caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 34

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:34

وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَٰٓئِكَةِ ٱسْجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوٓا۟ إِلَّآ إِبْلِيسَ أَبَىٰ وَٱسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትን «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ከዲያብሎስ በቀር መላዕክት ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ። እርሱማ እምቢ አለ። ኮራም። ከከሓዲያንም ሆነ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ (ሁሉም) ወዲያውኑ ሰገዱ፤ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር እምቢ አለ፤ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70