لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا ٱكْتَسَبَتْ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَآ إِن نَّسِينَآ أَوْ أَخْطَأْنَا رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَآ إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِنَا رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِۦ وَٱعْفُ عَنَّا وَٱغْفِرْ لَنَا وَٱرْحَمْنَآ أَنتَ مَوْلَىٰنَا فَٱنصُرْنَا عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy286. አላህ የትኛዋንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም:: ነፍስ ሁሉ ለሰራችው መልካም ስራ ሁሉ ተገቢው ምንዳ አላት:: በእርሷም ላይ ባፈራችው (ኃጢአት) ተገቢው ቅጣት አለባት:: (ሙስሊሞች) «ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንሳሳት (አትቅጣን):: ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ህዝቦች ላይ እንደጫንከው ሁሉ በእኛ ላይ አትጫንብን:: ጌታችን ሆይ! ለእኛ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን:: ለእኛም ይቅርታ አድርግልን:: ለእኛም ምህረትን አድርግልን:: እዘንልንም:: ረዳታችን አንተ ብቻ ነህና:: በከሓዲ ሕዝቦች ላይም ድልን አጎናጽፈን።» (በሉ።)
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለርስዋ የሠራችው አላት፡፡ በርስዋም ላይ ያፈራችው (ኀጢአት) አለባት፡፡ (በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፡፡ ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በእኛ ላይ አትጫንብን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለኛም በርሱ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን፡፡ ከእኛም ይቅርታ አድርግ ለእኛም ምሕረት አድርግ፡፡ እዘንልንም፤ ዋቢያችን አንተ ነህና፡፡ በከሓዲዎች ሕዝቦች ላይም እርዳን፡፡