caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 213

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:213

كَانَ ٱلنَّاسُ أُمَّةً وَٰحِدَةً فَبَعَثَ ٱللَّهُ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ وَأَنزَلَ مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ لِيَحْكُمَ بَيْنَ ٱلنَّاسِ فِيمَا ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ وَمَا ٱخْتَلَفَ فِيهِ إِلَّا ٱلَّذِينَ أُوتُوهُ مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ بَغْيًۢا بَيْنَهُمْ فَهَدَى ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لِمَا ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ مِنَ ٱلْحَقِّ بِإِذْنِهِۦ وَٱللَّهُ يَهْدِى مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy213. ሰዎች ሁሉ (አላህን አንድ በማድረግ) አንድ ሕዝብ ነበሩ:: (ከዚያም ተለያዩ):: ከዚያም አላህ ነብያትን ለመልካም ሰዎች በገነት አብሳሪዎችና ለመጥፎ ሰዎች ደግሞ ከእሳት አስጠንቃቂዎች አድርጎ ላከ:: ከነሱ ጋርም ከሰዎቹ መካከል በዚያ እነርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ መጽሐፍትን በእውነት አወረደ:: በእርሱ ግልጽ አስረጂዎች ከመጡላቸው በኋላ በመካከላቸው በተፈጠረው ምቀኝነት ሰበብ እነዚያው መጽሐፍትን የተሰጡት ሰዎች እንጂ አልተለያዩበትም:: አላህ እነዚያን በአላህ ያመኑትን ሰዎች በእነርሱ የተለያዩበትን እውነታ ይገነዘቡ ዘንድ በፈቃዱ መራቸው:: አላህ የሚሻውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)፡፡ አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ፡፡ ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ በእውነት አወረደ፡፡ በእርሱም (በሃይማኖት) ግልጽ አስረጂዎች ከመጡላቸው በኋላ በመካከላቸው ለኾነው ምቀኝነት እነዚያው የተሰጡት እንጂ አልተለያዩበትም፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትን ሰዎች ለእዚያ ከእውነት በርሱ ለተለያዩበት በፍቃዱ መራቸው፡፡ አላህም የሚሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70