وَإِن كُنتُمْ عَلَىٰ سَفَرٍ وَلَمْ تَجِدُوا۟ كَاتِبًا فَرِهَٰنٌ مَّقْبُوضَةٌ فَإِنْ أَمِنَ بَعْضُكُم بَعْضًا فَلْيُؤَدِّ ٱلَّذِى ٱؤْتُمِنَ أَمَٰنَتَهُۥ وَلْيَتَّقِ ٱللَّهَ رَبَّهُۥ وَلَا تَكْتُمُوا۟ ٱلشَّهَٰدَةَ وَمَن يَكْتُمْهَا فَإِنَّهُۥٓ ءَاثِمٌ قَلْبُهُۥ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy283. በጉዞ ላይ ብትሆኑና ጸሐፊ ባታገኙ በእጅ የተጨበጡ መተማመኛዎችን ያዙ:: ከፊላችሁ ከፊሉን ቢያምን ያ የታመነው ሰው አደራውን በትክክል ያድርስ:: አላህንም ጌታውን ይፍራ:: ምስክርነትንም አትደብቁ። ምስክርነትን የሚደብቃት ልበ ኃጢአተኛ ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበጉዞ ላይ ብትኾኑና ጸሐፊን ባታገኙ የተጨበጡ መተማመኛዎችን ያዙ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን ቢያምን ያ የታመነው ሰው አደራውን ያድርስ፡፡ አላህንም ጌታውን ይፍራ፡፡ ምስክርነትንም አትደብቁ፡፡ የሚደብቃትም ሰው እርሱ ልቡ ኃጢኣተኛ ነው፡፡ አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡