وَإِذِ ٱسْتَسْقَىٰ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦ فَقُلْنَا ٱضْرِب بِّعَصَاكَ ٱلْحَجَرَ فَٱنفَجَرَتْ مِنْهُ ٱثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا قَدْ عَلِمَ كُلُّ أُنَاسٍ مَّشْرَبَهُمْ كُلُوا۟ وَٱشْرَبُوا۟ مِن رِّزْقِ ٱللَّهِ وَلَا تَعْثَوْا۟ فِى ٱلْأَرْضِ مُفْسِدِينَ
Amharic Translation - Africa Academy60. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለሕዝቦቹ የመጠጥ ውሃን በፈለገ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውሱ:: «ድንጋዩን በዘንግህ ምታው።» አልነው:: መታዉም ከእርሱም አስራ ሁለት ምንጮች ፈለቁ (ፈነዱ)፤ ሰዎቹ ሁሉ በትክክል መጠጫቸውን አወቁ:: «ከአላህ ሲሳይ ብሉ፤ ጠጡም፤ አመጸኞችም ሆናችሁ በምድር ላይ አታበላሹ።» (አልናቸው)።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ (የኾነውን አስታውሱ)፡፡ «ድንጋዩንም በበትርህ ምታ» አልነው፡፡ (መታውም) ከርሱም ዐሥራ ሁለት ምንጮች ፈለቁ፡፡ ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ ዐወቁ፡፡ «ከአላህ ሲሳይ ብሉ፤ ጠጡም፤ አመጠኞችም ኾናችሁ በምድር ላይ አታበላሹ» (አልናቸው)፡፡