caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 220

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:220

فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْيَتَٰمَىٰ قُلْ إِصْلَاحٌ لَّهُمْ خَيْرٌ وَإِن تُخَالِطُوهُمْ فَإِخْوَٰنُكُمْ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ ٱلْمُفْسِدَ مِنَ ٱلْمُصْلِحِ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَأَعْنَتَكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy220. በዱኒያም በአኼራም ታስተነትኑ ዘንድ ይገልፅላችኃል። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለየቲሞችም ይጠይቁሀል:: «የእነርሱን ሁኔታ ማሻሻል በላጭ ነው:: የእነርሱ ጉዳይ ከናንተ ጋር ብትቀላቅሉም ወንድሞቻችሁ ናቸው:: አላህም አጥፊውን ከአልሚው ለይቶ ያውቃል:: አላህም በፈለገ ኖሮ መፈናፈኛ ያሳጣችሁ (ባስቸገራችሁ) ነበር:: አላህ በሁሉም ነገር አሸናፊና ጥበበኛ ነው በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበቅርቢቱ ዓለምና በመጨረሻይቱ ታስተነትኑ ዘንድ (ይገለጽላችኋል)፡፡ ከየቲሞችም ይጠይቁሃል፡፡ «ለእነርሱ (ገንዘባቸውን በማራባት) ማሳመር በላጭ ነው፡፡ ብትቀላቀሏቸውም ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡ አላህም የሚያጠፋውን ከሚያበጀው (ለይቶ) ያውቃል፡፡ አላህም በሻ ኖሮ ባስቸገራችሁ ነበር፤ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70