሙ።» አልን:: «ሰማን ግን አመጽን» አሉ:: የወይፈኑም ውዴታ በክህደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ገብቷል:: «ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ እምነታችሁ የሚያዛችሁ ነገር የከፋ ነው።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِن كَانَتْ لَكُمُ ٱلدَّارُ ٱلْـَٔاخِرَةُ عِندَ ٱللَّهِ خَالِصَةً مِّن دُونِ ٱلنَّاسِ فَتَمَنَّوُا۟ ٱلْمَوْتَ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ለአይሁድ) «የመጨረሻይቱ አገር ገነት በአላህ ዘንድ ከሌሎች በተለየ ለእናንተ ብቻ በመሆኗ እውነተኞች ከሆናችሁ እስቲ ሞትን ተመኙ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَن يَتَمَنَّوْهُ أَبَدًۢا بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌۢ بِٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy95. እጆቻቸው (ባሳለፉት) በሰሩት ወንጀል ምክንያት ሞትን ምንጊዜም ፈጽሞ አይመኙትም:: አላህ በዳዩችን አዋቂ ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَتَجِدَنَّهُمْ أَحْرَصَ ٱلنَّاسِ عَلَىٰ حَيَوٰةٍ وَمِنَ ٱلَّذِينَ أَشْرَكُوا۟ يَوَدُّ أَحَدُهُمْ لَوْ يُعَمَّرُ أَلْفَ سَنَةٍ وَمَا هُوَ بِمُزَحْزِحِهِۦ مِنَ ٱلْعَذَابِ أَن يُعَمَّرَ وَٱللَّهُ بَصِيرٌۢ بِمَا يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድ ሁሉ እና ከእነዚያ ጣኦትን በአላህ ካጋሩት ይበልጥ በሕይወት ላይ የሚጓጉ ሆነው በእርግጥ ታገኛቸዋለህ:: ለአንዳቸውም አንድ ሺህ ዓመት ዕድሜ ቢሰጥ ይወዳል:: እርሱም (ዕድሜ መሰጠቱ) ከቅጣት የሚያድነው አይደለም:: አላህም የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُۥ نَزَّلَهُۥ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ ٱللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመልዐኩ ጅብሪል ጠላት የሆነ (ግልጽ ከሃዲ ነው)። ከርሱ በፊት የወረዱ መጽሐፍትን የሚያረጋግጥ ለአማኞች መሪና ብስራት ነጋሪ ሲሆን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ ያወረደው መሆኑን ንገራቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَن كَانَ عَدُوًّا لِّلَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَرُسُلِهِۦ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَىٰلَ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَدُوٌّ لِّلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy98. ለአላህና ለመላዕክቱ፤ እንዲሁም ለመልዕክተኞቹ፤ ለጅብሪልና ለሚካኢልም ጠላት የሆነ ሁሉ ግልጽ ከሐዲ ነው:: አላህ ደግሞ ለከሓዲያን ሁሉ ጠላት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ءَايَٰتٍۭ بَيِّنَٰتٍ وَمَا يَكْفُرُ بِهَآ إِلَّا ٱلْفَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ አንተ ግልጽ የሆኑ (አናቅጽን) መመሪያዎችን በእርግጥ አውርደናል:: በእነርሱም አመጸኞች እንጂ ሌላ አይክድም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَكُلَّمَا عَٰهَدُوا۟ عَهْدًا نَّبَذَهُۥ فَرِيقٌ مِّنْهُم بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy100. ቃልኪዳን በገቡ ቁጥር ከእነርሱ መካከል ከፊሉ ቃል ኪዳኑን ይጥለዋልን? (ያፈርሰዋልን?):: ይልቁንም አብዛኞቻቸው አያምኑም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا جَآءَهُمْ رَسُولٌ مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ مُصَدِّقٌ لِّمَا مَعَهُمْ نَبَذَ فَرِيقٌ مِّنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ كِتَٰبَ ٱللَّهِ وَرَآءَ ظُهُورِهِمْ كَأَنَّهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy101. ከእነርሱ ጋር ያለን መጽሐፍ የሚያረጋግጥ መልዕክተኛ ከአላህ ዘንድ ተልኮ በመጣ ጊዜ ከእነዚያው መጽሐፍት ከተሰጣቸው ወገኖች ከፊሎቹ ምንም እንደማያውቁ ሆነው የአላህን መጽሐፍ ወደ ኋላቸው ወረወሩት (ጣሉት)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌ فَلَا تَكْفُرْ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ وَمَا هُم بِضَآرِّينَ بِهِۦ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَلَقَدْ عَلِمُوا۟ لَمَنِ ٱشْتَرَىٰهُ مَا لَهُۥ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنْ خَلَٰقٍ وَلَبِئْسَ مَا شَرَوْا۟ بِهِۦٓ أَنفُسَهُمْ لَوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy102. (የአላህን መጽሐፍ አንቀበልም ያሉ አይሁዶች) ሰይጣናት በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ድግምት ተከተሉ:: ሱለይማን ጌታውን አልካደም::( ድግምተኛ አልነበረም::) ሰይጣናት ግን ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲሆኑ በጌታቸው ካዱ:: በባቢሎን (በባቢል) በሁለቱ መላዕክት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደውን ተከተሉ:: (ሀሩትና ማሩት) ግን «እኛ ለእናንተ መፍፈተኛዎች ነንና በጌታህ አትካድ» እስከሚሉ ድረስ አንድንም አያስተምሩም ነበር:: ከእነርሱም በባልና በሚስቱ መካከል የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ:: እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር አንድንም በርሱ አይጎዱም:: (ድግምት የሚማሩ ሁሉ) የሚጎዳቸውንና ቅንጣት የማይጠቅማቸውን ትምህርት ይማራሉ:: የገዛው በመጨረሻይቱ አገር ምንም ዕድል የሌለው መሆኑን በእርግጥ ተገንዝበዋል:: ነፍሶቻቸውን የሸጡበት ዋጋ ምንኛ ከፋ:: የሚያውቁ በሆኑ ኑሮ (ይህን ተግባር ባልተገበሩት ነበር::)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَنَّهُمْ ءَامَنُوا۟ وَٱتَّقَوْا۟ لَمَثُوبَةٌ مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ خَيْرٌ لَّوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy103. በአላህ ባመኑና የከለከለውን በተጠነቀቁ ኖሮ (መልካምን በተመነዱ ነበር):: የሚያውቁ ቢሆኑ ከአላህ ዘንድ የሚገኘው ምንዳ (ነፍሶቻቸውን ከሚሸጡበት) በላጭ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَقُولُوا۟ رَٰعِنَا وَقُولُوا۟ ٱنظُرْنَا وَٱسْمَعُوا۟ وَلِلْكَٰفِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy104. (እናንተያመናችሁ ሆይ!) ለነብዩ "ራዒና" አትበሉ:: “ኡንዙርና” (ተመልከተን) በሉ:: የምትባሉትንም ስሙ:: ለካሃዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት ተዘጋጅቶላቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّا يَوَدُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ وَلَا ٱلْمُشْرِكِينَ أَن يُنَزَّلَ عَلَيْكُم مِّنْ خَيْرٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَٱللَّهُ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِۦ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ ذُو ٱلْفَضْلِ ٱلْعَظِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy105. እነዚያ ከመጽሐፍ ባለቤቶችም ሆነ ከአጋሪዎች በአላህ የካዱት በእናንተ ላይ ከጌታችሁ የሆነ መልካም ነገር መውረዱን አይወዱም:: አላህም በችሮታው (በነብይነት) የሚፈልገውን ሰው ይመርጣል:: አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا نَنسَخْ مِنْ ءَايَةٍ أَوْ نُنسِهَا نَأْتِ بِخَيْرٍ مِّنْهَآ أَوْ مِثْلِهَآ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከቁርኣን አናቅጽ መካከል አንዱን እንኳን ብንሽር ወይም እርሱን ብናስረሳህ ከእርሱ የሚበልጥ ወይም ተመሳሳዩን እናመጣለን:: አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ መሆኑን አላወቅክምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ መሆኑን እና ለእናንተም ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ ረዳት እንደሌላችሁ አላወቅክምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ تُرِيدُونَ أَن تَسْـَٔلُوا۟ رَسُولَكُمْ كَمَا سُئِلَ مُوسَىٰ مِن قَبْلُ وَمَن يَتَبَدَّلِ ٱلْكُفْرَ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ ضَلَّ سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ
Amharic Translation - Africa Academy108. (ሰዎች ሆይ!) ከአሁን በፊት (ነብዩ) ሙሳ እንደተጠየቀው ዓይነት መልዕክተኛችሁን (ሙሐመድን) ልትጠይቁ ትፈልጋላችሁን? በእምነት ክህደትን የሚለውጥ ሁሉ በእርግጥ ትክክለኛውን መንገድ ስቷል፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَدَّ كَثِيرٌ مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ لَوْ يَرُدُّونَكُم مِّنۢ بَعْدِ إِيمَٰنِكُمْ كُفَّارًا حَسَدًا مِّنْ عِندِ أَنفُسِهِم مِّنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ ٱلْحَقُّ فَٱعْفُوا۟ وَٱصْفَحُوا۟ حَتَّىٰ يَأْتِىَ ٱللَّهُ بِأَمْرِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy109. ከመጽሐፍ ባለቤቶች መካከል ብዙዎቹ እውነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በሆነው ምቀኝነት በመገፋፋት ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲያን ሊያደርጓችሁ ተመኙ:: እናም አላህ ትዕዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ይቅርታ አድርጉ:: እለፏቸዉም:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَمَا تُقَدِّمُوا۟ لِأَنفُسِكُم مِّنْ خَيْرٍ تَجِدُوهُ عِندَ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy110. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሶላትን አስተካክላችሁ ስገዱ:: ዘካንም ለተገቢዎች ስጡ:: ለነፍሶቻችሁም የምታስቀድሙትን በጎ ስራ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ لَن يَدْخُلَ ٱلْجَنَّةَ إِلَّا مَن كَانَ هُودًا أَوْ نَصَٰرَىٰ تِلْكَ أَمَانِيُّهُمْ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy111. «ገነትን አይሁድ ወይም ክርስቲያኖች የሆነ እንጂ ሌላ አይገባትም።» አሉ:: «ይህች ከንቱ ምኞታቸው ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ ማስረጃችሁን አምጡ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلَىٰ مَنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُۥ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَلَهُۥٓ أَجْرُهُۥ عِندَ رَبِّهِۦ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy112. ጉዳዩ እንደመሰላቸው አይደለም:: ይልቁንም በጎ ሰሪ ሆኖ ፊቱን ለአላህ የሰጠ ሁሉ ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳ አለው:: በእነርሱ ላይ ስጋትም የለባቸዉም። አይተክዙምም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَتِ ٱلْيَهُودُ لَيْسَتِ ٱلنَّصَٰرَىٰ عَلَىٰ شَىْءٍ وَقَالَتِ ٱلنَّصَٰرَىٰ لَيْسَتِ ٱلْيَهُودُ عَلَىٰ شَىْءٍ وَهُمْ يَتْلُونَ ٱلْكِتَٰبَ كَذَٰلِكَ قَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ مِثْلَ قَوْلِهِمْ فَٱللَّهُ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُوا۟ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy113. እነርሱ መጽሐፉን የሚያነቡ ሲሆን አይሁድ «ክርስቲያኖች በምንም ላይ አይደሉም።» አሉ:: ክርስቲያኖችም «አይሁዶች በምንም ላይ አይደሉም።» አሉ። እንደዚሁ እነዚያ የማያውቁት አጋሪዎችም የነሱን ተመሳሳይ ንግግር ተናገሩ:: አላህ በዚያ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ላይ ሁሉ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ أَن يُذْكَرَ فِيهَا ٱسْمُهُۥ وَسَعَىٰ فِى خَرَابِهَآ أُو۟لَٰٓئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَن يَدْخُلُوهَآ إِلَّا خَآئِفِينَ لَهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا خِزْىٌ وَلَهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy114. የአላህን መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳበት ከከለከለና መስጊዶችንም ለማበላሸት ከጣረ ይበልጥ ድንበር አላፊ (አጥፊ) ማን ነው? እነዚያ በፍርሃት ተውጠው እንጂ ወደ መስጊዶች ሊገቡ አይገባቸዉም። ለነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው:: በመጨረሻይቱ ሀገርም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِلَّهِ ٱلْمَشْرِقُ وَٱلْمَغْرِبُ فَأَيْنَمَا تُوَلُّوا۟ فَثَمَّ وَجْهُ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy115. ምስራቁም ምዕራቡም የአላህ ብቻ ነው:: በአላህ ትእዛዝ (ፊቶቻችሁን) ለሶላት ወደ የትም አቅጣጫ ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ዘንድ ነው:: አላህ በእርግጥ ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነዉና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًا سُبْحَٰنَهُۥ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ كُلٌّ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
Amharic Translation - Africa Academy116. አላህ «ልጅ አለው።» አሉ:: ከሚሉት ጥራት ተገባው:: ይልቁንም በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው:: ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَإِذَا قَضَىٰٓ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ
Amharic Translation - Africa Academy117. ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው:: ማንንም ነገር ማስገኘት በፈለገ ጊዜ ለእርሱ የሚለው ‹‹ሁን›› ብቻ ነው:: ወዲያዉም እንዳለው ይሆናል፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ لَوْلَا يُكَلِّمُنَا ٱللَّهُ أَوْ تَأْتِينَآ ءَايَةٌ كَذَٰلِكَ قَالَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِم مِّثْلَ قَوْلِهِمْ تَشَٰبَهَتْ قُلُوبُهُمْ قَدْ بَيَّنَّا ٱلْـَٔايَٰتِ لِقَوْمٍ يُوقِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy118. እነዚያ የማያውቁት «(አንተ መልዕክተኛ ስለመሆንህ) አላህ ለምን አያናግረንም? ወይም (ለእውነተኛነትህ) ተዓምር አይመጣልንም ኖሯልን? አሉ:: እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚሁ ንግግራቸው ብጤ ብለዋል:: ልቦቻቸው በክህደት ተመሳሰሉ:: ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን በእርግጥ አብራርተናል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ بَشِيرًا وَنَذِيرًا وَلَا تُسْـَٔلُ عَنْ أَصْحَٰبِ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy119. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን በእውነት ላክንህ:: ከእሳት ጓዶችም ሁኔታ አትጠየቅም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ ٱلْيَهُودُ وَلَا ٱلنَّصَٰرَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ قُلْ إِنَّ هُدَى ٱللَّهِ هُوَ ٱلْهُدَىٰ وَلَئِنِ ٱتَّبَعْتَ أَهْوَآءَهُم بَعْدَ ٱلَّذِى جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ مَا لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy120. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድም ሆኑ ክርስቲያኖች የየራሳቸውን ሀይማኖትን እስከምትከተል ድረስ ፈጽሞ አይደሰቱብህም:: «ትክክለኛው መንገድ በእርግጥ የአላህ አመራር ነው።» በላቸው። ትክክለኛው እውቀት ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል አንተን ከአላህ የሚከላከልልህ ወዳጅም ሆነ ረዳት የለህም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ ءَاتَيْنَٰهُمُ ٱلْكِتَٰبَ يَتْلُونَهُۥ حَقَّ تِلَاوَتِهِۦٓ أُو۟لَٰٓئِكَ يُؤْمِنُونَ بِهِۦ وَمَن يَكْفُرْ بِهِۦ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْخَٰسِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy121. እነዚያ መጽሐፉን የሰጠናቸው ሰዎች ተገቢ ንባቡን ያነቡታል:: በእርሱም ያምናሉ:: እነዚያ በእርሱ የሚክዱ ግን ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتِىَ ٱلَّتِىٓ أَنْعَمْتُ عَلَيْكُمْ وَأَنِّى فَضَّلْتُكُمْ عَلَى ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy122. እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! እኔ ያ በእናንተ ላይ የለገስኳችሁን ጸጋዎቼንና (በዘመናችሁ ከነበሩት) የዓለማት ሕዝቦች በላይ ያበለጥኳችሁ መሆኔን አስታውሱ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتَّقُوا۟ يَوْمًا لَّا تَجْزِى نَفْسٌ عَن نَّفْسٍ شَيْـًٔا وَلَا يُقْبَلُ مِنْهَا عَدْلٌ وَلَا تَنفَعُهَا شَفَٰعَةٌ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy123. አንዲት (አማኝ) ነፍስ ለሌላ (ከሓዲ) ነፍስ ምንንም የማትጠቅምበትን፤ ከእርሷም ቤዛ የማይወሰድበትን፤ ምልጃም ለእርሷ የማትፈይድበትን፤ እነርሱም ከየትም በኩል የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذِ ٱبْتَلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ رَبُّهُۥ بِكَلِمَٰتٍ فَأَتَمَّهُنَّ قَالَ إِنِّى جَاعِلُكَ لِلنَّاسِ إِمَامًا قَالَ وَمِن ذُرِّيَّتِى قَالَ لَا يَنَالُ عَهْدِى ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂምን ጌታው በትዕዛዛት በፈተነውና በፈጸማቸውም ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ):: «እኔ የሰው ዘር መሪ አድርጌሀላሁ።» አለው:: ኢብራሂምም «ከዘሮቼም አድርግ?» ሲል ጠየቀ:: አላህም «ኢብራሂም ሆይ! ቃል ኪዳኔ ለግፈኛ አጥፊዎች ተፈፃሚ አይሆንም እንጂ።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ جَعَلْنَا ٱلْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَٱتَّخِذُوا۟ مِن مَّقَامِ إِبْرَٰهِـۧمَ مُصَلًّى وَعَهِدْنَآ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْعَٰكِفِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ
Amharic Translation - Africa Academy125. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቤቱንም (ከዕባን) ለሰዎች መሰባሰቢያና የሰላም ማዕከል ባደረግን ጊዜ የነበረውን ታሪክ አሰታውስ:: (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከኢብራሂም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ:: ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ {1}
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ إِبْرَٰهِـۧمُ رَبِّ ٱجْعَلْ هَٰذَا بَلَدًا ءَامِنًا وَٱرْزُقْ أَهْلَهُۥ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ مَنْ ءَامَنَ مِنْهُم بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ قَالَ وَمَن كَفَرَ فَأُمَتِّعُهُۥ قَلِيلًا ثُمَّ أَضْطَرُّهُۥٓ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلنَّارِ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy126. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ይህንን ሀገር (መካን) ሰላማዊ ሀገር አድርገው:: ከኗሪዉም መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነውን ክፍል ከፍራፍሬዎች ሲሳይ ስጠው።» ባለ ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ):: አላህም «የካደውንም በጥቂቱ እንዲጎናጸፍ አደርገዋለሁ:: ከዚያ ወደ እሳት ቅጣት እዳርገዋለሁ:: ይህም እጅግ አስከፊ መመለሻ ነው።» አለ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَٰهِـۧمُ ٱلْقَوَاعِدَ مِنَ ٱلْبَيْتِ وَإِسْمَٰعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّآ إِنَّكَ أَنتَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy127. ኢብራሂምና ኢስማዒልም (እንደሚከተለው) በማለት እየለመኑ የካዕባን ህንፃ (መሰረቶች ግንባታ) ባሳደጉ ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ): «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበለን:: አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبَّنَا وَٱجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَآ أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَآ إِنَّكَ أَنتَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy128. «ጌታችን ሆይ! ላንተው ፍጹም ታዛዦችም አድርገን:: ከዘሮቻችንም ላንተ ፍጹም ታዛዦች ሕዝቦችን አስነሳ:: አምልኳዊ ክንውኖቻችንንም አሳውቀን:: ንሰሀችንን ተቀበለን:: ጸጸትን ተቀባይና ሩህሩህ አንተ ብቻ ነህና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَبَّنَا وَٱبْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُوا۟ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy129. «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸው ከእነርሱ የሆነን መልዕክተኛ፤ በእነርሱ ላይ አናቅጽህን የሚያነብላቸው፤ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውንም ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክላቸው:: አሸናፊዉና ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና።» የሚሉም ሲሆኑ (ከዕባን ገነቡ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن يَرْغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبْرَٰهِـۧمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفْسَهُۥ وَلَقَدِ ٱصْطَفَيْنَٰهُ فِى ٱلدُّنْيَا وَإِنَّهُۥ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ لَمِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
Amharic Translation - Africa Academy130. ከኢብራሂምም እምነት ሞኝ ካልሆነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማን ነው? በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ (ለተልዕኳችን) መረጥነው:: በመጨረሻይቱ ዓለምም እርሱ ከመልካሞቹ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy131. ጌታው ለእርሱ «ፍጹም ታዛዥ ሁን።» ባለው ጊዜ «ለዓለማቱ ጌታ ታዛዥ ሆኛለሁ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوَصَّىٰ بِهَآ إِبْرَٰهِـۧمُ بَنِيهِ وَيَعْقُوبُ يَٰبَنِىَّ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰ لَكُمُ ٱلدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy132. ኢብራሂምም ልጆቹን በተመሳሳይ አዘዘ:: የዕቁብም እንደዚሁ በዚሁ ጉዳይ ልጆቹን አዘዘ:: (እንዲህም አለ) «ልጆቼ ሆይ! አላህ ለእናንተ ሀይማኖትን መረጠ:: ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ እንዳትሞቱ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ كُنتُمْ شُهَدَآءَ إِذْ حَضَرَ يَعْقُوبَ ٱلْمَوْتُ إِذْ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعْبُدُونَ مِنۢ بَعْدِى قَالُوا۟ نَعْبُدُ إِلَٰهَكَ وَإِلَٰهَ ءَابَآئِكَ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ إِلَٰهًا وَٰحِدًا وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy133. የዕቆብም ለጣዕረ ሞት በተዳረገበት ጊዜና ለልጆቹ «ከእኔ በኋላ ምንን ትገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ ነበራችሁን? እነርሱም «አንድ የሆነውን አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን፤ የኢስማዒልንና የኢስሃቅንም አምላክ እንገዛለን:: እኛም ለእርሱ ፍጹም ታዛዦች ሆነን እናመልከዋለን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ أُمَّةٌ قَدْ خَلَتْ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَلَكُم مَّا كَسَبْتُمْ وَلَا تُسْـَٔلُونَ عَمَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy134. እነኝህ (ከላይ የተወሱት ህዝቦች) በእርግጥ ያለፉ ሕዝቦች ናቸው:: ለእነርሱም የስራቸው ምንዳ አላቸው:: ለእናንተም የስራችሁ (ምንዳ) አላችሁ:: እነርሱ ይሰሩት በነበረው ፈጽሞ አትጠየቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ كُونُوا۟ هُودًا أَوْ نَصَٰرَىٰ تَهْتَدُوا۟ قُلْ بَلْ مِلَّةَ إِبْرَٰهِـۧمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ
Amharic Translation - Africa Academy135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድና ክርስቲያኖች በየበኩላቸው “አይሁድ ወይም ክርስቲያን ሁኑ ቅንን መንገድ ትመራላችሁና” አሉ:: “አይደለም ይልቁንም የኢብራሂምን ሀይማኖት ቀጥተኛ ሲሆን እንከተላለን፣ ኢብራሂምም ከአጋሪዎችም አልነበረም” በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَآ أُنزِلَ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطِ وَمَآ أُوتِىَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَآ أُوتِىَ ٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy136. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) «በአላህና ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሀቅም፣ ወደ የዕቁብና ወደ ነገዶችም በተወረደው መለኮታዊ መልዕክት ሁሉ በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት፤ በዚያም ነብያት ሁሉ ከጌታቸው በተለገሱት ከእነርሱ አንዱን ከሌላው የማንለይ ስንሆን አመንን:: እኛም (ለአላህ) ፍጹም ታዛዦች ነን።» በሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِنْ ءَامَنُوا۟ بِمِثْلِ مَآ ءَامَنتُم بِهِۦ فَقَدِ ٱهْتَدَوا۟ وَّإِن تَوَلَّوْا۟ فَإِنَّمَا هُمْ فِى شِقَاقٍ فَسَيَكْفِيكَهُمُ ٱللَّهُ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy137. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ ባመናችሁበት መልኩ ካመኑ በእርግጥ በትክክለኛው ጎዳና ላይ ናቸው:: ከእርሱ ካፈነገጡ ግን እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው:: የእነርሱንም ተንኮል አላህ ይበቃሀል:: እርሱም ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
صِبْغَةَ ٱللَّهِ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ ٱللَّهِ صِبْغَةً وَنَحْنُ لَهُۥ عَٰبِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy138. የአላህን የተፈጥሮ መንከር (እምነት) ያዙ:: በመንከርም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? (ማንም የለም):: እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን (በሉ)፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَتُحَآجُّونَنَا فِى ٱللَّهِ وَهُوَ رَبُّنَا وَرَبُّكُمْ وَلَنَآ أَعْمَٰلُنَا وَلَكُمْ أَعْمَٰلُكُمْ وَنَحْنُ لَهُۥ مُخْلِصُونَ
Amharic Translation - Africa Academy139. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ጌታችንና ጌታችሁ ሲሆን ለእኛም ስራችን ያለን ስንሆን ለእናንተም ስራችሁ ያላችሁ ስትሆኑ እኛም ስራችንን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች ሆነን ሳለን በአላህ (ሀይማኖት) ትከራከሩናላችሁን?» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ تَقُولُونَ إِنَّ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطَ كَانُوا۟ هُودًا أَوْ نَصَٰرَىٰ قُلْ ءَأَنتُمْ أَعْلَمُ أَمِ ٱللَّهُ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن كَتَمَ شَهَٰدَةً عِندَهُۥ مِنَ ٱللَّهِ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy140. ወይስ «ኢብራሂምም፣ ኢስማዒልም፣ ኢስሐቅም፣ ያዕቆብም፣ እንዲሁም ነገዶቹም አይሁድ ወይም ክርስቲያኖች ነበሩ» ትላላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) “እናንተ ናችሁ የምታውቁት? ወይንስ አላህ?” በላቸው:: እርሱ ዘንድ ከአላህ የሆነችን ምስክርነት ከደበቀ ይበልጥ አጥፊ ማነው? አላህ የምትፈጽሙትን ሁሉ ዘንጊ አይደለም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ أُمَّةٌ قَدْ خَلَتْ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَلَكُم مَّا كَسَبْتُمْ وَلَا تُسْـَٔلُونَ عَمَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy141. እነዚህ ያለፉ ሕዝቦች ናቸው:: ለእነርሱ የሰሩት አላቸው:: ለእናንተም የሰራችሁት አላችሁ:: እነርሱ ይሰሩት ከነበሩት ሁሉ አትጠየቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَيَقُولُ ٱلسُّفَهَآءُ مِنَ ٱلنَّاسِ مَا وَلَّىٰهُمْ عَن قِبْلَتِهِمُ ٱلَّتِى كَانُوا۟ عَلَيْهَا قُل لِّلَّهِ ٱلْمَشْرِقُ وَٱلْمَغْرِبُ يَهْدِى مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy142. ቂል የህብረተሰብ ክፍሎች «ከዚያች ከነበሩባት ቂብላቸው (አቅጣጫቻቸው) ምን አዞራቸው?» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው:: የሻውንም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَٰكُمْ أُمَّةً وَسَطًا لِّتَكُونُوا۟ شُهَدَآءَ عَلَى ٱلنَّاسِ وَيَكُونَ ٱلرَّسُولُ عَلَيْكُمْ شَهِيدًا وَمَا جَعَلْنَا ٱلْقِبْلَةَ ٱلَّتِى كُنتَ عَلَيْهَآ إِلَّا لِنَعْلَمَ مَن يَتَّبِعُ ٱلرَّسُولَ مِمَّن يَنقَلِبُ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ وَإِن كَانَتْ لَكَبِيرَةً إِلَّا عَلَى ٱلَّذِينَ هَدَى ٱللَّهُ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُضِيعَ إِيمَٰنَكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ بِٱلنَّاسِ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy143. እንደዚሁም (እንደመራናችሁ) ሁሉ በሰዎች ላይ መስካሪዎች ልትሆኑና መልዕክተኛዉም (ሙሐመድ) በእናንተ ላይ መስካሪ ይሆን ዘንድ መካከለኞች (ምርጥ) ማህበረሰብ (ህዝቦች) አደረግናችሁ:: ያችንም በእርሷ ላይ የነበርክባትን አቅጣጫ መልዕክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ልናውቅ (ልንለይ) (ልንገልጽ) እንጂ ቂብላን አላደረግናትም:: እርሷም በዚያ አላህ በመራቸው ሰዎች ላይ በስተቀር በእርግጥ ከባድ ናት:: አላህም እምነታችሁን (ስግደታችሁን) የሚያጠፋ አይደለም:: አላህም ለሰዎች በጣም ሩህሩህና አዛኝ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَدْ نَرَىٰ تَقَلُّبَ وَجْهِكَ فِى ٱلسَّمَآءِ فَلَنُوَلِّيَنَّكَ قِبْلَةً تَرْضَىٰهَا فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَحَيْثُ مَا كُنتُمْ فَوَلُّوا۟ وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُۥ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ لَيَعْلَمُونَ أَنَّهُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy144. የፊትህን ወደ ሰማይ ማንጋጠጥክን በእርግጥ ተመልክተናል:: እናም ወደ ምትወዳት (ከዕባ) ቂብላ እናዞርሃለን:: ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙር:: (ሙስሊሞች ሆይ!) የትም ስፍራ ብትሆኑ ስትሰግዱ ፊቶቻችሁን ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙሩ:: እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት መሆኑን ያውቃሉ:: አላህ ከሚሰሩት ስራ ዘንጊ አይደለም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَئِنْ أَتَيْتَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ بِكُلِّ ءَايَةٍ مَّا تَبِعُوا۟ قِبْلَتَكَ وَمَآ أَنتَ بِتَابِعٍ قِبْلَتَهُمْ وَمَا بَعْضُهُم بِتَابِعٍ قِبْلَةَ بَعْضٍ وَلَئِنِ ٱتَّبَعْتَ أَهْوَآءَهُم مِّنۢ بَعْدِ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ إِنَّكَ إِذًا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy145.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ መጽሐፍን ለተሰጡት ሕዝቦች የምትችለውን ያህል ተዓምር (መረጃ) ሁሉ ብታቀርብላቸው እንኳ ቂብላህን አይከተሉም:: አንተም ቂብላቸውን ተከታይ አይደለህም:: ከፊላቸዉም የከፊሉን ቂብላ አይከተሉም:: ከእውቀትም (ራእይ) ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ያን ጊዜ አንተ ከአጥፊዎች ትሆናለህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ ءَاتَيْنَٰهُمُ ٱلْكِتَٰبَ يَعْرِفُونَهُۥ كَمَا يَعْرِفُونَ أَبْنَآءَهُمْ وَإِنَّ فَرِيقًا مِّنْهُمْ لَيَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَهُمْ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy146. እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ሰዎች ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ሁሉ (ሙሐመድን) ያውቁታል:: ከእነርሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُمْتَرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy147. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው:: እናም ከተጠራጣሪዎችም አትሁን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِكُلٍّ وِجْهَةٌ هُوَ مُوَلِّيهَا فَٱسْتَبِقُوا۟ ٱلْخَيْرَٰتِ أَيْنَ مَا تَكُونُوا۟ يَأْتِ بِكُمُ ٱللَّهُ جَمِيعًا إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy148. ለሁሉም ለስግደት ፊታቸዉን የሚያዞሩባት አቅጣጫ አላቸው:: ወደ መልካም ስራዎችም ተሽቀዳደሙ:: የትም ስፍራ ብትሆኑ አላህ ሁላችሁንም ያመጣችኋል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَإِنَّهُۥ لَلْحَقُّ مِن رَّبِّكَ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ሁነህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አቅጣጫ አዙር:: እርሱም ከጌታህ የሆነ እርግጠኛ እውነት ነው:: አላህም ከምትሰሩት ስራ ሁሉ ዘንጊ አይደለም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَحَيْثُ مَا كُنتُمْ فَوَلُّوا۟ وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُۥ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَيْكُمْ حُجَّةٌ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْهُمْ فَلَا تَخْشَوْهُمْ وَٱخْشَوْنِى وَلِأُتِمَّ نِعْمَتِى عَلَيْكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy150.ከየትም ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከለለው መስጊድ አግጣጫ አዙር፡፡ በየትም ስፍራ ብትኾኑ ለሰዎቹ እነዚያ ከነሱ የበደሉት ሲቀሩ (ሃይማኖታችንን ይክዳሉ ቂብላችንን ይከተላሉ በማለት) በናንተ ላይ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው ፊቶቻችሁን ወደ አግጣጫው አዙሩ፡፡ አትፍሩዋቸውም፤ ፍሩኝም፤ (በዚህም ያዘዝኳችሁ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው) በናንተም ላይ ጸጋየን እንድሞላላችሁና (ወደ እውነትም) እንድትመሩ ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَمَآ أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُوا۟ عَلَيْكُمْ ءَايَٰتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا۟ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy151. ከመካከላችሁ ከናንተ የሆነን በእናንተ ላይ አናቅጻችንን የሚያነብላችሁ እና የሚያጠራችሁ መጽሐፉንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁን መልእክተኛ እንደላክን ሁሉ ጸጋን ሞላንላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱذْكُرُونِىٓ أَذْكُرْكُمْ وَٱشْكُرُوا۟ لِى وَلَا تَكْفُرُونِ
Amharic Translation - Africa Academy152. አስታውሱኝ አስታውሳችኋለሁና:: አመስግኑኝ አትካዱኝም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱسْتَعِينُوا۟ بِٱلصَّبْرِ وَٱلصَّلَوٰةِ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy153. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ታጋዙ (ጥንካሬን ፈልጉ):: አላህም ከታጋሾች ጋር ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَقُولُوا۟ لِمَن يُقْتَلُ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ أَمْوَٰتٌۢ بَلْ أَحْيَآءٌ وَلَٰكِن لَّا تَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy154. በአላህ መንገድ (ለሀይማኖቱ) የሚገደሉትን «ሙታን ናቸው።» አትበሉ:: በእውነቱ ሕያው ናቸውና:: እናንተ ግን አትገነዘቡትም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَىْءٍ مِّنَ ٱلْخَوْفِ وَٱلْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ ٱلْأَمْوَٰلِ وَٱلْأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَٰتِ وَبَشِّرِ ٱلصَّٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy155. ከፍርሀትና ከርሀብም ከሀብት፣ ከሕይወትና ከአዝመራ በመቀነስም በእርግጥ እንሞክራችኋለን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታጋሾችንም (በገነት) አብስር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ إِذَآ أَصَٰبَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوٓا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّآ إِلَيْهِ رَٰجِعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy156. እነዚያ መከራ በነካቸቻው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን። እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን።» የሚሉትን አብስር።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ عَلَيْهِمْ صَلَوَٰتٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَرَحْمَةٌ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy157. እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የሆኑ ምህረቶችና ችሮታም አሉ:: እነርሱም ወደ ቀናው መንገድ እውነት ተመሪዎቹ እነርሱው ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلصَّفَا وَٱلْمَرْوَةَ مِن شَعَآئِرِ ٱللَّهِ فَمَنْ حَجَّ ٱلْبَيْتَ أَوِ ٱعْتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَا وَمَن تَطَوَّعَ خَيْرًا فَإِنَّ ٱللَّهَ شَاكِرٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy158. የሶፋና የመርዋ (ጋራዎች) የአላህን ትዕዛዝ ከመፈጸሚያ ጉልህ ቦታዎች (ምልክቶች) ናቸው:: ካዕባን በሐጅ ወይም በዑምራ ስራ ምክኒያት የጎበኘ ሁሉ በሁለቱ ጋራዎች መካከል በመመላለሱ ምንም ኃጢአት የለበትም:: መልካምንም ስራ በፈቃደኝነት የሰራ (ሁሉ አላህ ይመነዳዋል):: አላህ አመሰጋኝና ሁሉን አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكْتُمُونَ مَآ أَنزَلْنَا مِنَ ٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلْهُدَىٰ مِنۢ بَعْدِ مَا بَيَّنَّٰهُ لِلنَّاسِ فِى ٱلْكِتَٰبِ أُو۟لَٰٓئِكَ يَلْعَنُهُمُ ٱللَّهُ وَيَلْعَنُهُمُ ٱللَّٰعِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy159. እነዚያ (ስለነብዩ ሙሐመድና ሌሎችም) ከአናቅጽና ቅን መመሪያዎች ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፍ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁትን ሁሉ አላህ ይረግማቸዋል:: ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُوا۟ وَأَصْلَحُوا۟ وَبَيَّنُوا۟ فَأُو۟لَٰٓئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ وَأَنَا ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy160. እነዚያ የተጸጸቱ፤ (ያበላሹትን) ያስተካከሉና (የደበቁትንም) የገለጹ ሲቀሩ:: የእነርሱን ጸጸትንማ እቀበላለሁ:: እኔም ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነኝ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَمَاتُوا۟ وَهُمْ كُفَّارٌ أُو۟لَٰٓئِكَ عَلَيْهِمْ لَعْنَةُ ٱللَّهِ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلنَّاسِ أَجْمَعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy161. እነዚያ በአላህ የካዱና በክህደታቸው ላይ እያሉ የሞቱ ሰዎች በእነርሱ ላይ የአላህ፤ የመላዕክትና የመላው የሰው ዘር ሁሉ እርግማን አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يُخَفَّفُ عَنْهُمُ ٱلْعَذَابُ وَلَا هُمْ يُنظَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy162. በእርግማን ውስጥም ሁልጊዜ ዘውታሪዎች ይሆናሉ:: ቅጣቱ ከእነርሱ አይቃለልም። ጊዜም አይሰጡም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلرَّحْمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy163. (ሰዎች ሆይ!) አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ከእርሱም ሌላ (ትክክለኛ) አምላክ የለም:: እርሱም እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ فِى خَلْقِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفِ ٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ وَٱلْفُلْكِ ٱلَّتِى تَجْرِى فِى ٱلْبَحْرِ بِمَا يَنفَعُ ٱلنَّاسَ وَمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مِن مَّآءٍ فَأَحْيَا بِهِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا وَبَثَّ فِيهَا مِن كُلِّ دَآبَّةٍ وَتَصْرِيفِ ٱلرِّيَٰحِ وَٱلسَّحَابِ ٱلْمُسَخَّرِ بَيْنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy164. የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና ቀንም መፈራረቅ (መተካካት)፤ ያችም ሰዎችን የሚጠቅም ነገር (ተጭና) በባህር ላይ የምትንሳፈፈው መርከብ፤ አላህም ከሰማይ ባወረደው ውሃና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ በእርሷም ውስጥ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በመበተኑ፤ ንፋሶችንም በየአቅጣጫው የሚያገላብጥ መሆኑ እንዲሁም በሰማይና በምድር በሚነዳው ዳመና ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ አያሌ ተዐምራት አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ وَلَوْ يَرَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓا۟ إِذْ يَرَوْنَ ٱلْعَذَابَ أَنَّ ٱلْقُوَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا وَأَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعَذَابِ
Amharic Translation - Africa Academy165. ከሰዎች መካከል ከአላህ ሌላ ባላንጣዎችን/ ጣዖታትን/ አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ሆነው የሚይዙ አሉ። እነዚያ ያመኑት ግን አላህን ከምንም በላይ ይወዳሉ:: እነዚያም የበደሉት ሰዎች ቅጣትን በትንሳኤ ቀን ባዩ ጊዜ ሀይል ሁሉ ለአላህ ብቻ መሆኑንና አላህም ቅጣቱ ብርቱ እንደሆነ ይገነዘባሉ:: በዚህች ዐለም ቢያውቁ ኖሮ (ባላንጣዎችን በመያዛቸው በተጸጸቱ ነበር)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ تَبَرَّأَ ٱلَّذِينَ ٱتُّبِعُوا۟ مِنَ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوا۟ وَرَأَوُا۟ ٱلْعَذَابَ وَتَقَطَّعَتْ بِهِمُ ٱلْأَسْبَابُ
Amharic Translation - Africa Academy166. (ይህም የሚሆነው) እነዚያ አስከታዮች ተከታዮቻቸውን በካዱበትና የሲዖልን ቅጣት ባዩ ጊዜ፤ በእነርሱም መካከል የግንኙነት መስመሮች ሁሉ በሚበጠስበት ጊዜ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوا۟ لَوْ أَنَّ لَنَا كَرَّةً فَنَتَبَرَّأَ مِنْهُمْ كَمَا تَبَرَّءُوا۟ مِنَّا كَذَٰلِكَ يُرِيهِمُ ٱللَّهُ أَعْمَٰلَهُمْ حَسَرَٰتٍ عَلَيْهِمْ وَمَا هُم بِخَٰرِجِينَ مِنَ ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy167. እነዚያም የተከተሉት «ለእኛ (ወደ ቅርቢቱ ዓለም) አንዲት ጊዜ መመለስ በኖረችንና ከእኛ እንደተጥራሩ ከእነርሱ በተጥራራን እንመኛለን» ይላሉ፡፡ እንደዚሁ አላህ ሥራዎቻቸውን በነርሱ ላይ ጸጸቶች አድርጎ ያሳያቸዋል፡፡ እነርሱም ከእሳት ወጪዎች አይደሉም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ كُلُوا۟ مِمَّا فِى ٱلْأَرْضِ حَلَٰلًا طَيِّبًا وَلَا تَتَّبِعُوا۟ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيْطَٰنِ إِنَّهُۥ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy168. እናንት ሰዎች ሆይ! በምድር ካለው ነገር የተፈቀደና ጣፋጭ የሆነን ምግብ ብሉ:: የሰይጣንንም ዱካዎች (እርምጃዎች) አትከተሉ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا يَأْمُرُكُم بِٱلسُّوٓءِ وَٱلْفَحْشَآءِ وَأَن تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy169. እርሱ የሚያዛችሁ በኃጢአትና በጸያፍ ነገርና በአላህ ላይ የማታውቁትን እንድትናገሩ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُوا۟ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُوا۟ بَلْ نَتَّبِعُ مَآ أَلْفَيْنَا عَلَيْهِ ءَابَآءَنَآ أَوَلَوْ كَانَ ءَابَآؤُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ شَيْـًٔا وَلَا يَهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy170. ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ የለም አባቶቻችንን በእርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር ብቻ እንከተላለን» ይላሉ:: አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና ወደ እውነት የማይመሩም ቢሆኑ ይከተሏቸዋልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَثَلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ كَمَثَلِ ٱلَّذِى يَنْعِقُ بِمَا لَا يَسْمَعُ إِلَّا دُعَآءً وَنِدَآءً صُمٌّۢ بُكْمٌ عُمْىٌ فَهُمْ لَا يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy171. የእነዚያም በአላህ የካዱት ምሳሌ ልክ እንደዚያ ድምጽንና ጥሪን እንጂ ሌላን በማይሰማ እንሰሳ ላይ እንደሚጮህ (እረኛ) ብጤ ነው:: እነርሱ (እውነትን የማይሰሙ) ደንቆሮዎች፤ (ሐቅን የማይናገሩ) ዲዳዎች፤ (ትክክለኛውን መንገድ የማያዩ) እውሮች ናቸው:: ምንንም ነገር የሚገነዘቡ አይደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُلُوا۟ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقْنَٰكُمْ وَٱشْكُرُوا۟ لِلَّهِ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy172. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሰጠናችሁ ሲሳዮች መካከል ጥሩውን ተመገቡ:: አላህንም በብቸኝነት የምታመልኩት ከሆናችሁ እሱኑ ብቻ አመስግኑት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ ٱلْمَيْتَةَ وَٱلدَّمَ وَلَحْمَ ٱلْخِنزِيرِ وَمَآ أُهِلَّ بِهِۦ لِغَيْرِ ٱللَّهِ فَمَنِ ٱضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَآ إِثْمَ عَلَيْهِ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy173. (አላህ) በእናንተ ላይ እርም ያደረገባችሁ በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ስጋንና ከአላህ ሌላ በሆነ ስም የታረደን ስጋ ብቻ ነው:: ተገዶ ችግሩን ለማስወገድ ያክል ብቻ ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይሆን (ቢመገብ) በእርሱ ላይ ምንም ሀጢአት የለበትም:: አላህ መሐሪና አዛኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكْتُمُونَ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَشْتَرُونَ بِهِۦ ثَمَنًا قَلِيلًا أُو۟لَٰٓئِكَ مَا يَأْكُلُونَ فِى بُطُونِهِمْ إِلَّا ٱلنَّارَ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ ٱللَّهُ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy174. እነዚያ አላህ ካወረደው መጽሐፍ (የትኛውንም ክፍል) የሚደብቁ፤ በሱ (በደበቁትም) ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ፤ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም:: አላህም በትንሳኤ ቀን አያናግራቸዉም:: ከኃጢአትም አያጠራቸዉምም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱشْتَرَوُا۟ ٱلضَّلَٰلَةَ بِٱلْهُدَىٰ وَٱلْعَذَابَ بِٱلْمَغْفِرَةِ فَمَآ أَصْبَرَهُمْ عَلَى ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy175. እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት ቅጣትንም በምህረት የለወጡ ናቸው:: በእሳት ላይ ምን ታጋሽ አደረጋቸው?!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ نَزَّلَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخْتَلَفُوا۟ فِى ٱلْكِتَٰبِ لَفِى شِقَاقٍۭ بَعِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy176. ይህም አላህ መጽሐፍን በእውነት ያወረደ በመሆኑና (በእርሱም በመካዳቸው ነው):: እነዚያም በመጽሐፉ የተለያዩት ከእውነት በራቀ ውዝግብ ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّيْسَ ٱلْبِرَّ أَن تُوَلُّوا۟ وُجُوهَكُمْ قِبَلَ ٱلْمَشْرِقِ وَٱلْمَغْرِبِ وَلَٰكِنَّ ٱلْبِرَّ مَنْ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلْكِتَٰبِ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ وَءَاتَى ٱلْمَالَ عَلَىٰ حُبِّهِۦ ذَوِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينَ وَٱبْنَ ٱلسَّبِيلِ وَٱلسَّآئِلِينَ وَفِى ٱلرِّقَابِ وَأَقَامَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَى ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلْمُوفُونَ بِعَهْدِهِمْ إِذَا عَٰهَدُوا۟ وَٱلصَّٰبِرِينَ فِى ٱلْبَأْسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَحِينَ ٱلْبَأْسِ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ صَدَقُوا۟ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy177. መልካምነት ፊቶቻችሁን ወደ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞራችሁ አይደለም። መልካምነት በአላህ፣ በመጨረሻው ቀን፣ በመላዕክት፣ በመጸሐፍት በነብያት ያመነ፤ ገንዘብንም ምንም ያህል የነዋይ (ገንዘብ) ፍቅር ቢኖረዉም ለዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለሚስኪኖች፣ ለመንገደኞች፣ ለለማኞች፣ ባሪያዎችን ነፃ ለማውጣት የሰጠ፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቆ የሰገደና ዘካንም ያወጣ ነው:: እንዲሁም ቃልኪዳን በገቡ ጊዜም ቃልኪዳናቸውን የሚሞሉ በችግር፣ በበሽታና በፍልሚያ ጊዜ ታጋሾች ናቸው። እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል:: አላህን የሚፈሩም ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلْقِصَاصُ فِى ٱلْقَتْلَى ٱلْحُرُّ بِٱلْحُرِّ وَٱلْعَبْدُ بِٱلْعَبْدِ وَٱلْأُنثَىٰ بِٱلْأُنثَىٰ فَمَنْ عُفِىَ لَهُۥ مِنْ أَخِيهِ شَىْءٌ فَٱتِّبَاعٌۢ بِٱلْمَعْرُوفِ وَأَدَآءٌ إِلَيْهِ بِإِحْسَٰنٍ ذَٰلِكَ تَخْفِيفٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَرَحْمَةٌ فَمَنِ ٱعْتَدَىٰ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَلَهُۥ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy178. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ግድያን በተመለከተ አጸፋዊ እርምጃ በእናንተ ላይ ተደንግጓል:: (እርሱም) ነፃ ሰውን በነፃ መግደል፤ ባሪያን በባሪያ መግደል፤ ሴትን በሴት መግደል::(ነው) ከሟች ወንድሙ ደም ትንሽ ነገር እንኳን ምህረት የተደረገለት ሰው በመሃሪው የሟች ወገን ላይ ካሳውን በመልካም መከታተል ሲኖርበት ምህረት የተደረገለት ገዳይም የነፍስ ዋጋውን ለእርሱ በመልካም አኳኋን መክፈል አለበት:: ይህ ከጌታችሁ የሆነ ማቃለልና እዝነት ነው:: ከዚህም በኋላ ህግን የተላለፈ ሰው እርሱ አሳማሚ ቅጣት ይጸናበታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَكُمْ فِى ٱلْقِصَاصِ حَيَوٰةٌ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy179. እናንተ ባለ አእምሮዎች ሆይ! በአጸፋዊ እርምጃ ህግ ሕይወትን ትጎናጸፋላችሁ:: ይህም ግድያን ከመፈጸም ልትጠነቀቁ ዘንድ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كُتِبَ عَلَيْكُمْ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ ٱلْمَوْتُ إِن تَرَكَ خَيْرًا ٱلْوَصِيَّةُ لِلْوَٰلِدَيْنِ وَٱلْأَقْرَبِينَ بِٱلْمَعْرُوفِ حَقًّا عَلَى ٱلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy180. በማንኛዉም ላይ ሞት በመጣበት ጊዜና ቀሪ ሀብት ያለው እንደሆነ ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች በአግባቡ መናዘዝ በእናንተ ላይ ተደንግጓል:: ይህ አላህን በሚፈሩ ላይ መፈጸም ያለበት ግዴታ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَنۢ بَدَّلَهُۥ بَعْدَ مَا سَمِعَهُۥ فَإِنَّمَآ إِثْمُهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ يُبَدِّلُونَهُۥٓ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy181. (ኑዛዜውን) ከሰማው በኋላ የለወጠው ኃጢአቱ በእነዚያ በሚለውጡት ላይ ብቻ ነው:: አላህም ሁሉን ሰሚ ሁሉን አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَنْ خَافَ مِن مُّوصٍ جَنَفًا أَوْ إِثْمًا فَأَصْلَحَ بَيْنَهُمْ فَلَآ إِثْمَ عَلَيْهِ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy182. ከተናዛዥም በኩል (ከእውነት) መዘንበልን ወይም (ከሲሶ የመጨመር) ኃጢአትን የፈራ (ያወቀ) ከዚያም በመካከላቸው ያስታረቀ በእርሱ ላይ ምንም ኃጢአት የለበትም:: አላህ በጣም መሀሪና በጣም አዛኝ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy183. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ፆም በእነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ ግዴታነቱ እንደተፃፈ ሁሉ በእናንተም ላይ ተደነገገ:: ልትጠነቀቁ ይከጀላልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَيَّامًا مَّعْدُودَٰتٍ فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ وَعَلَى ٱلَّذِينَ يُطِيقُونَهُۥ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ فَمَن تَطَوَّعَ خَيْرًا فَهُوَ خَيْرٌ لَّهُۥ وَأَن تَصُومُوا۟ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy184. ውስን ቀናትን ጹሙ። ከናንተም ውስጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ባልፆማቸው ቀናት ልክ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸውን ቀናት መፆም አለበት:: እነዚያ ለመፆም ከአቅም በላይ ችግር የገጠማቸው ሰዎች ደግሞ አፍጥረው ለየቀኑ እንድ ድሃን የአንድ ጊዜ ምግብ ማብላት ይኖርባቸዋል:: ከዚህ በላይ ቤዛን በመጨመር መልካምንም ስራ የፈቀደ ሰው (እርሱ ፈቅዶ መጨመሩ ለራሱ) በላጭ ተግባር ነው:: ግና በመንገድ ላይ ሆናችሁ መፆማቸሁ ለእናንተ የበለጠ ነው:: የምታውቁ ብትሆኑ ትመርጡታላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
شَهْرُ رَمَضَانَ ٱلَّذِىٓ أُنزِلَ فِيهِ ٱلْقُرْءَانُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَٰتٍ مِّنَ ٱلْهُدَىٰ وَٱلْفُرْقَانِ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ ٱلشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ يُرِيدُ ٱللَّهُ بِكُمُ ٱلْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ ٱلْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا۟ ٱلْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا۟ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَىٰكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy185. (ያ እንድትጾሙት የተደነገገላችሁ ወር) በእርሱ ዉስጥ ለሰዎች መሪ ሐቅን መንገድና እውነትን ከዉሸት የሚለየው ገላጭ ቁርአን የተወረደበት የረመዷን ወር ነው:: ከናንተ መካከል ወሩን ያገኘ ሁሉ ይጹመው:: በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ካፈጠረ ከሌሎች ቀናት ባልፆማቸው ቀናት ቁጥሮች ልክ መፆም አለበት:: አላህ ሁልጊዜም ለእናንተ ገሩን ነገር ይሻል እንጂ በእናንተ ላይ ጫናን መፍጠርን አይሻምና ነው። ለፆም የተወሰኑትን ቀናት ልትሞሉና አላህን ቅንኑ መንገድ ስለመራችሁ ልታከብሩትና ልታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገገላችሁ)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَنِّى فَإِنِّى قَرِيبٌ أُجِيبُ دَعْوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لِى وَلْيُؤْمِنُوا۟ بِى لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy186. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባሮቼ ስለ እኔ በጠየቁህ ጊዜ እኔ ቅርብ ነኝ:: የለማኝን ጸሎትም በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ:: ስለዚህ ወደ ቀናው መንገድ ይመሩ ዘንድ ለእኔ ብቻ ይታዘዙ:: በእኔም ብቻ ይመኑ። (በላቸው።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ ٱلصِّيَامِ ٱلرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَآئِكُمْ هُنَّ لِبَاسٌ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌ لَّهُنَّ عَلِمَ ٱللَّهُ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَخْتَانُونَ أَنفُسَكُمْ فَتَابَ عَلَيْكُمْ وَعَفَا عَنكُمْ فَٱلْـَٰٔنَ بَٰشِرُوهُنَّ وَٱبْتَغُوا۟ مَا كَتَبَ ٱللَّهُ لَكُمْ وَكُلُوا۟ وَٱشْرَبُوا۟ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكُمُ ٱلْخَيْطُ ٱلْأَبْيَضُ مِنَ ٱلْخَيْطِ ٱلْأَسْوَدِ مِنَ ٱلْفَجْرِ ثُمَّ أَتِمُّوا۟ ٱلصِّيَامَ إِلَى ٱلَّيْلِ وَلَا تُبَٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَٰكِفُونَ فِى ٱلْمَسَٰجِدِ تِلْكَ حُدُودُ ٱللَّهِ فَلَا تَقْرَبُوهَا كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy187. (ሙስሊሞች ሆይ!) በፆም ሌሊት ከሚስቶቻችሁ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ተፈቀደላችሁ:: እነርሱ ለእናንተ ልብሶች ናቸው:: እናንተም ለእነርሱ ልብሶች ናችሁና:: አላህ በዚህ ረገድ ነፍሶቻችሁን በማታለል ላይ መሆናችሁን ያውቃል::በእናንተም ላይ ተመለሰላችሁ፡፡ ከእናንተም ይቅርታ አደረገ፡፡ አሁን ተገናኙዋቸው፡፡ አላህም ለናንተ የጻፈላችሁን ነገር (ልጅን) ፈልጉ፡፡ ነጩ የንጋት ገመድ ከጥቁሩ የሌሊት ገመድ ለእናንተ እስከሚገለጽላችሁ ድረስ ብሉ:: ጠጡም:: ከዚያም ፆምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ:: እናንተ በመስጊዶች ተቀማጮች ኢዕቲካፍ ላይ ስትሆኑ ግን ሚስቶቻችሁን አትገናኙዋቸው:: ይህች የአላህ ህግጋት ናትና ለመተላለፍ አትቅረቧት:: ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ለሰዎች ያብራራል:: እነርሱ የተከለከሉትን ሊጠነቀቁ ይከጅላልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَأْكُلُوٓا۟ أَمْوَٰلَكُم بَيْنَكُم بِٱلْبَٰطِلِ وَتُدْلُوا۟ بِهَآ إِلَى ٱلْحُكَّامِ لِتَأْكُلُوا۟ فَرِيقًا مِّنْ أَمْوَٰلِ ٱلنَّاسِ بِٱلْإِثْمِ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy188. ገንዘቦቻችሁንም በመካከላችሁ በከንቱ (ያለ አግባብ) አትብሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትኾኑ ከሰዎች ገንዘቦች ከፊልን በኃጢኣት ትበሉ ዘንድ ወደ ዳኞች አትጣሏት፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْأَهِلَّةِ قُلْ هِىَ مَوَٰقِيتُ لِلنَّاسِ وَٱلْحَجِّ وَلَيْسَ ٱلْبِرُّ بِأَن تَأْتُوا۟ ٱلْبُيُوتَ مِن ظُهُورِهَا وَلَٰكِنَّ ٱلْبِرَّ مَنِ ٱتَّقَىٰ وَأْتُوا۟ ٱلْبُيُوتَ مِنْ أَبْوَٰبِهَا وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy189. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለለጋ ጨረቃ መለዋወጥ ይጠይቁሃል። «ይህ ክስተት ሰዎች ጊዜን ለመለካት የሚጠቀሙበትና የሐጅንም ወቅት ለማወቅ የሚረዳ ምልክት ነው:: መልካም ስራ ቤቶችን ከጀርባዎቻቸው መግባታችሁ አይደለም:: ይልቁንም የመልካም ስራ ባለቤት አላህን የሚፈራው ነው:: ቤቶችንም በፊት በሮቻቸው በኩል ግቡ:: አላህንም ፍሩ ከጀሀነም ቅጣት ልትድኑ ዘንድ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَٰتِلُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ يُقَٰتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلْمُعْتَدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy190. (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) እነዚያን የሚጋደሏችሁን ከሓዲያን በአላህ መንገድ ተጋደሉ:: ነገር ግን ድንበር አትለፉ :: አላህ ድንበር አላፊዎችን አይወድምና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱقْتُلُوهُمْ حَيْثُ ثَقِفْتُمُوهُمْ وَأَخْرِجُوهُم مِّنْ حَيْثُ أَخْرَجُوكُمْ وَٱلْفِتْنَةُ أَشَدُّ مِنَ ٱلْقَتْلِ وَلَا تُقَٰتِلُوهُمْ عِندَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ حَتَّىٰ يُقَٰتِلُوكُمْ فِيهِ فَإِن قَٰتَلُوكُمْ فَٱقْتُلُوهُمْ كَذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy191. ባገኛችኃቸዉም ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ካስወጧችሁም ስፍራ አስወጧቸው:: ፈተና (ሁክት) ከመግደል የከፋ ነውና:: በተከበረው መስጊድም ዘንድ በእርሱ ውስጥ እስከሚጋደሏችሁ ድረስ በእርሱ ውስጥ አትጋደሏቸው:: ከተጋደሏችሁ ግን ግደሏቸው:: የከሓዲያን ቅጣት ልክ እንደዚህ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِنِ ٱنتَهَوْا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy192. ከውጊያ ከታቀቡ ግን አላህ መሀሪና አዛኝ ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَٰتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ ٱلدِّينُ لِلَّهِ فَإِنِ ٱنتَهَوْا۟ فَلَا عُدْوَٰنَ إِلَّا عَلَى ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy193. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ፈተና (ሁከት) እስኪወገድና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስኪሆን ድረስ ተጋደሏቸው:: ከታቀቡ ግን የሀይል እርምጃ ድንበርን ባለፉ ላይ እንጂ (በሰላማዊ ላይ) አይጸናም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلشَّهْرُ ٱلْحَرَامُ بِٱلشَّهْرِ ٱلْحَرَامِ وَٱلْحُرُمَٰتُ قِصَاصٌ فَمَنِ ٱعْتَدَىٰ عَلَيْكُمْ فَٱعْتَدُوا۟ عَلَيْهِ بِمِثْلِ مَا ٱعْتَدَىٰ عَلَيْكُمْ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy194. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የተከበረው ወር በተከበረው ወር አንፃር ነው::ክብሮችም ሁሉ ተመሳሳዮች ናቸው፡፡ (ፍትሃዊ አጸፋዊ እርምጃ የተከበረን ህግ በጣሱ ላይ ተደንግጓል):: ወሰን ያለፈባችሁን በእናንተ ወሰን ባለፈው ቢጤ ወሰን ያለፈውን ያህል በእርሱም ላይ ወሰን እለፉበት:: አላህንም ፍሩ:: አላህ እርሱን ከሚፈሩት ጋር መሆኑንም እወቁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنفِقُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا تُلْقُوا۟ بِأَيْدِيكُمْ إِلَى ٱلتَّهْلُكَةِ وَأَحْسِنُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy195. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ለግሱ:: ራሳችሁንም በገዛ እጃችሁ ለጥፋት አትዳርጉ:: በበጎ ስራም ላይ ጽኑ:: አላህ በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَتِمُّوا۟ ٱلْحَجَّ وَٱلْعُمْرَةَ لِلَّهِ فَإِنْ أُحْصِرْتُمْ فَمَا ٱسْتَيْسَرَ مِنَ ٱلْهَدْىِ وَلَا تَحْلِقُوا۟ رُءُوسَكُمْ حَتَّىٰ يَبْلُغَ ٱلْهَدْىُ مَحِلَّهُۥ فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِيضًا أَوْ بِهِۦٓ أَذًى مِّن رَّأْسِهِۦ فَفِدْيَةٌ مِّن صِيَامٍ أَوْ صَدَقَةٍ أَوْ نُسُكٍ فَإِذَآ أَمِنتُمْ فَمَن تَمَتَّعَ بِٱلْعُمْرَةِ إِلَى ٱلْحَجِّ فَمَا ٱسْتَيْسَرَ مِنَ ٱلْهَدْىِ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٍ فِى ٱلْحَجِّ وَسَبْعَةٍ إِذَا رَجَعْتُمْ تِلْكَ عَشَرَةٌ كَامِلَةٌ ذَٰلِكَ لِمَن لَّمْ يَكُنْ أَهْلُهُۥ حَاضِرِى ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
Amharic Translation - Africa Academy196. ሐጅንና ዑምራን ለአላህ ብቻ ብላችሁ በትክክል ፈጽሙ:: ከጀመራችሁ በኋላ ብትታጉዱም ከመስዋአት የቻላችሁትን መሰዋት አለባችሁ:: መስዋእቱ ከመታረጃው ስፍራ እስኪደርስ ድረስም ራሶቻችሁን አትላጩ:: ከናንተም ውስጥ በሐጅ ላይ ሁኖ የታመመ ወይም በራስ ቅሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሰው ቢላጭ ከመፆም ወይም መስዋዕትን ቤዛ መስጠት አለበት:: ጸጥታም ባገኛችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ መፈጸሚያ ቀን ድረስ በዑምራ አስቀድሞ በመፈጸም የተገላገለ ሰው ከመስዋእቱ የተገራውን (የቻለዉን) መሰዋት አለበት:: ያላገኘም ሰው ሶስትን ቀናት በሐጅ (ወራት) ላይ ሰባትንም ቀናት ደግሞ በተመለሳችሁ ጊዜ መፆም አለበት:: እነዚህ ሙሉ አስር (ቀናት) ናቸው:: ይህም (ህግ) ቤተሰቦቹ ከቅዱሱ መስጊድ አቅራቢያ ላልሆኑ ነው:: አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ መሆኑንም እወቁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلْحَجُّ أَشْهُرٌ مَّعْلُومَٰتٌ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ ٱلْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِى ٱلْحَجِّ وَمَا تَفْعَلُوا۟ مِنْ خَيْرٍ يَعْلَمْهُ ٱللَّهُ وَتَزَوَّدُوا۟ فَإِنَّ خَيْرَ ٱلزَّادِ ٱلتَّقْوَىٰ وَٱتَّقُونِ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy197. ሐጅ የሚፈጸመው በተወሰኑ የታወቁ ወራት ነው:: እናም በእነርሱ ውስጥ ሐጅን ለመስራት ግዴታ የገባ ሰው በሐጅ ክንውን ውስጥ እያለ ሴትን መገናኘት፤ በአላህ ላይ ማመጽና ክርክር አያደርግም:: (ሙስሊሞች ሆይ!)የምትሰሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል። ስንቅም ያዙ:: ከስንቅ ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው:: የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! እኔን ብቻ ፍሩኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ أَن تَبْتَغُوا۟ فَضْلًا مِّن رَّبِّكُمْ فَإِذَآ أَفَضْتُم مِّنْ عَرَفَٰتٍ فَٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ عِندَ ٱلْمَشْعَرِ ٱلْحَرَامِ وَٱذْكُرُوهُ كَمَا هَدَىٰكُمْ وَإِن كُنتُم مِّن قَبْلِهِۦ لَمِنَ ٱلضَّآلِّينَ
Amharic Translation - Africa Academy198. በሐጅ ጊዜ (በስራ) ከጌታችሁ ችሮታን በመፈለጋችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ከአረፋት በተንቀሳቀሳችሁም ጊዜ መሸዐረል ሀራም ዘንድ ስትደርሱ አላህን አውሱ:: ወደ ቀናው የኢስላም መንገድ ስለመራችሁም አውሱት:: ቀደም ሲል በእርግጥ ከተሳሳቾች ነበራችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ أَفِيضُوا۟ مِنْ حَيْثُ أَفَاضَ ٱلنَّاسُ وَٱسْتَغْفِرُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy199. ከዚያ ሰዎች ከተንቀሳቀሱበት ስፍራ ተንቀሳቀሱ :: የአላህንም ምህረት ለምኑ:: አላህ በእጅጉ መሀሪና አዛኝ ነውና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِذَا قَضَيْتُم مَّنَٰسِكَكُمْ فَٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ كَذِكْرِكُمْ ءَابَآءَكُمْ أَوْ أَشَدَّ ذِكْرًا فَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَقُولُ رَبَّنَآ ءَاتِنَا فِى ٱلدُّنْيَا وَمَا لَهُۥ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنْ خَلَٰقٍ
Amharic Translation - Africa Academy200. የሐጅ ስራዎቻችሁን በፈጸማችሁ ጊዜ አባቶቻችሁን እንደምታወሱ ወይም ከእርሱም ይበልጥ በበረታ አላህን አውሱ:: ከሰዎችም መካከል፡- «ጌታችን ሆይ! በምድረ ዓለም መልካም እድልን ስጠን።» የሚል ሰው አለ:: ለእርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنْهُم مَّن يَقُولُ رَبَّنَآ ءَاتِنَا فِى ٱلدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِى ٱلْـَٔاخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy201. ከእነርሱም መካከል «ጌታችን ሆይ! በምድር ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱ ሀገርም ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን:: ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።» የሚሉ አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ نَصِيبٌ مِّمَّا كَسَبُوا۟ وَٱللَّهُ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ
Amharic Translation - Africa Academy202. እነዚያ ከሰሩት በጎ ስራ ድርሻ አላቸው:: አላህም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ فِىٓ أَيَّامٍ مَّعْدُودَٰتٍ فَمَن تَعَجَّلَ فِى يَوْمَيْنِ فَلَآ إِثْمَ عَلَيْهِ وَمَن تَأَخَّرَ فَلَآ إِثْمَ عَلَيْهِ لِمَنِ ٱتَّقَىٰ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّكُمْ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy203. (ሙስሊሞች ሆይ!) በእነዚያ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ አላህን አውሱ:: በሁለት ቀናት ውስጥ ለመሄድ የተቻኮለ ሰው በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም:: የቆየም ሰው ኃጢአት የለበትም:: ይህም (ምህረት) አላህን ለፈራ ሰው ሁሉ ነው:: አላህንም ፍሩ:: እናንተ ወደ እርሱ የምትሰበሰቡ መሆናችሁንም እወቁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُعْجِبُكَ قَوْلُهُۥ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَيُشْهِدُ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا فِى قَلْبِهِۦ وَهُوَ أَلَدُّ ٱلْخِصَامِ
Amharic Translation - Africa Academy204. ከሰዎችም መካከል እርሱ ክርክረ ብርቱ ሲሆን በቅርቢቱ ሕይወት ንግግሩ የሚያስደስትህ (የሚደንቅህ) ፤ በልቡ ውስጥ በሚያጠነጥነውም አላህን የሚያስመሰክር ሰው አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا تَوَلَّىٰ سَعَىٰ فِى ٱلْأَرْضِ لِيُفْسِدَ فِيهَا وَيُهْلِكَ ٱلْحَرْثَ وَٱلنَّسْلَ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلْفَسَادَ
Amharic Translation - Africa Academy205. (ካንተ) በዞረ ጊዜ በውስጧ ሊያበላሽና አዝመራንና እንሰሳዎችን ሊያጠፋ በምድር ላይ ይሮጣል:: አላህም ጥፋትን አይወድም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا قِيلَ لَهُ ٱتَّقِ ٱللَّهَ أَخَذَتْهُ ٱلْعِزَّةُ بِٱلْإِثْمِ فَحَسْبُهُۥ جَهَنَّمُ وَلَبِئْسَ ٱلْمِهَادُ
Amharic Translation - Africa Academy206. ለእርሱ “አላህን ፍራ” በተባለም ጊዜ ትዕቢት (በኃጢአት ስራ ላይ) ይገፋፋዋል። ገሀነምም ለእሱ በቂው ናት:: እርሷም በእርግጥ የከፋች ምንጣፍ ናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَشْرِى نَفْسَهُ ٱبْتِغَآءَ مَرْضَاتِ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ رَءُوفٌۢ بِٱلْعِبَادِ
Amharic Translation - Africa Academy207. ከሰዎችም ውስጥ የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲል ነፍሱን የሚሸጥም ሰው አለ:: አላህም ለባሮቹ በጣም ሩህሩህ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱدْخُلُوا۟ فِى ٱلسِّلْمِ كَآفَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا۟ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيْطَٰنِ إِنَّهُۥ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy208. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም ወደ አላህ መንገድ እስልምና ጠቅልላችሁ ግቡ:: የሰይጣንን እርምጃዎችም አትከተሉ፤ እርሱም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِن زَلَلْتُم مِّنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْكُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ فَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy209. ግልጽ ማስረጃዎች ከመጡላችሁ በኋላ እውነትን ከመቀበል ብታፈገፍጉ አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن يَأْتِيَهُمُ ٱللَّهُ فِى ظُلَلٍ مِّنَ ٱلْغَمَامِ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَقُضِىَ ٱلْأَمْرُ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرْجَعُ ٱلْأُمُورُ
Amharic Translation - Africa Academy210. አላህ በዳመና ጥላዎች ዉሥጥ ሆኖ እና መላዕክቱ ከያቅጣጫው ወደ እነርሱ እንዲመጡና ጉዳዩ እንዲወሰን እንጂ ሌላ ምንን ይጠባበቃሉ:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
سَلْ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ كَمْ ءَاتَيْنَٰهُم مِّنْ ءَايَةٍۭ بَيِّنَةٍ وَمَن يُبَدِّلْ نِعْمَةَ ٱللَّهِ مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْهُ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
Amharic Translation - Africa Academy211. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኢስራኢል ልጆችን ምን ያህል ግልጽ ተዐምር እንደሰጣናቸው ጠይቃቸው:: የአላህን ጸጋ ከመጣለት በኋላ ለሚለውጥ (ሰው አላህ ይቀጠዋል) አላህ ቅጣተ ብርቱ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
زُيِّنَ لِلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا وَيَسْخَرُونَ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ فَوْقَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَٱللَّهُ يَرْزُقُ مَن يَشَآءُ بِغَيْرِ حِسَابٍ
Amharic Translation - Africa Academy212. ለእነዚያ ለካዱት ባመኑት የሚሳለቁ ሲሆኑ ቅርቢቱ ሕይወት ተሸለመችላቸው:: እነዚያ አላህን የሚፈሩት በትንሳኤ ቀን ከበላያቸው ናቸው:: አላህም ለፈለገው ገጸ በረከቱን ያለገደብ ይሰጣልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَانَ ٱلنَّاسُ أُمَّةً وَٰحِدَةً فَبَعَثَ ٱللَّهُ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ وَأَنزَلَ مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ لِيَحْكُمَ بَيْنَ ٱلنَّاسِ فِيمَا ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ وَمَا ٱخْتَلَفَ فِيهِ إِلَّا ٱلَّذِينَ أُوتُوهُ مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ بَغْيًۢا بَيْنَهُمْ فَهَدَى ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لِمَا ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ مِنَ ٱلْحَقِّ بِإِذْنِهِۦ وَٱللَّهُ يَهْدِى مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy213. ሰዎች ሁሉ (አላህን አንድ በማድረግ) አንድ ሕዝብ ነበሩ:: (ከዚያም ተለያዩ):: ከዚያም አላህ ነብያትን ለመልካም ሰዎች በገነት አብሳሪዎችና ለመጥፎ ሰዎች ደግሞ ከእሳት አስጠንቃቂዎች አድርጎ ላከ:: ከነሱ ጋርም ከሰዎቹ መካከል በዚያ እነርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ መጽሐፍትን በእውነት አወረደ:: በእርሱ ግልጽ አስረጂዎች ከመጡላቸው በኋላ በመካከላቸው በተፈጠረው ምቀኝነት ሰበብ እነዚያው መጽሐፍትን የተሰጡት ሰዎች እንጂ አልተለያዩበትም:: አላህ እነዚያን በአላህ ያመኑትን ሰዎች በእነርሱ የተለያዩበትን እውነታ ይገነዘቡ ዘንድ በፈቃዱ መራቸው:: አላህ የሚሻውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا۟ ٱلْجَنَّةَ وَلَمَّا يَأْتِكُم مَّثَلُ ٱلَّذِينَ خَلَوْا۟ مِن قَبْلِكُم مَّسَّتْهُمُ ٱلْبَأْسَآءُ وَٱلضَّرَّآءُ وَزُلْزِلُوا۟ حَتَّىٰ يَقُولَ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ مَتَىٰ نَصْرُ ٱللَّهِ أَلَآ إِنَّ نَصْرَ ٱللَّهِ قَرِيبٌ
Amharic Translation - Africa Academy214. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት አማኞችን ያጋጠመ መከራ የመሰለ ሳይመጣባችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልዕክተኛውና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት «የአላህ እርዳታ መቼ ነው?» እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ደረሰባቸው:: ተርበደበዱም። (ሙስሊሞች ሆይ! ) አስተውሉ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው (አልናቸው)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَسْـَٔلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلْ مَآ أَنفَقْتُم مِّنْ خَيْرٍ فَلِلْوَٰلِدَيْنِ وَٱلْأَقْرَبِينَ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَا تَفْعَلُوا۟ مِنْ خَيْرٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِهِۦ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy215. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምንን እንደሚለግሱ ይጠይቁሃል። «ከየትኛዉም ሀብት የምትለግሱት ለወላጆች፣ ለቅርብ ዘመዶች፣ ለየቲሞች፣ ለድሆችና ለመንገደኞች (ሊሆን ይገባል።) ከበጎ ነገርም ማንኛውንም ብትሰሩ አላህ እርሱን አዋቂ ነው።»በላቸው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلْقِتَالُ وَهُوَ كُرْهٌ لَّكُمْ وَعَسَىٰٓ أَن تَكْرَهُوا۟ شَيْـًٔا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَعَسَىٰٓ أَن تُحِبُّوا۟ شَيْـًٔا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy216. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከሓዲያንን መጋደል በእናንተ ዘንድ የሚጠላ ቢሆንም በእናንተ ላይ በግዴታነት ተደነገገ:: አንድ ነገር ለእናንተ ጥሩ ቢሆንም ምናልባት ትጠሉት ይሆናል:: አንድንም ነገር እርሱ ለእናንተ መጥፎ ሆኖ እያለ ትወዱት ይሆናል:: አላህም የሚሻላችሁን ያውቃል:: እናንተ ግን አታውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلشَّهْرِ ٱلْحَرَامِ قِتَالٍ فِيهِ قُلْ قِتَالٌ فِيهِ كَبِيرٌ وَصَدٌّ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَكُفْرٌۢ بِهِۦ وَٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَإِخْرَاجُ أَهْلِهِۦ مِنْهُ أَكْبَرُ عِندَ ٱللَّهِ وَٱلْفِتْنَةُ أَكْبَرُ مِنَ ٱلْقَتْلِ وَلَا يَزَالُونَ يُقَٰتِلُونَكُمْ حَتَّىٰ يَرُدُّوكُمْ عَن دِينِكُمْ إِنِ ٱسْتَطَٰعُوا۟ وَمَن يَرْتَدِدْ مِنكُمْ عَن دِينِهِۦ فَيَمُتْ وَهُوَ كَافِرٌ فَأُو۟لَٰٓئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَأُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy217. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በተከበረው ወር ስለመጋደል ይጠይቁሃል። «በእነርሱ ውስጥ መጋደል ትልቅ ኃጢአት ነው:: ግን ከአላህ መንገድ ሰዎችን መከልከል፤ በእርሱም መካድ፤ ከተከበረው መስጊድ ማገድ፤ ባለቤቶቹንም ከእርሱ ማፈናቀል አላህ ዘንድ ይበልጥ የተለቀ ወንጀል ነው:: ፈተናም (በአላህ ማጋራትም) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው» በላቸው። ከሓዲያን ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስኪመልሷችሁ ድረስ የሚዋጓችሁ ከመሆን አይቦዝኑም:: ከናንተ ውስጥ ከሀይማኖቱ የሚመለስና እርሱ ከሃዲ ሆኖ የሚሞት ሁሉ እነዚያ በቅርቢቱ ሀገርም ሆነ በመጨረሻይቱ ሀገር በጎ ስራቸው ተበላሸች:: እነዚህ የእሳት ጓዶች ናቸው:: በእርሷም ውስጥ ለዘላለም ይዝወትራሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَٱلَّذِينَ هَاجَرُوا۟ وَجَٰهَدُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ أُو۟لَٰٓئِكَ يَرْجُونَ رَحْمَتَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy218. እነዚያ ያመኑና ከሀገራቸው የተሰደዱ፤ በአላህ መንገድ ላይም የተጋደሉ፤ እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ:: አላህም እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْخَمْرِ وَٱلْمَيْسِرِ قُلْ فِيهِمَآ إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَٰفِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَآ أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا وَيَسْـَٔلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ ٱلْعَفْوَ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy219. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዕምሮን ስለሚያሰክር መጠጥና ስለ ቁማር ይጠይቁሃል:: «በሁለቱም ትልቅ ኃጢአትነትና ለሰዎችም ጥቅም አለባቸው:: ኃጢአታቸው ግን ከጥቅማቸው በጣም የገዘፈ ነው።» በላቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምንን እንደሚመጸውቱም (መጠኑን) ይጠይቁሀል:: «የተረፋችሁን መጽውቱ።» በላቸው:: እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْيَتَٰمَىٰ قُلْ إِصْلَاحٌ لَّهُمْ خَيْرٌ وَإِن تُخَالِطُوهُمْ فَإِخْوَٰنُكُمْ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ ٱلْمُفْسِدَ مِنَ ٱلْمُصْلِحِ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَأَعْنَتَكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy220. በዱኒያም በአኼራም ታስተነትኑ ዘንድ ይገልፅላችኃል። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለየቲሞችም ይጠይቁሀል:: «የእነርሱን ሁኔታ ማሻሻል በላጭ ነው:: የእነርሱ ጉዳይ ከናንተ ጋር ብትቀላቅሉም ወንድሞቻችሁ ናቸው:: አላህም አጥፊውን ከአልሚው ለይቶ ያውቃል:: አላህም በፈለገ ኖሮ መፈናፈኛ ያሳጣችሁ (ባስቸገራችሁ) ነበር:: አላህ በሁሉም ነገር አሸናፊና ጥበበኛ ነው በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَنكِحُوا۟ ٱلْمُشْرِكَٰتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ وَلَأَمَةٌ مُّؤْمِنَةٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكَةٍ وَلَوْ أَعْجَبَتْكُمْ وَلَا تُنكِحُوا۟ ٱلْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا۟ وَلَعَبْدٌ مُّؤْمِنٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكٍ وَلَوْ أَعْجَبَكُمْ أُو۟لَٰٓئِكَ يَدْعُونَ إِلَى ٱلنَّارِ وَٱللَّهُ يَدْعُوٓا۟ إِلَى ٱلْجَنَّةِ وَٱلْمَغْفِرَةِ بِإِذْنِهِۦ وَيُبَيِّنُ ءَايَٰتِهِۦ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy221. (ሙስሊሞች ሆይ!) አጋሪዎችን ሴቶችን በአላህ እስከሚያምኑ ድረስ አታግቧቸው:: አጋሪይቱ ነፃ ሴት ምንም ብትስባችሁ እንኳ ያመነችው ባሪያ ሴት በእርግጥ ለእናንተ በላጭ ናት:: ለአጋሪዎቹ እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው:: ከአጋሪ ወንድ ምንም ቢስባችሁ አማኝ ባሪያዎች ለእናንተ በላጭ ናቸው:: እነዚያ አጋሪዎች ወደ እሳት ይጠራሉ:: አላህ ደግሞ ወደ ገነትና ወደ ምህረት ይጠራል:: ህግጋቱንም ለሰዎች ሊገሰጹ ዘንድ ይገልፅላቸዋል፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْمَحِيضِ قُلْ هُوَ أَذًى فَٱعْتَزِلُوا۟ ٱلنِّسَآءَ فِى ٱلْمَحِيضِ وَلَا تَقْرَبُوهُنَّ حَتَّىٰ يَطْهُرْنَ فَإِذَا تَطَهَّرْنَ فَأْتُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ أَمَرَكُمُ ٱللَّهُ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلتَّوَّٰبِينَ وَيُحِبُّ ٱلْمُتَطَهِّرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy222. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለ ሴቶች የወር አበባ ይጠይቁሃል:: «እርሱ ጎጂ (አጸያፊ) ነው። እናም ሚስቶቻችሁን በወር አበባቸው ጊዜ ራቁዋቸው፤ ደሙ ቆሞ ንጹህ እስከሚሆኑ ድረስ ለግንኙነት በፍጹም አትቅረቧቸው:: ንጹህ በሆኑ ጊዜም አላህ ባዘዛችሁ ቦታ ተገናኟቸው:: አላህ ከኃጢአት ተመላሾችንና ንጽህናን የሚጠብቁትን ይወዳልና።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
نِسَآؤُكُمْ حَرْثٌ لَّكُمْ فَأْتُوا۟ حَرْثَكُمْ أَنَّىٰ شِئْتُمْ وَقَدِّمُوا۟ لِأَنفُسِكُمْ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّكُم مُّلَٰقُوهُ وَبَشِّرِ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy223. ሚስቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው:: እናም እርሻዎቻችሁን በፈለጋችሁት ሁኔታ ግንኙነት ፈጽሙ:: ለነፍሶቻችሁ መልካም ስራን አስቀድሙ:: አላህንም ፍሩ:: እናንተም ከእርሱ ጋር የምትገናኙ መሆናችሁን እውቁ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችንም በገነት አብስራቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَجْعَلُوا۟ ٱللَّهَ عُرْضَةً لِّأَيْمَٰنِكُمْ أَن تَبَرُّوا۟ وَتَتَّقُوا۟ وَتُصْلِحُوا۟ بَيْنَ ٱلنَّاسِ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy224. (ሙስሊሞች ሆይ!) በአላህ ስም የፈጸማችሁት መሀላ በጎ ከመዋል አላህን ከመፍራትም ወይም በሰዎች መካከል እርቀ ሰላም ከማውረድ ግርዶ አታድርጉ:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّا يُؤَاخِذُكُمُ ٱللَّهُ بِٱللَّغْوِ فِىٓ أَيْمَٰنِكُمْ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا كَسَبَتْ قُلُوبُكُمْ وَٱللَّهُ غَفُورٌ حَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy225. ያለ አስተውሎት በምትፈጽሙት መሐላዎቻችሁ አላህ አይቀጣችሁም:: ግን ልቦቻችሁ በጽኑ ባሰቡበት መሐላዎቻችሁ ይይዛችኋል:: አላህ በጣም መሀሪ፤ ታጋሽ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّلَّذِينَ يُؤْلُونَ مِن نِّسَآئِهِمْ تَرَبُّصُ أَرْبَعَةِ أَشْهُرٍ فَإِن فَآءُو فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy226. እነዚያ ሚስቶቻቸውን ላለመገናኘት የሚምሉ ወንዶች ሁሉ ለማሰላሰያ ጊዜ አራት ወራት አላቸው:: እናም መሀላቸውን ቢያጥፉና ቢመለሱ አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنْ عَزَمُوا۟ ٱلطَّلَٰقَ فَإِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy227. ፍችን ለመፈጸም ጽኑ ውሳኔ ላይ ከደረሱ ደግሞ (ይፋቱ):: አላህም ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነዉና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْمُطَلَّقَٰتُ يَتَرَبَّصْنَ بِأَنفُسِهِنَّ ثَلَٰثَةَ قُرُوٓءٍ وَلَا يَحِلُّ لَهُنَّ أَن يَكْتُمْنَ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ فِىٓ أَرْحَامِهِنَّ إِن كُنَّ يُؤْمِنَّ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَبُعُولَتُهُنَّ أَحَقُّ بِرَدِّهِنَّ فِى ذَٰلِكَ إِنْ أَرَادُوٓا۟ إِصْلَٰحًا وَلَهُنَّ مِثْلُ ٱلَّذِى عَلَيْهِنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ وَلِلرِّجَالِ عَلَيْهِنَّ دَرَجَةٌ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy228. የተፈቱ ሴቶችም በራሳቸው ሶስትን የወር አበባ ይጠብቁ። በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ ከሆኑ አላህ በማህጸኖቻቸው ውስጥ የፈጠረውን ጽንስ ሊደብቁ አይፈቀድላቸዉም:: ባሎቻቸዉም እርቅን ከፈለጉ በእነዚህ ወራት ውስጥ የመመለስ መብታቸው ቅድሚያ ነው:: ለሴቶች ግዳጅ እንዳለባቸው ሁሉ ፍትሀዊ መብትም አላቸው:: ይሁንና ወንዶች (የበለጠ ሀላፊነትን ስለሚሸከሙ) ብልጫ አላቸው። (ተጥሎባቸዋል):: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلطَّلَٰقُ مَرَّتَانِ فَإِمْسَاكٌۢ بِمَعْرُوفٍ أَوْ تَسْرِيحٌۢ بِإِحْسَٰنٍ وَلَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَأْخُذُوا۟ مِمَّآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ شَيْـًٔا إِلَّآ أَن يَخَافَآ أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ ٱللَّهِ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ ٱللَّهِ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا فِيمَا ٱفْتَدَتْ بِهِۦ تِلْكَ حُدُودُ ٱللَّهِ فَلَا تَعْتَدُوهَا وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ ٱللَّهِ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy229. የመመለስ እድል የሚሰጠው ፍቺ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው:: ከዚያም በመልካም መያዝ ወይም በበጎ አኳኋን ማሰናበት ነው:: (ባሎች ሆይ!) የአላህን ህግጋት ያለማክበር ስጋት ካልኖረባቸው በስተቀር ከሰጣችኋቸው ነገር ምንንም ልትወስዱ ለእናንተ አይፈቀድላችሁም:: የአላህን ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ብትገነዘቡ ነፃ ለማውጣት በምትፈጽመው ነገር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: እኒህ የአላህ ሕግጋት ናቸው:: አትተላለፏቸው:: እነዚያ እነርሱ የአላህን ሕግጋት የሚተላለፉ ሁሉ (በደለኞች) አጥፊዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِن طَلَّقَهَا فَلَا تَحِلُّ لَهُۥ مِنۢ بَعْدُ حَتَّىٰ تَنكِحَ زَوْجًا غَيْرَهُۥ فَإِن طَلَّقَهَا فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَآ أَن يَتَرَاجَعَآ إِن ظَنَّآ أَن يُقِيمَا حُدُودَ ٱللَّهِ وَتِلْكَ حُدُودُ ٱللَّهِ يُبَيِّنُهَا لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy230. ከዚያም ለሶስተኛ ጊዜ ከፈታት በኋላ ሌላን ባል እስካላገባች (ከዚያም እስካልተፈታች ወይም እስካልሞተባት) ድረስ ለእርሱ አትፈቀደለትም:: ሁለተኛው ባል ከፈታት የአላህን ሕግጋት እንደሚጠብቁ ተስፋ ካደረጉ በመማለሳቸው በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለባቸውም:: እነኚህ የአላህ ሕግጋት ናቸው:: ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ ያብራራላቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَبَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ سَرِّحُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ وَلَا تُمْسِكُوهُنَّ ضِرَارًا لِّتَعْتَدُوا۟ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُۥ وَلَا تَتَّخِذُوٓا۟ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ هُزُوًا وَٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ وَمَآ أَنزَلَ عَلَيْكُم مِّنَ ٱلْكِتَٰبِ وَٱلْحِكْمَةِ يَعِظُكُم بِهِۦ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy231. (ሙስሊሞች ሆይ!) ሚስቶቻችሁን በፈታችሁ እና የኢዳ ጊዜያቸውን ለማገባደድ በቀረቡ ጊዜ በመልካም መልሷቸው:: ወይም በመልካም ሁኔታ ያለ አንድ ጉዳት አሰናብቷቸው:: ለመጉዳትም ወሰን ታልፉባቸው ዘንድ አትያዟቸው:: ይህን የሚሰራም ነፍሱን በእርግጥ በደለ:: የአላህን አናቅጽ ማላገጫ አታድርጉ:: አላህ በእናንተ ላይ የዋለውን ጸጋ፤ በእርሱ ሊገስፃችሁም ያወረደውን መጽሐፍ (ቁርኣንን) እና ጥበብንም (ሱናን) አስታውሱ:: አላህንም ፍሩ:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ አዋቂ መሆኑንም እወቁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَبَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَلَا تَعْضُلُوهُنَّ أَن يَنكِحْنَ أَزْوَٰجَهُنَّ إِذَا تَرَٰضَوْا۟ بَيْنَهُم بِٱلْمَعْرُوفِ ذَٰلِكَ يُوعَظُ بِهِۦ مَن كَانَ مِنكُمْ يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ ذَٰلِكُمْ أَزْكَىٰ لَكُمْ وَأَطْهَرُ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy232. ሚስቶቻችሁን በፈታችሁ እና የኢዳ ጊዜያቸውን በጨረሱ ጊዜ ጥንዶቹ በመካከላቸው ሕጋዊና ፍትሀዊ የጋራ ስምምነት ላይ ከደረሱ ባሎቻቸውን ከማግባት አታስተጓጉሏቸው:: ይህ ከናንተ መካከል በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን ሁሉ ይገሰጽበታል:: ይህ ለእናንተ በላጭና አጥሪ ነው:: አላህ ያውቃል:: እናንተ ግን አታውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْوَٰلِدَٰتُ يُرْضِعْنَ أَوْلَٰدَهُنَّ حَوْلَيْنِ كَامِلَيْنِ لِمَنْ أَرَادَ أَن يُتِمَّ ٱلرَّضَاعَةَ وَعَلَى ٱلْمَوْلُودِ لَهُۥ رِزْقُهُنَّ وَكِسْوَتُهُنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ لَا تُكَلَّفُ نَفْسٌ إِلَّا وُسْعَهَا لَا تُضَآرَّ وَٰلِدَةٌۢ بِوَلَدِهَا وَلَا مَوْلُودٌ لَّهُۥ بِوَلَدِهِۦ وَعَلَى ٱلْوَارِثِ مِثْلُ ذَٰلِكَ فَإِنْ أَرَادَا فِصَالًا عَن تَرَاضٍ مِّنْهُمَا وَتَشَاوُرٍ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا وَإِنْ أَرَدتُّمْ أَن تَسْتَرْضِعُوٓا۟ أَوْلَٰدَكُمْ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِذَا سَلَّمْتُم مَّآ ءَاتَيْتُم بِٱلْمَعْرُوفِ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy233. እናቶች ልጆቻቸውን ሁለት ሙሉ ዓመታትን ያጠባሉ:: ይህም ማጥባትን የተሟላ ለማድረግ ለፈለገ ሰው ነው:: በአባት ላይ ምግባቸውንና ልብሳቸውን የማቅረብ ግዴታ አለበት:: ማንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አትገደድምና:: እናት በልጇ ምክኒያት ጉዳት እንዲደርስባት አይደረግም:: አባትም በልጁ ምክንያት እንዲንገላታ መሆን የለበትም:: በወራሽም ላይ የዚሁ ተመሳሳይ ሀላፊነት አለበት:: ወላጆቹ በመልካም ፈቃድ ልጁን ከጡት መነጠል (ማስጣል) ቢፈልጉ በሁለቱም መማከር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: ለልጆቻችሁ አጥቢዎችን ብትቀጥሩ ተስፋ የሰጣችሁትን ክፍያ በአግባቡ እስከሰጣችሁ ድረስ በማስጠባታችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህን ፍሩ:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች መሆኑን እወቁ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ يُتَوَفَّوْنَ مِنكُمْ وَيَذَرُونَ أَزْوَٰجًا يَتَرَبَّصْنَ بِأَنفُسِهِنَّ أَرْبَعَةَ أَشْهُرٍ وَعَشْرًا فَإِذَا بَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِيمَا فَعَلْنَ فِىٓ أَنفُسِهِنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy234. (ወንዶች ሆይ!) እነዚያ ከናንተ ውስጥ የሚሞቱና ሚስቶችን የሚተው ሚስቶቻቸው በራሳቸው አራት ወር ከአስር ቀናትን ከጋብቻ ይታገሱ:: ጊዜያቸውንም በጨረሱ ጊዜ በራሳቸው ተነሳሽነት በሚፈጽሙት ሕጋዊ ተግባር በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِيمَا عَرَّضْتُم بِهِۦ مِنْ خِطْبَةِ ٱلنِّسَآءِ أَوْ أَكْنَنتُمْ فِىٓ أَنفُسِكُمْ عَلِمَ ٱللَّهُ أَنَّكُمْ سَتَذْكُرُونَهُنَّ وَلَٰكِن لَّا تُوَاعِدُوهُنَّ سِرًّا إِلَّآ أَن تَقُولُوا۟ قَوْلًا مَّعْرُوفًا وَلَا تَعْزِمُوا۟ عُقْدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ ٱلْكِتَٰبُ أَجَلَهُۥ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِىٓ أَنفُسِكُمْ فَٱحْذَرُوهُ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy235. (ወንዶች ሆይ!) ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች የጋብቻ (አሽሙር) ፍንጭ በመስጠታችሁ ወይም እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ በውስጣችሁ በማሰባችሁ ምክንያት በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ እናንተ በእርግጥ እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ እንደምታስተናግዱ ቀድሞውኑ ያውቃል:: ስለዚህ (አሽሙር) ፍንጭ መስጠትንና ማሰብን ፈቀደላችሁ:: ግና በሕግ የታወቀን ጨዋ ንግግር የምትነጋገሩ ካልሆናችሁ በስተቀር የተፃፈው የኢዳ ጊዜው እስከሚደርስ ድረስ ለትዳር እንደምትፈልጓቸው በሚስጥር ቃል አትግቡላቸው:: ጋብቻን ለመዋዋልም ቁርጥ ሀሳብ አታድርጉ:: አላህ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን እወቁ:: ተጠንቀቁም፤ አላህ መሀሪና ታጋሽ መሆኑንም እወቁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ مَا لَمْ تَمَسُّوهُنَّ أَوْ تَفْرِضُوا۟ لَهُنَّ فَرِيضَةً وَمَتِّعُوهُنَّ عَلَى ٱلْمُوسِعِ قَدَرُهُۥ وَعَلَى ٱلْمُقْتِرِ قَدَرُهُۥ مَتَٰعًۢا بِٱلْمَعْرُوفِ حَقًّا عَلَى ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy236. (ባሎች ሆይ!) ሴቶችን ግንኙነት ከማድረግ በፊት ወይም ለእነርሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: ነገር ግን ሀብታምም ደሃም እንደየአቅማቸው ይካሷቸው:: ይህ አቅምን መሰረት ያደረገ ካሳ በቅን ሰዎች ላይ የተደነገገ ህግ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِن قَبْلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ وَقَدْ فَرَضْتُمْ لَهُنَّ فَرِيضَةً فَنِصْفُ مَا فَرَضْتُمْ إِلَّآ أَن يَعْفُونَ أَوْ يَعْفُوَا۟ ٱلَّذِى بِيَدِهِۦ عُقْدَةُ ٱلنِّكَاحِ وَأَن تَعْفُوٓا۟ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ وَلَا تَنسَوُا۟ ٱلْفَضْلَ بَيْنَكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy237. (ባሎች ሆይ!) ለሚስቶቻችሁ መህርን የወሰናችሁላቸው ስትሆኑ ሳትገናኟቸው በፊት ብትፈቷቸው ራሳቸው ይቅር ካላሉ ወይም ያ የጋብቻ ውል በእጁ የሆነ ባል ካላግራራ በስተቀር ከወሰናችሁት ግማሹን መስጠት ግድ ሆኖባችኋል:: ሁላችሁም ይቅር መባባላችሁ ወደ አላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው:: አንዱ ለሌላው በጎ መዋልን አይዘንጋ:: አላህም የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
حَٰفِظُوا۟ عَلَى ٱلصَّلَوَٰتِ وَٱلصَّلَوٰةِ ٱلْوُسْطَىٰ وَقُومُوا۟ لِلَّهِ قَٰنِتِينَ
Amharic Translation - Africa Academy238. (ሙስሊሞች ሆይ!) ሶላቶችን በተለይ መካከለኛይቱን ሶላት ወቅታቸውንና ስርዓታቸውን ጠብቃችሁ ስገዱ:: በሙሉ ታዛዥነትም ለአላህ ቁሙ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِنْ خِفْتُمْ فَرِجَالًا أَوْ رُكْبَانًا فَإِذَآ أَمِنتُمْ فَٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ كَمَا عَلَّمَكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا۟ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy239. (ሙስሊሞች ሆይ!) የደህንነት ስጋት ሲኖር በእግር እየሄዳችሁም ሆነ ተሳፍራች ስገዱ:: ሰላም ሲሰፍን በተለመደው ሥርዓት (ስገዱ።) ታውቁት ያልነበራችሁትን እንዳሳወቃችሁ ሁሉ አላህን በአግባቡ አውሱ (ስገዱ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ يُتَوَفَّوْنَ مِنكُمْ وَيَذَرُونَ أَزْوَٰجًا وَصِيَّةً لِّأَزْوَٰجِهِم مَّتَٰعًا إِلَى ٱلْحَوْلِ غَيْرَ إِخْرَاجٍ فَإِنْ خَرَجْنَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِى مَا فَعَلْنَ فِىٓ أَنفُسِهِنَّ مِن مَّعْرُوفٍ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy240. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እነዚያ ከናንተ ውስጥ ሚስቶችን ትተው የሚሞቱ ሁሉ ለሚስቶቻቸው ከየቤቶቻቸው የማይወጡ ሆነው ሳለ ዓመት ድረስ ወጫቸው እንዲሸፈን መናዘዝ ይኖርባቸዋል:: ሚስቶች በፈቃዳቸው ከቤት ቢወጡ ግን ደንብ ጠብቀውና ኃላፊነትን ወስደው በሰሩት ጉዳይ ላይ በሟች ዘመዶች ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِلْمُطَلَّقَٰتِ مَتَٰعٌۢ بِٱلْمَعْرُوفِ حَقًّا عَلَى ٱلْمُتَّقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy241. ለተፈቱ ሴቶች ሁሉ በፈችው ባል ችሎታ መጠን ዳረጎት (የገንዘብ ድጎማ) ይሰጣቸዋል:: ይህ አላህን በሚፈሩ ሰዎች ሁሉ ላይ ተደንግጓል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy242. ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ ያብራራላችኋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ خَرَجُوا۟ مِن دِيَٰرِهِمْ وَهُمْ أُلُوفٌ حَذَرَ ٱلْمَوْتِ فَقَالَ لَهُمُ ٱللَّهُ مُوتُوا۟ ثُمَّ أَحْيَٰهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy243. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብዙ ሺህ ሆነው ሞትን በመፍራት ከሀገሮቻቸው የወጡ ሰዎችን ታሪክ አላየህምን (አላወክምን?) አላህ ለእነርሱ «ሙቱ» አላቸው:: ሞቱም:: ከዚያ እንደገና ነፍስ ዘራባቸው:: አላህም ለሰዎች እጅግ ቸር ነው:: ይሁንና አብዛሀኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَٰتِلُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy244. (ሙስሊሞች ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ተጋደሉ:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ መሆኑንም እወቁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّن ذَا ٱلَّذِى يُقْرِضُ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَٰعِفَهُۥ لَهُۥٓ أَضْعَافًا كَثِيرَةً وَٱللَّهُ يَقْبِضُ وَيَبْصُۜطُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy245. ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና አላህም ብዙ እጥፍ ድርብ አድርጎ እንዲከፍለው የሚሻ ማን ነው? አላህ ለፈለገው ሰው ሲሳዩን ያጠብበታል፤ ለፈለገው ደግሞ ያሰፋለታልም:: ወደ እርሱ ብቻ ትመለሳላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلْمَلَإِ مِنۢ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ مِنۢ بَعْدِ مُوسَىٰٓ إِذْ قَالُوا۟ لِنَبِىٍّ لَّهُمُ ٱبْعَثْ لَنَا مَلِكًا نُّقَٰتِلْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ قَالَ هَلْ عَسَيْتُمْ إِن كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلْقِتَالُ أَلَّا تُقَٰتِلُوا۟ قَالُوا۟ وَمَا لَنَآ أَلَّا نُقَٰتِلَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَقَدْ أُخْرِجْنَا مِن دِيَٰرِنَا وَأَبْنَآئِنَا فَلَمَّا كُتِبَ عَلَيْهِمُ ٱلْقِتَالُ تَوَلَّوْا۟ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌۢ بِٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy246. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስራኢል ልጆች ከሙሳ ዘመን በኋላ ወደ ነበሩት የቤተ-ኢስራኢል ቅምጥሎች ተልኮላቸው ለነበረው ለነብያቸው «ለእኛ ንጉስን ሹምልን እና በአላህ መንገድ እንዋጋ።» ባሉ ጊዜ የሆነውን አላየህምን? እሱም «መዋጋት ቢፃፍባችሁ አትዋጉ ይሆናል።» አላቸው:: እነርሱም «ከአገሮቻችንና ከልጆቻችን ተባረን ሳለ በአላህ መንገድ የማንዋጋበት ምን ምክንያት አለን?» አሉ:: በእነርሱ ላይ መዋጋት በተፃፈባቸው ጊዜ ግን ከእነርሱ ጥቂቶች ሲቀሩ ከመዋጋት አፈገፈጉ:: አላህ አጥፊዎችን ሁሉ በሚገባ ያውቃቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ قَدْ بَعَثَ لَكُمْ طَالُوتَ مَلِكًا قَالُوٓا۟ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُ ٱلْمُلْكُ عَلَيْنَا وَنَحْنُ أَحَقُّ بِٱلْمُلْكِ مِنْهُ وَلَمْ يُؤْتَ سَعَةً مِّنَ ٱلْمَالِ قَالَ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُۥ بَسْطَةً فِى ٱلْعِلْمِ وَٱلْجِسْمِ وَٱللَّهُ يُؤْتِى مُلْكَهُۥ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy247. ነብያቸው ‹‹አላህ ጧሉትን ንጉስ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ›› አላቸው:: እነርሱም፡- «ሰፊ ሀብትም ያልተሰጠ እኛም ከእርሱ ይልቅ ለንግስና ተገቢዎች ስንሆን እርሱ በእኛ ላይ እንዴት ይነግሣል?» አሉ:: ነብያቸዉም፡- «አላህ በእናንተ ላይ መረጠው እውቀትና የሰውነት ጥንካሬም አጎናጽፎታል:: አላህ ንግስናውን ለሚሻለት ሰው ይሰጣል:: አላህ ችሮታው ሰፊና አዋቂ ነው።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ ءَايَةَ مُلْكِهِۦٓ أَن يَأْتِيَكُمُ ٱلتَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ ءَالُ مُوسَىٰ وَءَالُ هَٰرُونَ تَحْمِلُهُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy248. በተጨማሪም ነብያቸው እንዲህ አላቸው:: «የንግስናው ምልክት መላእክት የሚሸከሙት ሳጥን ወደ እናንተ ይመጣል:: በውስጡ ለናንተ እርጋታን የሚፈጥርና የሙሳ እና የሀሩን ቤተሰብ የተውት ቅርስም ይገኝበታል:: በዚህም ውስጥ ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ ከባድ ተዐምር አለላችሁ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِٱلْجُنُودِ قَالَ إِنَّ ٱللَّهَ مُبْتَلِيكُم بِنَهَرٍ فَمَن شَرِبَ مِنْهُ فَلَيْسَ مِنِّى وَمَن لَّمْ يَطْعَمْهُ فَإِنَّهُۥ مِنِّىٓ إِلَّا مَنِ ٱغْتَرَفَ غُرْفَةًۢ بِيَدِهِۦ فَشَرِبُوا۟ مِنْهُ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ فَلَمَّا جَاوَزَهُۥ هُوَ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ قَالُوا۟ لَا طَاقَةَ لَنَا ٱلْيَوْمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِۦ قَالَ ٱلَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَٰقُوا۟ ٱللَّهِ كَم مِّن فِئَةٍ قَلِيلَةٍ غَلَبَتْ فِئَةً كَثِيرَةًۢ بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy249. ጧሉትም በሰራዊቱ ታጅቦ በመጣ ጊዜ ‹‹አላህ በወንዝ ውሃ ይፈትናችኃል:: እናም ከእርሱ የጠጣ ሰው ሁሉ ከእኔ አይደለም:: እሱን ያልቀመሰው ሰው ግን በእጁ አንድ እፍኝ ያህል የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው›› አለ:: ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች ሲቀሩ ከእርሱ ጠጡ:: እርሱና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሉትን (ጎልያድን) እና ሰራዊቱን ለመዋጋት በቂ ችሎታና ጥንካሬ የለንም።» አሉት:: እነዚያ ከአላህ ጋር እንደሚገናኙ የሚያረጋግጡትም «ጥቂት ቡድን በአላህ ፈቃድ ብዙውን ቡድን ያሸነፈበት አጋጣሚ ብዙ ነው:: አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَمَّا بَرَزُوا۟ لِجَالُوتَ وَجُنُودِهِۦ قَالُوا۟ رَبَّنَآ أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَٱنصُرْنَا عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy250. ለጃሉትና ለሰራዊቱ በተሰለፉም ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! ትግስትን ለግሰን:: እግሮቻችንን አጽናልን:: በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُۥدُ جَالُوتَ وَءَاتَىٰهُ ٱللَّهُ ٱلْمُلْكَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَهُۥ مِمَّا يَشَآءُ وَلَوْلَا دَفْعُ ٱللَّهِ ٱلنَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّفَسَدَتِ ٱلْأَرْضُ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ ذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy251. እናም በአላህ ፈቃድ ድል መቷቸው:: ነብዩ ዳውድም ጃሉትን ገደለ:: ለዳውድ ንግሥናን፤ ጥበብን እና ነብይነትን አላህ ሰጣቸው:: ከሚሻው ነገር ሁሉ አሳወቀው:: አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መመለሱ (መከላከሉ) ባልነበረ ኖሮ ምድር በጠቅላላ በተበላሸች ነበር:: ግን አላህ በዓለማት ላይ የችሮታ ባለቤት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِٱلْحَقِّ وَإِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy252. እነዚህ አናቅጽ በእውነት ባንተ ላይ የምናነባቸው ሲሆኑ የአላህ አናቅጽ ናቸው:: አንተም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ መካከል አንዱ ነህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تِلْكَ ٱلرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ مِّنْهُم مَّن كَلَّمَ ٱللَّهُ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَٰتٍ وَءَاتَيْنَا عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ ٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَيَّدْنَٰهُ بِرُوحِ ٱلْقُدُسِ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ مَا ٱقْتَتَلَ ٱلَّذِينَ مِنۢ بَعْدِهِم مِّنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ وَلَٰكِنِ ٱخْتَلَفُوا۟ فَمِنْهُم مَّنْ ءَامَنَ وَمِنْهُم مَّن كَفَرَ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ مَا ٱقْتَتَلُوا۟ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَفْعَلُ مَا يُرِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy253. እነዚያን መልዕክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን:: ከእነርሱ መካከልም አላህ ያነጋገረው አለ:: ከፊሎቻቸውንም በደረጃ ከሌሎች ከፍ አድርጓል:: የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተዐምራት ሰጠነው:: በቅዱስ መንፈስም (በመላኩ ጂብሪል) አበረታነው:: አላህ በፈለገ ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ በኋላ የነበሩት መረጃው ከመጣላቸው በኋላ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር:: ግን ተለያዩ:: በመሆኑም ከመሀከላቸው ትክክለኛ አማኝ ክፍል አለ:: ከመሀከላቸዉም ከሃዲ አለ:: አላህ በፈለገ ኖሮ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር:: አላህ ግን የሚሻውን ሁሉ ይሰራል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَنفِقُوا۟ مِمَّا رَزَقْنَٰكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِىَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خُلَّةٌ وَلَا شَفَٰعَةٌ وَٱلْكَٰفِرُونَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy254. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ያ ንግድ፤ ወዳጅነትም ሆነ ምልጃ የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ:: በዳዮች ማለት ከሓዲያን ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْحَىُّ ٱلْقَيُّومُ لَا تَأْخُذُهُۥ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ مَن ذَا ٱلَّذِى يَشْفَعُ عِندَهُۥٓ إِلَّا بِإِذْنِهِۦ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَىْءٍ مِّنْ عِلْمِهِۦٓ إِلَّا بِمَا شَآءَ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَلَا يَـُٔودُهُۥ حِفْظُهُمَا وَهُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْعَظِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy255. አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ምንግዜም ሕያው፤ በራሱ የተብቃቃ ነው:: ማንጎላጀትም ሆነ እንቅልፍ አትይዘዉም:: በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማን ነው? (ከፍጡራን) ሁሉ በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል:: በሻው ነገር እንጂ ከእውቀቱ (ፍጡራን) በምንም ነገር አያካብቡም:: መንበሩ የሰማያትንና የምድርን ስፋት ይበልጣል:: ጥበቃቸዉም አያቅተዉም:: እርሱ የሁሉ የበላይና ታላቅ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَآ إِكْرَاهَ فِى ٱلدِّينِ قَد تَّبَيَّنَ ٱلرُّشْدُ مِنَ ٱلْغَىِّ فَمَن يَكْفُرْ بِٱلطَّٰغُوتِ وَيُؤْمِنۢ بِٱللَّهِ فَقَدِ ٱسْتَمْسَكَ بِٱلْعُرْوَةِ ٱلْوُثْقَىٰ لَا ٱنفِصَامَ لَهَا وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy256. በሃይማኖት ማስገደድ የለም:: ቅኑ መንገድ ከጠማማው መንገድ በእርግጥ ተገለጠ:: በጣኦት (ባዕድ አምልኮ) የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ሁሉ የማትበጠስ ጠንካራ ገመድን ጨብጧል:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ وَلِىُّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ يُخْرِجُهُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَوْلِيَآؤُهُمُ ٱلطَّٰغُوتُ يُخْرِجُونَهُم مِّنَ ٱلنُّورِ إِلَى ٱلظُّلُمَٰتِ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy257. አላህ የአማኞች ወዳጅ ነው:: ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል:: እነዚያ አላህን የካዱት ግን ረዳቶቻቸው ጣኦታት ናቸው:: ከብርሃን ወደ ጨለማ ይመሯቸዋል:: እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِى حَآجَّ إِبْرَٰهِـۧمَ فِى رَبِّهِۦٓ أَنْ ءَاتَىٰهُ ٱللَّهُ ٱلْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَٰهِـۧمُ رَبِّىَ ٱلَّذِى يُحْىِۦ وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا۠ أُحْىِۦ وَأُمِيتُ قَالَ إِبْرَٰهِـۧمُ فَإِنَّ ٱللَّهَ يَأْتِى بِٱلشَّمْسِ مِنَ ٱلْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ ٱلْمَغْرِبِ فَبُهِتَ ٱلَّذِى كَفَرَ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy258. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን አላህ ንግስናን ስለ ሰጠውና በጌታው ጉዳይ በኢብራሂም ላይ ክርክር ስለ ከፈተው ሰው (ታሪክ) መረጃ አላየህምን? ኢብራሂም፡-‹‹ጌታዬ ያ የፈለገውን ሕያው የሚያደርግና የፈለገውን የሚገድል ነው›› ሲለው «እኔም የፈለኩትን ህያው አደርጋለሁ፤ የፈለኩትን እገድላለሁ» አለ:: ኢብራሂምም፡- «አላህ ጸሐይን በምስራቅ በኩል ያወጣል:: እስኪ አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው:: ያም የካደ ሰው ዋለለ (መልስ አጣ):: አላህ ግፈኛ ሕዝቦችን ሁሉ አይመራምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوْ كَٱلَّذِى مَرَّ عَلَىٰ قَرْيَةٍ وَهِىَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا قَالَ أَنَّىٰ يُحْىِۦ هَٰذِهِ ٱللَّهُ بَعْدَ مَوْتِهَا فَأَمَاتَهُ ٱللَّهُ مِا۟ئَةَ عَامٍ ثُمَّ بَعَثَهُۥ قَالَ كَمْ لَبِثْتَ قَالَ لَبِثْتُ يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ قَالَ بَل لَّبِثْتَ مِا۟ئَةَ عَامٍ فَٱنظُرْ إِلَىٰ طَعَامِكَ وَشَرَابِكَ لَمْ يَتَسَنَّهْ وَٱنظُرْ إِلَىٰ حِمَارِكَ وَلِنَجْعَلَكَ ءَايَةً لِّلنَّاسِ وَٱنظُرْ إِلَى ٱلْعِظَامِ كَيْفَ نُنشِزُهَا ثُمَّ نَكْسُوهَا لَحْمًا فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُۥ قَالَ أَعْلَمُ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy259. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይም ያንን ሙሉ በሙሉ በፈራረሰች ከተማ ያለፈውን ሰው ተሞክሮ አላገናዘብክምን? ‹‹ይህችን ከተማ ከሞተች በኃላ አላህ እንዴት ሕያው ያደርጋታል? አለ:: ከዚያ አላህ ገደለውና መቶ ዓመትን አቆየው:: ከዚያ አስነሳው «ምን ያህል ቆየህ?» አለው:: «አንድ ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆይቻለሁ» አለ:: «ይልቁንም መቶ ዓመት ነው የቆየኸው:: ወደ ምግብህና ወደ መጠጥህም ተመልከት:: አንዱም አልተለወጠም:: ወደ አህያህም ተመልከት:: ለሰው ልጅም ተዐምር ልናደርግህ ዘንድ ይህንን ሰራን፤ ወደ አጽሞቿም እንዴት እንደምናስነሳት ከዚያ ስጋን እንዴት እንደምናለብሳት ተመልከት።» አለው:: ለእርሱም ማስረጃ በገለጸለት ጊዜ ‹‹አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አውቃለሁ›› አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قَالَ إِبْرَٰهِـۧمُ رَبِّ أَرِنِى كَيْفَ تُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ قَالَ أَوَلَمْ تُؤْمِن قَالَ بَلَىٰ وَلَٰكِن لِّيَطْمَئِنَّ قَلْبِى قَالَ فَخُذْ أَرْبَعَةً مِّنَ ٱلطَّيْرِ فَصُرْهُنَّ إِلَيْكَ ثُمَّ ٱجْعَلْ عَلَىٰ كُلِّ جَبَلٍ مِّنْهُنَّ جُزْءًا ثُمَّ ٱدْعُهُنَّ يَأْتِينَكَ سَعْيًا وَٱعْلَمْ أَنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy260. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ እስቲ አሳየኝ» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውስ:: አላህ፡- «አላመንክምን?» አለው:: ኢብራሂምም «በፍጹም (አይደለም) አምኛለሁ:: ግን ልቤ ሙሉ በሙሉ እንዲረጋጋ ነው።» አለው:: አላህም፡- «አራት ወፎችን ያዝና ወደ አንተ ሰብስባቸው:: ከዚያ ቆራርጣቸው:: ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከእነርሱ ቁራጭ ቁራጭ አካላቸውን አስቀምጥ:: ከዚያም ጥራቸው በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ:: አላህ አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቅ።» አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّثَلُ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَٰلَهُمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ كَمَثَلِ حَبَّةٍ أَنۢبَتَتْ سَبْعَ سَنَابِلَ فِى كُلِّ سُنۢبُلَةٍ مِّا۟ئَةُ حَبَّةٍ وَٱللَّهُ يُضَٰعِفُ لِمَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy261. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች ልግስና ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ መቶ ቅንጣት ያለባቸውን ሰባት ዘለላዎች እንዳበቀለች አንዲት ፍሬ ምሳሌ ነው:: አላህ ለሚሻው ሁሉ አባዝቶ ይለግሳል:: አላህ ችሮታው ሰፊና አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَٰلَهُمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ثُمَّ لَا يُتْبِعُونَ مَآ أَنفَقُوا۟ مَنًّا وَلَآ أَذًى لَّهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy262. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ከዚያ በሰጡት ነገር መመፃደቅና ማስከፋት የማያስከትሉ ሁሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አለላቸው:: በእነርሱም ላይ ስጋትም የለባቸዉም። አይተክዙምም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَوْلٌ مَّعْرُوفٌ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌ مِّن صَدَقَةٍ يَتْبَعُهَآ أَذًى وَٱللَّهُ غَنِىٌّ حَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy263. መልካም ንግግርና ይቅር ባይነት ብቻ ማስከፋት ከሚከተለው ምጽዋት በላጭ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂና ታጋሽ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تُبْطِلُوا۟ صَدَقَٰتِكُم بِٱلْمَنِّ وَٱلْأَذَىٰ كَٱلَّذِى يُنفِقُ مَالَهُۥ رِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ صَفْوَانٍ عَلَيْهِ تُرَابٌ فَأَصَابَهُۥ وَابِلٌ فَتَرَكَهُۥ صَلْدًا لَّا يَقْدِرُونَ عَلَىٰ شَىْءٍ مِّمَّا كَسَبُوا۟ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy264. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ገንዘብን ለሰዎች ለማሳየት ሲል እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻው ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመፃደቅና ተረጂውን በማስከፋት አታበላሹ:: የዚህ አይነቱም ድርጊት ምሳሌው በላዩ ላይ አፈር እንዳረፈበት ለስላሳ ድንጋይ ሲሆን እሱም ሀይለኛ ዝናብ አግኝቶት እንደተራቆተ ብጤ ነው:: እነኝህ አይነት ሰዎች ከሰሩት ነገር በምኑም ሊጠቀሙ አይችሉም:: አላህ ከሓዲያን ሕዝቦችን በፍጹም ወደ ቀናው መንገድ አይመራምና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَثَلُ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَٰلَهُمُ ٱبْتِغَآءَ مَرْضَاتِ ٱللَّهِ وَتَثْبِيتًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ كَمَثَلِ جَنَّةٍۭ بِرَبْوَةٍ أَصَابَهَا وَابِلٌ فَـَٔاتَتْ أُكُلَهَا ضِعْفَيْنِ فَإِن لَّمْ يُصِبْهَا وَابِلٌ فَطَلٌّ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy265. የእነዚያ የአላህን ውዴታ ለመፈለግና ከነፍሶቻቸው እምነትን ለማረጋገጥ ብለው ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱት ምሳሌያቸው በተስተካከለች ከፍተኛ ቦታ ላይ እንዳለች አትክልት ሲሆን ይህች አትክልት ከፍተኛ ዝናብ አግኝታ እጥፍ ድርብ ምርት እንደሰጠች ከፍተኛ ዝናብ ባታገኝ እንኳን ካፊያ ብቻ እንደሚበቃት የአትክልት አይነት ይመስላል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَيَوَدُّ أَحَدُكُمْ أَن تَكُونَ لَهُۥ جَنَّةٌ مِّن نَّخِيلٍ وَأَعْنَابٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ لَهُۥ فِيهَا مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ وَأَصَابَهُ ٱلْكِبَرُ وَلَهُۥ ذُرِّيَّةٌ ضُعَفَآءُ فَأَصَابَهَآ إِعْصَارٌ فِيهِ نَارٌ فَٱحْتَرَقَتْ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy266. ከናንተ አንዳችሁ ሁሉን ዓይነት ምርት የምትሰጥ ከስሯ ወንዞች የምፈሱባት የዘንባባዎችና የወይኖች የአትክልት ቦታ ልትኖረው እርጅናም ሊነካውና በእነርሱም ደካሞች ረዳት የለሽ ህፃናት ያሉት ሲሆኑ በውስጡ እሳት ያለበት ውርጭ ምርቱ ላይ አደጋ ሊያደርስበት እና ልትቃጠልበት ይወዳልን? ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ለእናንተ ያብራራል:: ልታስተነትኑ ይከጀላልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَنفِقُوا۟ مِن طَيِّبَٰتِ مَا كَسَبْتُمْ وَمِمَّآ أَخْرَجْنَا لَكُم مِّنَ ٱلْأَرْضِ وَلَا تَيَمَّمُوا۟ ٱلْخَبِيثَ مِنْهُ تُنفِقُونَ وَلَسْتُم بِـَٔاخِذِيهِ إِلَّآ أَن تُغْمِضُوا۟ فِيهِ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ غَنِىٌّ حَمِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy267. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ካፈራችሁትና ከዚያ ለእናንተ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙ ለግሱ:: መጥፎውንም ለመስጠት አታስቡ:: እርሱን ለራሳችሁ አይኖቻችሁን ጨፍናችሁ እንጂ የማትወስዱት ስትሆኑ ከእርሱ (ከመጥፎ) ትሰጣላችሁን? አላህ ተብቃቂና ምስጉን መሆኑን እወቁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلشَّيْطَٰنُ يَعِدُكُمُ ٱلْفَقْرَ وَيَأْمُرُكُم بِٱلْفَحْشَآءِ وَٱللَّهُ يَعِدُكُم مَّغْفِرَةً مِّنْهُ وَفَضْلًا وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy268. ሰይጣን እንዳትለግሱ በድህነት ያስፈራራችኋል:: በመጥፎም ያዛችኋል:: አላህ ከእርሱ የሆነን ምህረትና ችሮታን ሊያጎናጽፋችሁ ተስፋ ሰጥቷችኋል:: አላህ ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُؤْتِى ٱلْحِكْمَةَ مَن يَشَآءُ وَمَن يُؤْتَ ٱلْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِىَ خَيْرًا كَثِيرًا وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy269. አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል:: ጥበብንም የሚስ-ሰጥ ሰው ሁሉ ብዙ መልካም ነገርን በእርግጥ ተሰጥቷል:: የአዕምሮ ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَنفَقْتُم مِّن نَّفَقَةٍ أَوْ نَذَرْتُم مِّن نَّذْرٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُهُۥ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ
Amharic Translation - Africa Academy270. ከምጽዋት ማንኛውንም የለገሳችሁትን ወይም ከስለት የተሳላችሁትን አላህ ጠንቅቆ ያውቀዋል:: ለበዳዮች (ግፈኞች) ሁሉ ምንም አይነት ረዳቶች የሏቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِن تُبْدُوا۟ ٱلصَّدَقَٰتِ فَنِعِمَّا هِىَ وَإِن تُخْفُوهَا وَتُؤْتُوهَا ٱلْفُقَرَآءَ فَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَيُكَفِّرُ عَنكُم مِّن سَيِّـَٔاتِكُمْ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy271. ምጽዋቶችን ብትገልጹ እርሷ ምንኛ መልካም ተግባር ናት:: ብትደብቋትና ለድሆች ብትሰጧት እርሱ ለእናንተ በላጭ ነው:: ከኃጢአቶቻችሁ ከእናንተ ያብሳል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّيْسَ عَلَيْكَ هُدَىٰهُمْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَهْدِى مَن يَشَآءُ وَمَا تُنفِقُوا۟ مِنْ خَيْرٍ فَلِأَنفُسِكُمْ وَمَا تُنفِقُونَ إِلَّا ٱبْتِغَآءَ وَجْهِ ٱللَّهِ وَمَا تُنفِقُوا۟ مِنْ خَيْرٍ يُوَفَّ إِلَيْكُمْ وَأَنتُمْ لَا تُظْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy272. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ማቅናት ባንተ ላይ ግዴታ የለብህም:: አላህ ግን የሚሻውን ሰው ያቀናል:: የምትለግሱት ገንዘብ ሁሉ ምንዳው ለነፍሶቻችሁ ብቻ ነው:: የአላህን ውዴታውን በመፈለግ እንጂ ምንንም አትለግሱ:: ከገንዘብም የምትለግሱት ሁሉ ምንዳው ወደ እናንተ ይሞላል:: እናንተም ቅንጣት ያህል አትበደሉም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِلْفُقَرَآءِ ٱلَّذِينَ أُحْصِرُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ لَا يَسْتَطِيعُونَ ضَرْبًا فِى ٱلْأَرْضِ يَحْسَبُهُمُ ٱلْجَاهِلُ أَغْنِيَآءَ مِنَ ٱلتَّعَفُّفِ تَعْرِفُهُم بِسِيمَٰهُمْ لَا يَسْـَٔلُونَ ٱلنَّاسَ إِلْحَافًا وَمَا تُنفِقُوا۟ مِنْ خَيْرٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِهِۦ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy273. (ምጽዋት የምትሰጡት ዘካና ልገሳ) ለእነዚያ በአላህ መንገድ በግል ሕይወታቸው ከመንቀሳቀስ (ለታገዱት) ፋታ ላጡ ድሆች ነው:: መሬት ውስጥ መጓዝ (ልመና) አይችሉም:: ከቁጥብነታቸው የተነሳ ውስጣቸውን የማያውቅ ሰው ሁሉ ሀብታሞች ናቸው ብሎ ይገምታቸዋል:: በምልክታቸው ታውቃቸዋለህ:: ሰዎችን በችክታ አይለምኑም:: ከገንዘብም የምትለግሱትን ሁሉ አላህ ሁሉን አዋቂ ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَٰلَهُم بِٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ سِرًّا وَعَلَانِيَةً فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy274. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በሌሊትና በቀን በድብቅም ሆነ በግልጽ የሚለግሱ ሰዎች ሁሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ዋጋቸው ይስ-ሰጣቸዋል:: በእነርሱም ላይ ምንም ይደርስብናል ብለው ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም ነገር ያመልጠናል ብለው አያዝኑም፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ يَأْكُلُونَ ٱلرِّبَوٰا۟ لَا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ ٱلَّذِى يَتَخَبَّطُهُ ٱلشَّيْطَٰنُ مِنَ ٱلْمَسِّ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا ٱلْبَيْعُ مِثْلُ ٱلرِّبَوٰا۟ وَأَحَلَّ ٱللَّهُ ٱلْبَيْعَ وَحَرَّمَ ٱلرِّبَوٰا۟ فَمَن جَآءَهُۥ مَوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّهِۦ فَٱنتَهَىٰ فَلَهُۥ مَا سَلَفَ وَأَمْرُهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِ وَمَنْ عَادَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy275. እነዚያ አራጣን የሚበሉ ሁሉ ያ ሰይጣን ሰፍኖበት ራሱን የሚስት ሰው ከአውድቅቱ እንደሚነሳ አይነት ሁነው እንጂ ከመቃብራቸው አይነሱም:: ይህም የሆነው እነርሱ መሸጥ ልክ እንደ አራጣ ነው በማለታቸው ነው:: አላህ ግን መሸጥን ፈቅዷል:: አራጣን እርም አድርጓል:: ከጌታው ግሳጼ የመጣለት እና ከዚያ የተከለከለ ሰው ሁሉ ከዚህ አዋጅ በፊት ያካበተውን እንደያዘ መቆየት ይችላል:: የወደፊት እጣፈንታው ወደ አላህ ነው:: አራጣን ወደ መብላት የተመለሱ ሰዎች እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘወታሪዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَمْحَقُ ٱللَّهُ ٱلرِّبَوٰا۟ وَيُرْبِى ٱلصَّدَقَٰتِ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ كَفَّارٍ أَثِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy276. አላህ የአራጣን ገንዘብ ያከስማል (በረከቱን ያጠፋል):: መልካም ልገሳዎችን ያፋፋል:: አላህም ኃጢአተኛንና ከሓዲን ሁሉ አይወድምና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَوُا۟ ٱلزَّكَوٰةَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy277. እነዚያ ያመኑና መልካም ስራዎችንም የሰሩ፤ ሶላትን አስተካክለው የሰገዱና ዘካንም የሰጡ እነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፤ በእነርሱም ላይ ምንም ይደርስብናል ብለው ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም ነገር ያመልጠናል ብለው አያዝኑምም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَذَرُوا۟ مَا بَقِىَ مِنَ ٱلرِّبَوٰٓا۟ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy278. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ከአራጣም የቀረውን አትውሰዱ:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ (ተጠንቀቁ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَإِن لَّمْ تَفْعَلُوا۟ فَأْذَنُوا۟ بِحَرْبٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَإِن تُبْتُمْ فَلَكُمْ رُءُوسُ أَمْوَٰلِكُمْ لَا تَظْلِمُونَ وَلَا تُظْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy279. የታዘዛችሁትን ባትሰሩ ከአላህና ከመልዕክተኛ ጦርነት ታውጆባችኋል:: ከወለዳዊ ድርጊታችሁ ብትታቀቡ ግን አንጡራ ገንዘባችሁ ለእናንተው እንደተጠበቀ ነው:: ሌሎችን አትበድሉም አትበደሉምም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن كَانَ ذُو عُسْرَةٍ فَنَظِرَةٌ إِلَىٰ مَيْسَرَةٍ وَأَن تَصَدَّقُوا۟ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy280. የድህነት ባለቤት ባለዕዳ ሰው ቢኖር ገንዘብ እስኪያገኝ ድረስ ማቆየት ነው:: (የእፎይታ ጊዜ ይሰጠው) ስጡት:: እዳውን በበጎ አድራጊነት ሙሉ በሙሉ ብትሰርዙለትም ለእናንተ በላጭ ነው። የምታውቁ ብትሆኑ (ትሰሩታላችሁ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱتَّقُوا۟ يَوْمًا تُرْجَعُونَ فِيهِ إِلَى ٱللَّهِ ثُمَّ تُوَفَّىٰ كُلُّ نَفْسٍ مَّا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy281. ያን ወደ አላህ የምትመለሱበትን ቀን ፍሩ:: ሁሉም ነፍስ ያኔ ከሰራቸው አኳያ ዋጋዋን ታገኛለች:: በዚያ ዕለት (በሱ ዉስጥ) ተበዳይ ወገኖች ፈጽሞ አይኖሩም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا تَدَايَنتُم بِدَيْنٍ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى فَٱكْتُبُوهُ وَلْيَكْتُب بَّيْنَكُمْ كَاتِبٌۢ بِٱلْعَدْلِ وَلَا يَأْبَ كَاتِبٌ أَن يَكْتُبَ كَمَا عَلَّمَهُ ٱللَّهُ فَلْيَكْتُبْ وَلْيُمْلِلِ ٱلَّذِى عَلَيْهِ ٱلْحَقُّ وَلْيَتَّقِ ٱللَّهَ رَبَّهُۥ وَلَا يَبْخَسْ مِنْهُ شَيْـًٔا فَإِن كَانَ ٱلَّذِى عَلَيْهِ ٱلْحَقُّ سَفِيهًا أَوْ ضَعِيفًا أَوْ لَا يَسْتَطِيعُ أَن يُمِلَّ هُوَ فَلْيُمْلِلْ وَلِيُّهُۥ بِٱلْعَدْلِ وَٱسْتَشْهِدُوا۟ شَهِيدَيْنِ مِن رِّجَالِكُمْ فَإِن لَّمْ يَكُونَا رَجُلَيْنِ فَرَجُلٌ وَٱمْرَأَتَانِ مِمَّن تَرْضَوْنَ مِنَ ٱلشُّهَدَآءِ أَن تَضِلَّ إِحْدَىٰهُمَا فَتُذَكِّرَ إِحْدَىٰهُمَا ٱلْأُخْرَىٰ وَلَا يَأْبَ ٱلشُّهَدَآءُ إِذَا مَا دُعُوا۟ وَلَا تَسْـَٔمُوٓا۟ أَن تَكْتُبُوهُ صَغِيرًا أَوْ كَبِيرًا إِلَىٰٓ أَجَلِهِۦ ذَٰلِكُمْ أَقْسَطُ عِندَ ٱللَّهِ وَأَقْوَمُ لِلشَّهَٰدَةِ وَأَدْنَىٰٓ أَلَّا تَرْتَابُوٓا۟ إِلَّآ أَن تَكُونَ تِجَٰرَةً حَاضِرَةً تُدِيرُونَهَا بَيْنَكُمْ فَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ أَلَّا تَكْتُبُوهَا وَأَشْهِدُوٓا۟ إِذَا تَبَايَعْتُمْ وَلَا يُضَآرَّ كَاتِبٌ وَلَا شَهِيدٌ وَإِن تَفْعَلُوا۟ فَإِنَّهُۥ فُسُوقٌۢ بِكُمْ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَيُعَلِّمُكُمُ ٱللَّهُ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy282. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ በእዳ በተዋዋላችሁ ጊዜ ፃፉት:: ጸሐፊዉም በመካከላችሁ በትክከል ይፃፍ:: ጸሐፊም አላህ ልክ እንዳሳወቀው መፃፍን ለመፃፍ እንቢ አይበል:: ይፃፍም:: ያም በእርሱ ላይ እዳ ያለበት ሰው በቃሉ ያለበትን እዳ ያስጽፍ:: ጌታውን አላህን ይፍራ:: ካለበት እዳ ምንም አያጉድል:: ያም በእርሱ ላይ እዳው ያለበት የአእምሮም ሆነ የአካል መታወክ ካለበት ወይም በቃሉ ማስፃፍን የማይችል ከሆነ ወኪሉ በትክክል ያስጽፍለት:: ከወንዶቻችሁ ሁለትን ምስክሮች አስመስክሩ:: ሁለትም ወንዶች በስፍራው ካልተገኙ ግን ለምስክርነት በቂ የሆነ አንድ ወንድና አንደኛዋ ስትረሳ አንደኛይቱ ሌላዋን ታስታውሳት ዘንድ ሁለት ሴቶች ይመስክሩ:: ምስክሮችም በተጠሩ ጌዜ ከመመስከር እንቢ አይበሉ:: (እዳው) ትንሽ ወይም ትልቅ ቢሆንም እስከጊዜው ድረስ ከመፃፍ አትሰልቹ:: ይህ አላህ ዘንድ በጣም ትክክል ለምስክርነቱም ተዐማኒነት የሚያጎናጽፍ ጥርጣሬንም ለማስወገድ በጣም የተመቸ አሰራር ነው:: በመካከላችሁ እጅ በእጅ በምትለዋወጡት ንግድ ላይ ግን ባትጽፏት በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: በተሻሻጣቸሁ ጊዜ አስመስክሩ:: ጸሐፊም ሆነ ምስክር ባለጉዳዩ ጉዳት ሊያደርስባቸው አይገባም:: ይህንን ብትሰሩ በእናንተ በኩል የሚመጣ አመጽ ነው:: አላህን ፍሩ:: አላህ ያሳውቃችኋል:: አላህ ሁሉንም ነገር አዋቂ ነውና፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن كُنتُمْ عَلَىٰ سَفَرٍ وَلَمْ تَجِدُوا۟ كَاتِبًا فَرِهَٰنٌ مَّقْبُوضَةٌ فَإِنْ أَمِنَ بَعْضُكُم بَعْضًا فَلْيُؤَدِّ ٱلَّذِى ٱؤْتُمِنَ أَمَٰنَتَهُۥ وَلْيَتَّقِ ٱللَّهَ رَبَّهُۥ وَلَا تَكْتُمُوا۟ ٱلشَّهَٰدَةَ وَمَن يَكْتُمْهَا فَإِنَّهُۥٓ ءَاثِمٌ قَلْبُهُۥ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy283. በጉዞ ላይ ብትሆኑና ጸሐፊ ባታገኙ በእጅ የተጨበጡ መተማመኛዎችን ያዙ:: ከፊላችሁ ከፊሉን ቢያምን ያ የታመነው ሰው አደራውን በትክክል ያድርስ:: አላህንም ጌታውን ይፍራ:: ምስክርነትንም አትደብቁ። ምስክርነትን የሚደብቃት ልበ ኃጢአተኛ ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَإِن تُبْدُوا۟ مَا فِىٓ أَنفُسِكُمْ أَوْ تُخْفُوهُ يُحَاسِبْكُم بِهِ ٱللَّهُ فَيَغْفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy284. በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለ ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ብትገልጹት ወይም ብትደብቁት አላህ በእርሱ ይቆጣጠራችኋል የሚሻውን ሰው ይምራል:: የሚሻውንም ሰው ይቀጣል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና:: ይተሳሰባችኋል፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِۦ وَقَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy285. መልዕክተኛው (ሙሐመድ) ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደለት (ቁርኣን) አምኗል:: አማኞችም እንደዚሁ አመኑ:: ሁሉም በአላህ፣ በመልዕክቱ፣ በመጽሐፉትና በመልዕክተኞቹ «ከእነርሱ በአንዱም መካከል አንለይም (አንክድም)» የሚሉ ሲሆኑ አመኑ:: «የአላህን ትዕዛዛትንም ሰማን ታዘዝንም። ጌታችን ሆይ! ምህረትህን እንሻለን :: የሁሉም መመለሻ ወደ አንተው ብቻ ነው። አሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا ٱكْتَسَبَتْ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَآ إِن نَّسِينَآ أَوْ أَخْطَأْنَا رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَآ إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِنَا رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِۦ وَٱعْفُ عَنَّا وَٱغْفِرْ لَنَا وَٱرْحَمْنَآ أَنتَ مَوْلَىٰنَا فَٱنصُرْنَا عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy286. አላህ የትኛዋንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም:: ነፍስ ሁሉ ለሰራችው መልካም ስራ ሁሉ ተገቢው ምንዳ አላት:: በእርሷም ላይ ባፈራችው (ኃጢአት) ተገቢው ቅጣት አለባት:: (ሙስሊሞች) «ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንሳሳት (አትቅጣን):: ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ህዝቦች ላይ እንደጫንከው ሁሉ በእኛ ላይ አትጫንብን:: ጌታችን ሆይ! ለእኛ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን:: ለእኛም ይቅርታ አድርግልን:: ለእኛም ምህረትን አድርግልን:: እዘንልንም:: ረዳታችን አንተ ብቻ ነህና:: በከሓዲ ሕዝቦች ላይም ድልን አጎናጽፈን።» (በሉ።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→