فَأَزَلَّهُمَا ٱلشَّيْطَٰنُ عَنْهَا فَأَخْرَجَهُمَا مِمَّا كَانَا فِيهِ وَقُلْنَا ٱهْبِطُوا۟ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ وَلَكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy36. ሰይጣንም ከእርሷ አሳሳታቸው። ከነበሩበትም ገነት አወጣቸው። «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ሁላችሁም (ወደ ምድር) ውረዱ። ለእናንተም በምድር ላይ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።» አልናቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከርሷም ሰይጣን አዳለጣቸው በውስጡም ከነበሩበት (ድሎት) አወጣቸው፡፡ «ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ፤ ለናንተም በምድር ላይ እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ መርጊያና መጣቀሚያ አላችሁ» አልናቸው፡፡