وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ وَلَوْ يَرَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓا۟ إِذْ يَرَوْنَ ٱلْعَذَابَ أَنَّ ٱلْقُوَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا وَأَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعَذَابِ
Amharic Translation - Africa Academy165. ከሰዎች መካከል ከአላህ ሌላ ባላንጣዎችን/ ጣዖታትን/ አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ሆነው የሚይዙ አሉ። እነዚያ ያመኑት ግን አላህን ከምንም በላይ ይወዳሉ:: እነዚያም የበደሉት ሰዎች ቅጣትን በትንሳኤ ቀን ባዩ ጊዜ ሀይል ሁሉ ለአላህ ብቻ መሆኑንና አላህም ቅጣቱ ብርቱ እንደሆነ ይገነዘባሉ:: በዚህች ዐለም ቢያውቁ ኖሮ (ባላንጣዎችን በመያዛቸው በተጸጸቱ ነበር)።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡ እነዚያም የበደሉት ሰዎች ቅጣትን (በትንሣኤ ቀን) ባዩ ጊዜ ኀይል ሁሉ ለአላህ ብቻ መኾኑንና አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን (በአዱኛ ዓለም) ቢያውቁ ኖሮ (ባላንጣዎችን በመያዛቸው በተጸጸቱ ነበር)፡፡