caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 133

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:133

أَمْ كُنتُمْ شُهَدَآءَ إِذْ حَضَرَ يَعْقُوبَ ٱلْمَوْتُ إِذْ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعْبُدُونَ مِنۢ بَعْدِى قَالُوا۟ نَعْبُدُ إِلَٰهَكَ وَإِلَٰهَ ءَابَآئِكَ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ إِلَٰهًا وَٰحِدًا وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy133. የዕቆብም ለጣዕረ ሞት በተዳረገበት ጊዜና ለልጆቹ «ከእኔ በኋላ ምንን ትገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ ነበራችሁን? እነርሱም «አንድ የሆነውን አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን፤ የኢስማዒልንና የኢስሃቅንም አምላክ እንገዛለን:: እኛም ለእርሱ ፍጹም ታዛዦች ሆነን እናመልከዋለን።» አሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqያዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ ከኔ በኋላ ማንን ትገዛላችሁ ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? (እነርሱም) አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢስማዒልንና የኢስሐቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለርሱ ፍፁም ታዛዦች ኾነን እናመልካለን አሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70