وَإِذِ ٱبْتَلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ رَبُّهُۥ بِكَلِمَٰتٍ فَأَتَمَّهُنَّ قَالَ إِنِّى جَاعِلُكَ لِلنَّاسِ إِمَامًا قَالَ وَمِن ذُرِّيَّتِى قَالَ لَا يَنَالُ عَهْدِى ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂምን ጌታው በትዕዛዛት በፈተነውና በፈጸማቸውም ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ):: «እኔ የሰው ዘር መሪ አድርጌሀላሁ።» አለው:: ኢብራሂምም «ከዘሮቼም አድርግ?» ሲል ጠየቀ:: አላህም «ኢብራሂም ሆይ! ቃል ኪዳኔ ለግፈኛ አጥፊዎች ተፈፃሚ አይሆንም እንጂ።» አለው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqኢብራሂምንም ጌታው በቃላት (በሕግጋት) በፈተነውና በፈጸማቸው ጊዜ (አስታውስ)፤ «እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ» አለው፡፡ «ከዘሮቼም (አድርግ)» አለ፡፡ ቃል ኪዳኔ በዳዮቹን አያገኝም አለው፡፡