فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًا قَلِيلًا فَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy79. እነዚያ መጽሐፍን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያ በእርሱ ጥቂት ዋጋን ሊገዙበት ብለው: «ይህ ከአላህ ዘንድ የወረደ ነው» ለሚሉ ሁሉ ወዮላቸው። እነርሱ ከዚያ እጆቻቸው ከፃፉት ወንጀል ወዮላቸው:: እነርሱ ከዚያ ከሚሰሩት ኃጢአት ወዮላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡