caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 173

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:173

إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ ٱلْمَيْتَةَ وَٱلدَّمَ وَلَحْمَ ٱلْخِنزِيرِ وَمَآ أُهِلَّ بِهِۦ لِغَيْرِ ٱللَّهِ فَمَنِ ٱضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَآ إِثْمَ عَلَيْهِ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy173. (አላህ) በእናንተ ላይ እርም ያደረገባችሁ በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ስጋንና ከአላህ ሌላ በሆነ ስም የታረደን ስጋ ብቻ ነው:: ተገዶ ችግሩን ለማስወገድ ያክል ብቻ ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይሆን (ቢመገብ) በእርሱ ላይ ምንም ሀጢአት የለበትም:: አላህ መሐሪና አዛኝ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ የእሪያ ሥጋንም፣ በእርሱም (ማረድ) ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይኾን (ለመብላት) የተገደደ ሰውም በርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70