caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 203

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:203

وَٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ فِىٓ أَيَّامٍ مَّعْدُودَٰتٍ فَمَن تَعَجَّلَ فِى يَوْمَيْنِ فَلَآ إِثْمَ عَلَيْهِ وَمَن تَأَخَّرَ فَلَآ إِثْمَ عَلَيْهِ لِمَنِ ٱتَّقَىٰ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّكُمْ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy203. (ሙስሊሞች ሆይ!) በእነዚያ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ አላህን አውሱ:: በሁለት ቀናት ውስጥ ለመሄድ የተቻኮለ ሰው በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም:: የቆየም ሰው ኃጢአት የለበትም:: ይህም (ምህረት) አላህን ለፈራ ሰው ሁሉ ነው:: አላህንም ፍሩ:: እናንተ ወደ እርሱ የምትሰበሰቡ መሆናችሁንም እወቁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበተቆጠሩ ቀኖችም ውስጥ (በሚና ጠጠሮችን ስትወረውሩ) አላህን አውሱ፡፡ በሁለት ቀኖችም ውስጥ (በመኼድ) የተቻኮለ ሰው በርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፡፡ የቆየም ሰው በርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፡፡ (ይህም) አላህን ለፈራ ሰው ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ እናንተ ወደርሱ የምትሰበሰቡ መኾናችሁንም ዕወቁ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70