caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 164

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:164

إِنَّ فِى خَلْقِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفِ ٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ وَٱلْفُلْكِ ٱلَّتِى تَجْرِى فِى ٱلْبَحْرِ بِمَا يَنفَعُ ٱلنَّاسَ وَمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مِن مَّآءٍ فَأَحْيَا بِهِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا وَبَثَّ فِيهَا مِن كُلِّ دَآبَّةٍ وَتَصْرِيفِ ٱلرِّيَٰحِ وَٱلسَّحَابِ ٱلْمُسَخَّرِ بَيْنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy164. የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና ቀንም መፈራረቅ (መተካካት)፤ ያችም ሰዎችን የሚጠቅም ነገር (ተጭና) በባህር ላይ የምትንሳፈፈው መርከብ፤ አላህም ከሰማይ ባወረደው ውሃና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ በእርሷም ውስጥ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በመበተኑ፤ ንፋሶችንም በየአቅጣጫው የሚያገላብጥ መሆኑ እንዲሁም በሰማይና በምድር በሚነዳው ዳመና ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ አያሌ ተዐምራት አሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሰማያትንና ምድርን በመፍጠር፣ ሌሊትንና ቀንንም በማተካካት፣ በዚያቸም ሰዎችን በሚጠቅም ነገር (ተጭና) በባህር ላይ በምትንሻለለው ታንኳ፣ አላህም ከሰማይ ባወረደው ውሃና በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ፣ በርሷም ውስጥ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በመበተኑ፣ ነፋሶችንም (በየአግጣጫው) በማገለባበጥ፣ በሰማይና በምድር መካከል በሚነዳውም ደመና ለሚያውቁ ሕዝቦች እርግጠኛ ምልክቶች አሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70