قُلْ إِن كَانَتْ لَكُمُ ٱلدَّارُ ٱلْـَٔاخِرَةُ عِندَ ٱللَّهِ خَالِصَةً مِّن دُونِ ٱلنَّاسِ فَتَمَنَّوُا۟ ٱلْمَوْتَ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ለአይሁድ) «የመጨረሻይቱ አገር ገነት በአላህ ዘንድ ከሌሎች በተለየ ለእናንተ ብቻ በመሆኗ እውነተኞች ከሆናችሁ እስቲ ሞትን ተመኙ።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«የመጨረሻይቱ አገር (ገነት) አላህ ዘንድ ከሰው ሁሉ ሌላ የተለየች ስትኾን ለእናንተ ብቻ እንደኾነች እውነተኞች ከኾናችሁ ሞትን ተመኙ» በላቸው፡፡