فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُۥدُ جَالُوتَ وَءَاتَىٰهُ ٱللَّهُ ٱلْمُلْكَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَهُۥ مِمَّا يَشَآءُ وَلَوْلَا دَفْعُ ٱللَّهِ ٱلنَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّفَسَدَتِ ٱلْأَرْضُ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ ذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy251. እናም በአላህ ፈቃድ ድል መቷቸው:: ነብዩ ዳውድም ጃሉትን ገደለ:: ለዳውድ ንግሥናን፤ ጥበብን እና ነብይነትን አላህ ሰጣቸው:: ከሚሻው ነገር ሁሉ አሳወቀው:: አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መመለሱ (መከላከሉ) ባልነበረ ኖሮ ምድር በጠቅላላ በተበላሸች ነበር:: ግን አላህ በዓለማት ላይ የችሮታ ባለቤት ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፡፡ ዳውድም ጃሉትን (ዳዊት ጎልያድን) ገደለ፡፡ ንግሥናንና ጥበብንም (ነቢይነትን) አላህ ሰጠው፡፡ ከሚሻውም ነገር ሁሉ አሳወቀው፡፡ አላህም ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መመለሱ ባልነበረ ኖሮ ምድር በተበላሸች ነበር፤ ግን አላህ በዓለማት ላይ የችሮታ ባለቤት ነው፡፡