caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 61

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:61

وَإِذْ قُلْتُمْ يَٰمُوسَىٰ لَن نَّصْبِرَ عَلَىٰ طَعَامٍ وَٰحِدٍ فَٱدْعُ لَنَا رَبَّكَ يُخْرِجْ لَنَا مِمَّا تُنۢبِتُ ٱلْأَرْضُ مِنۢ بَقْلِهَا وَقِثَّآئِهَا وَفُومِهَا وَعَدَسِهَا وَبَصَلِهَا قَالَ أَتَسْتَبْدِلُونَ ٱلَّذِى هُوَ أَدْنَىٰ بِٱلَّذِى هُوَ خَيْرٌ ٱهْبِطُوا۟ مِصْرًا فَإِنَّ لَكُم مَّا سَأَلْتُمْ وَضُرِبَتْ عَلَيْهِمُ ٱلذِّلَّةُ وَٱلْمَسْكَنَةُ وَبَآءُو بِغَضَبٍ مِّنَ ٱللَّهِ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَانُوا۟ يَكْفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَيَقْتُلُونَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَوا۟ وَّكَانُوا۟ يَعْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ሙሳ ሆይ! በአንድ ዓይነት ምግብ ላይ በፍጹም አንታገስም:: ስለዚህ ጌታህ ከእነዚያ ምድር ከምታበቅላቸው ከቅጠላ ቅጠሏ፤ ከዱባዋ፤ ከስንዴዋ፤ ከምስሯና ከሽንኩርቷ ያወጣልን ዘንድ ለምንልን።» (ባላችሁም ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ):: ሙሳም «ያንን ዝቅተኛ የሆነውን በዚያ ከፍተኛና በላጭ በሆነው ነገር ልትተኩ ትፈልጋላችሁን? ወደ ከተማ ውረዱ:: የጠየቃችሁትን ነገር ታገኛላችሁና።» አላቸው። ውርደትና ድህነት ተጣለባቸው:: በአላህም ቁጣ ተመለሱ:: ይህ እነርሱ በአላህ ተዐምራት ይክዱና ነብያትንም ያለ አግባብ ይገድሉ ስለነበሩ፤ በኃጢአትም ላይ በመዘፈቃቸውና እንዲሁም ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሙሳ ሆይ፡- «በአንድ (ዓይነት) ምግብ ላይ በፍጹም አንታገሥም፤ ስለዚህ ጌታህን ከዚያ ምድር ከምታበቅለው ሁሉ ከቅጠላቅጠል ከዱባዋም ከስንዴዋም ከምስርዋም ከሽንኩርቷም ለኛ ያወጣ ዘንድ ለኛ ለምንልን» ባላችሁም ጊዜ (የኾነውን አስታውሱ፡፡ ሙሳም፡- «ያንን እርሱ ዝቅተኛ የኾነውን በዚያ እርሱ በላጭ በኾነው ነገር ለውጥን ትፈልጋላችሁን? ወደ ከተማ ውረዱ፤ ለናንተም የጠየቃችሁት ነገር አላችሁ» አላቸው፡፡ በነርሱም ላይ ውርደትና ድኽነት ተመታባቸው፡፡ ከአላህም በኾነ ቁጣ ተመለሱ፡፡ ይህ እነርሱ በአላህ ታምራቶች ይክዱና ነቢያትንም ያለ ሕግ ይገድሉ ስለነበሩ ነው፡፡ ይህ በማመጻቸውና ወሰን የሚያልፉ በመኾናቸው ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70