caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 184

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:184

أَيَّامًا مَّعْدُودَٰتٍ فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ وَعَلَى ٱلَّذِينَ يُطِيقُونَهُۥ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ فَمَن تَطَوَّعَ خَيْرًا فَهُوَ خَيْرٌ لَّهُۥ وَأَن تَصُومُوا۟ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy184. ውስን ቀናትን ጹሙ። ከናንተም ውስጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ባልፆማቸው ቀናት ልክ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸውን ቀናት መፆም አለበት:: እነዚያ ለመፆም ከአቅም በላይ ችግር የገጠማቸው ሰዎች ደግሞ አፍጥረው ለየቀኑ እንድ ድሃን የአንድ ጊዜ ምግብ ማብላት ይኖርባቸዋል:: ከዚህ በላይ ቤዛን በመጨመር መልካምንም ስራ የፈቀደ ሰው (እርሱ ፈቅዶ መጨመሩ ለራሱ) በላጭ ተግባር ነው:: ግና በመንገድ ላይ ሆናችሁ መፆማቸሁ ለእናንተ የበለጠ ነው:: የምታውቁ ብትሆኑ ትመርጡታላችሁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየተቆጠሩን ቀኖች (ጹሙ)፡፡ ከእናንተም ውሰጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (መጾም) አለበት፡፡ በእነዚያም ጾምን በማይችሉት ላይ ቤዛ ድኻን ማብላት አለባቸው፡፡ (ቤዛን በመጨመር) መልካምንም ሥራ የፈቀደ ሰው እርሱ (ፈቅዶ መጨመሩ) ለርሱ በላጭ ነው፡፡ መጾማችሁም ለናንተ የበለጠ ነው፤ የምታውቁ ብትኾኑ (ትመርጡታላችሁ)፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70