caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 93

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:93

وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَٰقَكُمْ وَرَفَعْنَا فَوْقَكُمُ ٱلطُّورَ خُذُوا۟ مَآ ءَاتَيْنَٰكُم بِقُوَّةٍ وَٱسْمَعُوا۟ قَالُوا۟ سَمِعْنَا وَعَصَيْنَا وَأُشْرِبُوا۟ فِى قُلُوبِهِمُ ٱلْعِجْلَ بِكُفْرِهِمْ قُلْ بِئْسَمَا يَأْمُرُكُم بِهِۦٓ إِيمَٰنُكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy93. የጡርን ጋራ ከበላያችሁ በማንሳት (በተውራት ሕግ እንደትሰሩ) ቃል ኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: «የሰጠናችሁን በጽናት ያዙ:: ያልነውንም ስሙ።» አልን:: «ሰማን ግን አመጽን» አሉ:: የወይፈኑም ውዴታ በክህደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ገብቷል:: «ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ እምነታችሁ የሚያዛችሁ ነገር የከፋ ነው።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየጡርንም ጋራ ከበላያችሁ ያነሳን ስንኾን (በኦሪት ሕግ እንድትሠሩ) ኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ «የሰጠናችሁን በኀይል ያዙ፤ ስሙም፤» (አልን)፡፡«ሰማን አመጽንም» አሉ፡፡ የወይፈኑንም ውዴታ በክሕደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ተጠጡ፡፡ «አማኞች እንደኾናችሁ እምነታችሁ በርሱ የሚያዛችሁ ነገር ከፋ!» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70