وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ ءَامِنُوا۟ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُوا۟ نُؤْمِنُ بِمَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا وَيَكْفُرُونَ بِمَا وَرَآءَهُۥ وَهُوَ ٱلْحَقُّ مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَهُمْ قُلْ فَلِمَ تَقْتُلُونَ أَنۢبِيَآءَ ٱللَّهِ مِن قَبْلُ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy91. «አላህ ባወረደው እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በእኛ ላይ በተወረደው መጽሐፍ ብቻ እናምናለን» ይላሉ:: ከእርሱ ኋላ የመጣው ቁርኣን ምንም እንኳን ከእነርሱ ጋር ላለው መጽሐፍ አረጋጋጭና ትክክለኛ የሆነ ቢሆንም ይክዳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነብያትን ለምን ገደላችሁ?» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህም ባወረደው (ሁሉ) ለእነርሱ «እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በኛ ላይ በተወረደው (መጽሐፍ ብቻ) እናምናለን» ይላሉ፡፡ ከርሱ ኋላ ባለው (ቁርአን) እርሱ ከነሱ ጋር ላለው (መጽሐፍ) አረጋጋጭ እውተኛ ሲኾን ይክዳሉ፡፡ «አማኞች ከኾናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነቢያት ለምን ገደላችሁ?» በላቸው፡፡