وَلَتَجِدَنَّهُمْ أَحْرَصَ ٱلنَّاسِ عَلَىٰ حَيَوٰةٍ وَمِنَ ٱلَّذِينَ أَشْرَكُوا۟ يَوَدُّ أَحَدُهُمْ لَوْ يُعَمَّرُ أَلْفَ سَنَةٍ وَمَا هُوَ بِمُزَحْزِحِهِۦ مِنَ ٱلْعَذَابِ أَن يُعَمَّرَ وَٱللَّهُ بَصِيرٌۢ بِمَا يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድ ሁሉ እና ከእነዚያ ጣኦትን በአላህ ካጋሩት ይበልጥ በሕይወት ላይ የሚጓጉ ሆነው በእርግጥ ታገኛቸዋለህ:: ለአንዳቸውም አንድ ሺህ ዓመት ዕድሜ ቢሰጥ ይወዳል:: እርሱም (ዕድሜ መሰጠቱ) ከቅጣት የሚያድነው አይደለም:: አላህም የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከሰዎችም ሁሉ ከእነዚያም (ጣዖትን) ከአጋሩት ይበልጥ በሕይወት ላይ የሚጓጉ ኾነው በእርግጥ ታገኛቸዋለህ፡፡ አንዳቸው ሺሕ ዓመት ዕድሜ ቢሰጥ ይወዳል፡፡ እርሱም ዕድሜ መሰጠቱ ከቅጣት የሚያርቀው አይደለም፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡