وَلَكُمْ فِى ٱلْقِصَاصِ حَيَوٰةٌ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy179. እናንተ ባለ አእምሮዎች ሆይ! በአጸፋዊ እርምጃ ህግ ሕይወትን ትጎናጸፋላችሁ:: ይህም ግድያን ከመፈጸም ልትጠነቀቁ ዘንድ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእናንተም ባለ አእምሮዎች ሆይ! በማመሳሰል (ሕግ) ውስጥ ሕይወት አላችሁ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ (ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ)፡፡