ثُمَّ أَنتُمْ هَٰٓؤُلَآءِ تَقْتُلُونَ أَنفُسَكُمْ وَتُخْرِجُونَ فَرِيقًا مِّنكُم مِّن دِيَٰرِهِمْ تَظَٰهَرُونَ عَلَيْهِم بِٱلْإِثْمِ وَٱلْعُدْوَٰنِ وَإِن يَأْتُوكُمْ أُسَٰرَىٰ تُفَٰدُوهُمْ وَهُوَ مُحَرَّمٌ عَلَيْكُمْ إِخْرَاجُهُمْ أَفَتُؤْمِنُونَ بِبَعْضِ ٱلْكِتَٰبِ وَتَكْفُرُونَ بِبَعْضٍ فَمَا جَزَآءُ مَن يَفْعَلُ ذَٰلِكَ مِنكُمْ إِلَّا خِزْىٌ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يُرَدُّونَ إِلَىٰٓ أَشَدِّ ٱلْعَذَابِ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy85. ከዚያም ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ የምትገድሉ፤ ከናንተም መካከል የሆኑ ሕዝቦችን በኃጢአትና በመበደል ላይ በመተባበር ከአገሮቻቸው የምታስወጡ እናንተው ራሳችሁ ናችሁ:: ምርኮኞች ሆነው ወደ እናንተ ሲመጡም ቤዛ ትሆኗቸዋላችሁ:: እነርሱን ከመኖሪያ ክልላቸው ማባረሩ በእናንተ ላይ የተከለከለ ነው:: በመጽሐፉ በከፊሉ አምናችሁ በሌላው ትክዳላችሁን? ከእናንተ መካከል ይህንን ጸያፍ ተግባር የሚሰራ ሰው ሁሉ ቅጣቱ በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት አንጂ ሌላ አይደለም:: በትንሳኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ። አላህ ከምትሰሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከዚያም እናንተ እነዚያ ነፍሶቻችሁን የምትገድሉ ከናንተም የኾኑ ጭፍሮችን በኃጢአትና በመበደል በነርሱ ላይ የምትረዳዱ ስትኾኑ ከአገሮቻቸው የምታወጡ ምርኮኞችም ኾነው ቢመጡዋችሁ የምትበዡ ናችሁ፡፡ እርሱ (ነገሩ) እነርሱን ማውጣት በእናንተ ላይ የተከለከለ ነው፡፡ በመጽሐፉ ከፊል ታምናላችሁን? በከፊሉም ትክዳላችሁን? ከእናንተም ይህንን የሚሠራ ሰው ቅጣት በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡