وَإِذَا طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَبَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ سَرِّحُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ وَلَا تُمْسِكُوهُنَّ ضِرَارًا لِّتَعْتَدُوا۟ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُۥ وَلَا تَتَّخِذُوٓا۟ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ هُزُوًا وَٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ وَمَآ أَنزَلَ عَلَيْكُم مِّنَ ٱلْكِتَٰبِ وَٱلْحِكْمَةِ يَعِظُكُم بِهِۦ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy231. (ሙስሊሞች ሆይ!) ሚስቶቻችሁን በፈታችሁ እና የኢዳ ጊዜያቸውን ለማገባደድ በቀረቡ ጊዜ በመልካም መልሷቸው:: ወይም በመልካም ሁኔታ ያለ አንድ ጉዳት አሰናብቷቸው:: ለመጉዳትም ወሰን ታልፉባቸው ዘንድ አትያዟቸው:: ይህን የሚሰራም ነፍሱን በእርግጥ በደለ:: የአላህን አናቅጽ ማላገጫ አታድርጉ:: አላህ በእናንተ ላይ የዋለውን ጸጋ፤ በእርሱ ሊገስፃችሁም ያወረደውን መጽሐፍ (ቁርኣንን) እና ጥበብንም (ሱናን) አስታውሱ:: አላህንም ፍሩ:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ አዋቂ መሆኑንም እወቁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሴቶችን በፈታችሁና (የዒዳ) ጊዜያቸውን በደረሱ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፤ (ተማለሷቸው) ወይም በመልካም ኹኔታ አሰናብቱዋቸው፡፡ ለመጉዳትም ወሰን ታልፋባቸው ዘንድ አትያዙዋቸው፤ ይህንንም የሚሠራ ሰው ነፍሱን በእርግጥ በደለ፡፡ የአላህንም አንቀጾች ማላገጫ አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ የአላህንም ጸጋ በናንተ ላይ ያደረገውን ከመጽሐፍና ከጥበብም በርሱ የሚገስጻችሁ ሲኾን በናንተ ላይ ያወረደውን አስታውሱ፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ መኾኑን ዕወቁ፡፡