caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 197

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:197

ٱلْحَجُّ أَشْهُرٌ مَّعْلُومَٰتٌ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ ٱلْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِى ٱلْحَجِّ وَمَا تَفْعَلُوا۟ مِنْ خَيْرٍ يَعْلَمْهُ ٱللَّهُ وَتَزَوَّدُوا۟ فَإِنَّ خَيْرَ ٱلزَّادِ ٱلتَّقْوَىٰ وَٱتَّقُونِ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ

Amharic Translation - Africa Academy197. ሐጅ የሚፈጸመው በተወሰኑ የታወቁ ወራት ነው:: እናም በእነርሱ ውስጥ ሐጅን ለመስራት ግዴታ የገባ ሰው በሐጅ ክንውን ውስጥ እያለ ሴትን መገናኘት፤ በአላህ ላይ ማመጽና ክርክር አያደርግም:: (ሙስሊሞች ሆይ!)የምትሰሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል። ስንቅም ያዙ:: ከስንቅ ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው:: የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! እኔን ብቻ ፍሩኝ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሐጅ (ጊዜያቱ) የታወቁ ወሮች ናቸው፡፡ በእነርሱም ውስጥ ሐጅን (እንዲሠራ) ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም፡፡ ከበጎም ሥራ የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል፡፡ ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው፡፡ የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70