وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ ٱلْيَهُودُ وَلَا ٱلنَّصَٰرَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ قُلْ إِنَّ هُدَى ٱللَّهِ هُوَ ٱلْهُدَىٰ وَلَئِنِ ٱتَّبَعْتَ أَهْوَآءَهُم بَعْدَ ٱلَّذِى جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ مَا لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّ وَلَا نَصِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy120. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድም ሆኑ ክርስቲያኖች የየራሳቸውን ሀይማኖትን እስከምትከተል ድረስ ፈጽሞ አይደሰቱብህም:: «ትክክለኛው መንገድ በእርግጥ የአላህ አመራር ነው።» በላቸው። ትክክለኛው እውቀት ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል አንተን ከአላህ የሚከላከልልህ ወዳጅም ሆነ ረዳት የለህም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡