وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ قَدْ بَعَثَ لَكُمْ طَالُوتَ مَلِكًا قَالُوٓا۟ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُ ٱلْمُلْكُ عَلَيْنَا وَنَحْنُ أَحَقُّ بِٱلْمُلْكِ مِنْهُ وَلَمْ يُؤْتَ سَعَةً مِّنَ ٱلْمَالِ قَالَ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُۥ بَسْطَةً فِى ٱلْعِلْمِ وَٱلْجِسْمِ وَٱللَّهُ يُؤْتِى مُلْكَهُۥ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy247. ነብያቸው ‹‹አላህ ጧሉትን ንጉስ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ›› አላቸው:: እነርሱም፡- «ሰፊ ሀብትም ያልተሰጠ እኛም ከእርሱ ይልቅ ለንግስና ተገቢዎች ስንሆን እርሱ በእኛ ላይ እንዴት ይነግሣል?» አሉ:: ነብያቸዉም፡- «አላህ በእናንተ ላይ መረጠው እውቀትና የሰውነት ጥንካሬም አጎናጽፎታል:: አላህ ንግስናውን ለሚሻለት ሰው ይሰጣል:: አላህ ችሮታው ሰፊና አዋቂ ነው።» አላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «አላህ ጧሉትን (ሳኦልን) ንጉሥ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ» አላቸው፡፡ (እነርሱም)፡- «እኛ ከእርሱ ይልቅ በንግሥና ተገቢዎች ስንኾን ከሀብትም ስፋትን ያልተሰጠ ሲኾን ለእርሱ በኛ ላይ እንዴት ንግሥና ይኖረዋል?» አሉ፡፡ (ነቢያቸውም)፡-«አላህ በእናንተ ላይ መረጠው፡፡ በዕውቀትና በአካልም ስፋትን ጨመረለት፡፡ አላህም ንግሥናውን ለሚሻው ሰው ይሰጣል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» አላቸው፡፡