تِلْكَ ٱلرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ مِّنْهُم مَّن كَلَّمَ ٱللَّهُ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَٰتٍ وَءَاتَيْنَا عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ ٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَيَّدْنَٰهُ بِرُوحِ ٱلْقُدُسِ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ مَا ٱقْتَتَلَ ٱلَّذِينَ مِنۢ بَعْدِهِم مِّنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ وَلَٰكِنِ ٱخْتَلَفُوا۟ فَمِنْهُم مَّنْ ءَامَنَ وَمِنْهُم مَّن كَفَرَ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ مَا ٱقْتَتَلُوا۟ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَفْعَلُ مَا يُرِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy253. እነዚያን መልዕክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን:: ከእነርሱ መካከልም አላህ ያነጋገረው አለ:: ከፊሎቻቸውንም በደረጃ ከሌሎች ከፍ አድርጓል:: የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተዐምራት ሰጠነው:: በቅዱስ መንፈስም (በመላኩ ጂብሪል) አበረታነው:: አላህ በፈለገ ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ በኋላ የነበሩት መረጃው ከመጣላቸው በኋላ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር:: ግን ተለያዩ:: በመሆኑም ከመሀከላቸው ትክክለኛ አማኝ ክፍል አለ:: ከመሀከላቸዉም ከሃዲ አለ:: አላህ በፈለገ ኖሮ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር:: አላህ ግን የሚሻውን ሁሉ ይሰራል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚህን መልክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፡፡ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አልለ፡፡ ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡ አላህ በሻ ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ከመልክተኞቹ) በኋላ የነበሩት ግልጽ ታምራቶች ከመጡላቸው በኋላ ባልተጋደሉ ነበር፡፡ ግን ተለያዩ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ያመነ ሰው አልለ፡፡ ከነርሱም ውስጥ የካደ ሰው አልለ፡፡ አላህ በሻ ኖሮ ባልተዋጉ (ባልተለያዩ) ነበር፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ይሠራል፡፡