caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 140

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:140

أَمْ تَقُولُونَ إِنَّ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطَ كَانُوا۟ هُودًا أَوْ نَصَٰرَىٰ قُلْ ءَأَنتُمْ أَعْلَمُ أَمِ ٱللَّهُ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن كَتَمَ شَهَٰدَةً عِندَهُۥ مِنَ ٱللَّهِ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy140. ወይስ «ኢብራሂምም፣ ኢስማዒልም፣ ኢስሐቅም፣ ያዕቆብም፣ እንዲሁም ነገዶቹም አይሁድ ወይም ክርስቲያኖች ነበሩ» ትላላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) “እናንተ ናችሁ የምታውቁት? ወይንስ አላህ?” በላቸው:: እርሱ ዘንድ ከአላህ የሆነችን ምስክርነት ከደበቀ ይበልጥ አጥፊ ማነው? አላህ የምትፈጽሙትን ሁሉ ዘንጊ አይደለም።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወይም ኢብራሂም ኢስማዒልም ኢስሐቅም ያዕቁብም ነገዶቹም አይሁዶች ወይም ክርስቲያኖች ነበሩ ትላላችሁን? «እናንተ ታውቃላችሁን? ወይንስ አላህ?» በላቸው፡፡ እርሱም ዘንድ ከአላህ የኾነችን ምስክርነት ከደበቀ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? አላህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70