يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلْقِصَاصُ فِى ٱلْقَتْلَى ٱلْحُرُّ بِٱلْحُرِّ وَٱلْعَبْدُ بِٱلْعَبْدِ وَٱلْأُنثَىٰ بِٱلْأُنثَىٰ فَمَنْ عُفِىَ لَهُۥ مِنْ أَخِيهِ شَىْءٌ فَٱتِّبَاعٌۢ بِٱلْمَعْرُوفِ وَأَدَآءٌ إِلَيْهِ بِإِحْسَٰنٍ ذَٰلِكَ تَخْفِيفٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَرَحْمَةٌ فَمَنِ ٱعْتَدَىٰ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَلَهُۥ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy178. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ግድያን በተመለከተ አጸፋዊ እርምጃ በእናንተ ላይ ተደንግጓል:: (እርሱም) ነፃ ሰውን በነፃ መግደል፤ ባሪያን በባሪያ መግደል፤ ሴትን በሴት መግደል::(ነው) ከሟች ወንድሙ ደም ትንሽ ነገር እንኳን ምህረት የተደረገለት ሰው በመሃሪው የሟች ወገን ላይ ካሳውን በመልካም መከታተል ሲኖርበት ምህረት የተደረገለት ገዳይም የነፍስ ዋጋውን ለእርሱ በመልካም አኳኋን መክፈል አለበት:: ይህ ከጌታችሁ የሆነ ማቃለልና እዝነት ነው:: ከዚህም በኋላ ህግን የተላለፈ ሰው እርሱ አሳማሚ ቅጣት ይጸናበታል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተገደሉ ሰዎች ማመሳሰል በናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ ነጻ በነጻ ባሪያም በባሪያ ሴትም በሴት (ይገደላሉ)፡፡ ለእርሱም (ለገዳዩ) ከወንድሙ (ደም) ትንሽ ነገር ምሕረት የተደረገለት ሰው (በመሓሪው ላይ ጉማውን) በመልካም መከታተል ወደርሱም (ወደ መሓሪው) ገዳዩ በመልካም አኳኋን መክፈል አለባቸው፡፡ ይህ ከጌታችሁ የኾነ ማቃለልና እዝነት ነው፡፡ ከዚህም በኋላ ሕግን የተላለፈ ሰው ለርሱ አሳማሚ ቅጣት አለው፡፡