caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 191

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:191

وَٱقْتُلُوهُمْ حَيْثُ ثَقِفْتُمُوهُمْ وَأَخْرِجُوهُم مِّنْ حَيْثُ أَخْرَجُوكُمْ وَٱلْفِتْنَةُ أَشَدُّ مِنَ ٱلْقَتْلِ وَلَا تُقَٰتِلُوهُمْ عِندَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ حَتَّىٰ يُقَٰتِلُوكُمْ فِيهِ فَإِن قَٰتَلُوكُمْ فَٱقْتُلُوهُمْ كَذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy191. ባገኛችኃቸዉም ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ካስወጧችሁም ስፍራ አስወጧቸው:: ፈተና (ሁክት) ከመግደል የከፋ ነውና:: በተከበረው መስጊድም ዘንድ በእርሱ ውስጥ እስከሚጋደሏችሁ ድረስ በእርሱ ውስጥ አትጋደሏቸው:: ከተጋደሏችሁ ግን ግደሏቸው:: የከሓዲያን ቅጣት ልክ እንደዚህ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqባገኛችኋቸውም ስፍራ ሁሉ ግደሉዋቸው፡፡ ከአወጧችሁም ስፍራ አውጧቸው፡፡ መከራም ከመግደል ይበልጥ የበረታች ናት፡፡ በተከበረው መስጊድም ዘንድ በርሱ ውስጥ እስከሚጋደሉዋችሁ ድረስ አትጋደሉዋቸው፡፡ ቢጋደሉዋችሁም ግደሉዋቸው፤ የከሓዲዎች ቅጣት እንደዚህ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70