أَوْ كَٱلَّذِى مَرَّ عَلَىٰ قَرْيَةٍ وَهِىَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا قَالَ أَنَّىٰ يُحْىِۦ هَٰذِهِ ٱللَّهُ بَعْدَ مَوْتِهَا فَأَمَاتَهُ ٱللَّهُ مِا۟ئَةَ عَامٍ ثُمَّ بَعَثَهُۥ قَالَ كَمْ لَبِثْتَ قَالَ لَبِثْتُ يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ قَالَ بَل لَّبِثْتَ مِا۟ئَةَ عَامٍ فَٱنظُرْ إِلَىٰ طَعَامِكَ وَشَرَابِكَ لَمْ يَتَسَنَّهْ وَٱنظُرْ إِلَىٰ حِمَارِكَ وَلِنَجْعَلَكَ ءَايَةً لِّلنَّاسِ وَٱنظُرْ إِلَى ٱلْعِظَامِ كَيْفَ نُنشِزُهَا ثُمَّ نَكْسُوهَا لَحْمًا فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُۥ قَالَ أَعْلَمُ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy259. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይም ያንን ሙሉ በሙሉ በፈራረሰች ከተማ ያለፈውን ሰው ተሞክሮ አላገናዘብክምን? ‹‹ይህችን ከተማ ከሞተች በኃላ አላህ እንዴት ሕያው ያደርጋታል? አለ:: ከዚያ አላህ ገደለውና መቶ ዓመትን አቆየው:: ከዚያ አስነሳው «ምን ያህል ቆየህ?» አለው:: «አንድ ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆይቻለሁ» አለ:: «ይልቁንም መቶ ዓመት ነው የቆየኸው:: ወደ ምግብህና ወደ መጠጥህም ተመልከት:: አንዱም አልተለወጠም:: ወደ አህያህም ተመልከት:: ለሰው ልጅም ተዐምር ልናደርግህ ዘንድ ይህንን ሰራን፤ ወደ አጽሞቿም እንዴት እንደምናስነሳት ከዚያ ስጋን እንዴት እንደምናለብሳት ተመልከት።» አለው:: ለእርሱም ማስረጃ በገለጸለት ጊዜ ‹‹አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አውቃለሁ›› አለ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወይም ያንን በከተማ ላይ እርሷ በጣራዎችዋ ላይ የወደቀች ስትኾን ያለፈውን ሰው ብጤ (አላየህምን)፡- «ይህችን (ከተማ) ከሞተች በኋላ አላህ እንዴት ሕያው ያደርጋታል» አለ፡፡ አላህም ገደለው መቶ ዓመትን (አቆየውም)፡፡ ከዚያም አስነሳው፡- «ምን ያህል ቆየህ» አለው፡፡ «አንድ ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየሁ» አለ፡፡ «አይደለም መቶን ዓመት ቆየህ፡፡ ወደ ምግብህና ወደ መጠጥህም ያልተለወጠ ሲኾን ተመልከት፡፡ ወደ አህያህም ተመልከት፡፡ ለሰዎችም አስረጅ እናደርግህ ዘንድ (ይህንን ሠሰራን)፡፡ ወደ ዐፅሞቹም እንዴት እንደምናስነሳት ከዚያም ሥጋን እንደምናለብሳት ተመልከት» አለው፡፡ ለርሱም (በማየት) በተገለጸለት ጊዜ፡- «አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን ዐውቃለሁ» አለ፡፡