وَلَمَّا جَآءَهُمْ رَسُولٌ مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ مُصَدِّقٌ لِّمَا مَعَهُمْ نَبَذَ فَرِيقٌ مِّنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ كِتَٰبَ ٱللَّهِ وَرَآءَ ظُهُورِهِمْ كَأَنَّهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy101. ከእነርሱ ጋር ያለን መጽሐፍ የሚያረጋግጥ መልዕክተኛ ከአላህ ዘንድ ተልኮ በመጣ ጊዜ ከእነዚያው መጽሐፍት ከተሰጣቸው ወገኖች ከፊሎቹ ምንም እንደማያውቁ ሆነው የአላህን መጽሐፍ ወደ ኋላቸው ወረወሩት (ጣሉት)።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነርሱ ጋርም ላለው (መጽሐፍ) አረጋጋጭ የኾነ መልክተኛ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ ከነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ከፊሉ እነርሱ እንደማያውቁ ኾነው የአላህን መጽሐፍ ከጀርባዎቻቸው ኋላ ጣሉ፡፡