وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ ءَايَةَ مُلْكِهِۦٓ أَن يَأْتِيَكُمُ ٱلتَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ ءَالُ مُوسَىٰ وَءَالُ هَٰرُونَ تَحْمِلُهُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy248. በተጨማሪም ነብያቸው እንዲህ አላቸው:: «የንግስናው ምልክት መላእክት የሚሸከሙት ሳጥን ወደ እናንተ ይመጣል:: በውስጡ ለናንተ እርጋታን የሚፈጥርና የሙሳ እና የሀሩን ቤተሰብ የተውት ቅርስም ይገኝበታል:: በዚህም ውስጥ ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ ከባድ ተዐምር አለላችሁ።»
Amharic Translation - Muhammad Sadiqነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሳ ቤተሰብና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ ሳጥኑ ሊመጣላችሁ ነው፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አልለ» አላቸው፡፡