caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 185

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:185

شَهْرُ رَمَضَانَ ٱلَّذِىٓ أُنزِلَ فِيهِ ٱلْقُرْءَانُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَٰتٍ مِّنَ ٱلْهُدَىٰ وَٱلْفُرْقَانِ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ ٱلشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ يُرِيدُ ٱللَّهُ بِكُمُ ٱلْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ ٱلْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا۟ ٱلْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا۟ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَىٰكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy185. (ያ እንድትጾሙት የተደነገገላችሁ ወር) በእርሱ ዉስጥ ለሰዎች መሪ ሐቅን መንገድና እውነትን ከዉሸት የሚለየው ገላጭ ቁርአን የተወረደበት የረመዷን ወር ነው:: ከናንተ መካከል ወሩን ያገኘ ሁሉ ይጹመው:: በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ካፈጠረ ከሌሎች ቀናት ባልፆማቸው ቀናት ቁጥሮች ልክ መፆም አለበት:: አላህ ሁልጊዜም ለእናንተ ገሩን ነገር ይሻል እንጂ በእናንተ ላይ ጫናን መፍጠርን አይሻምና ነው። ለፆም የተወሰኑትን ቀናት ልትሞሉና አላህን ቅንኑ መንገድ ስለመራችሁ ልታከብሩትና ልታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገገላችሁ)
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) (መጾም) አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70