caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 217

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:217

يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلشَّهْرِ ٱلْحَرَامِ قِتَالٍ فِيهِ قُلْ قِتَالٌ فِيهِ كَبِيرٌ وَصَدٌّ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَكُفْرٌۢ بِهِۦ وَٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَإِخْرَاجُ أَهْلِهِۦ مِنْهُ أَكْبَرُ عِندَ ٱللَّهِ وَٱلْفِتْنَةُ أَكْبَرُ مِنَ ٱلْقَتْلِ وَلَا يَزَالُونَ يُقَٰتِلُونَكُمْ حَتَّىٰ يَرُدُّوكُمْ عَن دِينِكُمْ إِنِ ٱسْتَطَٰعُوا۟ وَمَن يَرْتَدِدْ مِنكُمْ عَن دِينِهِۦ فَيَمُتْ وَهُوَ كَافِرٌ فَأُو۟لَٰٓئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَأُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy217. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በተከበረው ወር ስለመጋደል ይጠይቁሃል። «በእነርሱ ውስጥ መጋደል ትልቅ ኃጢአት ነው:: ግን ከአላህ መንገድ ሰዎችን መከልከል፤ በእርሱም መካድ፤ ከተከበረው መስጊድ ማገድ፤ ባለቤቶቹንም ከእርሱ ማፈናቀል አላህ ዘንድ ይበልጥ የተለቀ ወንጀል ነው:: ፈተናም (በአላህ ማጋራትም) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው» በላቸው። ከሓዲያን ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስኪመልሷችሁ ድረስ የሚዋጓችሁ ከመሆን አይቦዝኑም:: ከናንተ ውስጥ ከሀይማኖቱ የሚመለስና እርሱ ከሃዲ ሆኖ የሚሞት ሁሉ እነዚያ በቅርቢቱ ሀገርም ሆነ በመጨረሻይቱ ሀገር በጎ ስራቸው ተበላሸች:: እነዚህ የእሳት ጓዶች ናቸው:: በእርሷም ውስጥ ለዘላለም ይዝወትራሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከተከበረው ወር (ከረጀብ) በርሱ ውስጥ ከመጋደል ይጠይቁሃል፡፡ በላቸው «በርሱ ውስጥ መጋደል ታላቅ (ኀጢአት) ነው፡፡ ግን ከአላህ መንገድ (ሰዎችን) መከላከል፣ በርሱም መካድ፣ ከተከበረውም መስጊድ (ማገድ) ባለቤቶቹንም ከርሱ ማውጣት አላህ ዘንድ ይበልጥ ታላቅ (ወንጀል) ነው፡፡ ፈተናም (ማጋራት) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው፡፡ (ከሐዲዎች) ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስከሚመልሳችሁ ድረስ የሚዋጉዋችሁ ከመሆን አይቦዝኑም፡፡ ከእናንተ ውስጥም ከሃይማኖቱ የሚመለስና እርሱም ከሐዲ ሆኖ የሚሞት ሰው እነዚያ (በጎ) ሥራቸው በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም አገር ተበላሸች፡፡ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70