caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan آل عمران

200 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓمٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْحَىُّ ٱلْقَيُّومُ

Amharic Translation - Africa Academy2. አላህ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ህያው፤ በራሱ የተብቃቃና የሁሉ ነገር አስተናባሪ (የፍጡራን ተንከባካቢ) ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نَزَّلَ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ቁርኣንን ከእርሱ በፊት ያሉትን መጽሐፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደው። ከቁርኣን በፊትም ለሰዎች መሪ አድርጎ ተውራትንና ኢንጅልን አውርዷል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِن قَبْلُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ ٱلْفُرْقَانَ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ ذُو ٱنتِقَامٍ

Amharic Translation - Africa Academy4. ከቁርኣን በፊትም ለሰዎች መሪ አድርጎ ተውራትንና ኢንጅልን አውርዷል። (በእውነትና በውሸት መካከል መለያ የሆነውን) ፉርቃንንም አወረደ። እነዚያ በአላህ አናቅጽ የካዱ ሁሉ ብርቱ ቅጣት አለባቸው። አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ አስተባባዮችን ተበቃይም ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَخْفَىٰ عَلَيْهِ شَىْءٌ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَا فِى ٱلسَّمَآءِ

Amharic Translation - Africa Academy5. አላህ በምድርም ሆነ በሰማይ ምንም ነገር አይሸሸግበትም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِى يُصَوِّرُكُمْ فِى ٱلْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَآءُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy6. በማህጸኖች ውስጥ እንደፈለገው አድርጎ የሚቀርፃችሁ እርሱው ነው። ከእርሱ ከአሸናፊዉና ከጥበበኛው ጌታ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ በፍጹም የለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ مِنْهُ ءَايَٰتٌ مُّحْكَمَٰتٌ هُنَّ أُمُّ ٱلْكِتَٰبِ وَأُخَرُ مُتَشَٰبِهَٰتٌ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَٰبَهَ مِنْهُ ٱبْتِغَآءَ ٱلْفِتْنَةِ وَٱبْتِغَآءَ تَأْوِيلِهِۦ وَمَا يَعْلَمُ تَأْوِيلَهُۥٓ إِلَّا ٱللَّهُ وَٱلرَّٰسِخُونَ فِى ٱلْعِلْمِ يَقُولُونَ ءَامَنَّا بِهِۦ كُلٌّ مِّنْ عِندِ رَبِّنَا وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ

Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያ ባንተ ላይ መጽሐፍን-(ቁርኣንን) ያወረደ ነው:: ከመጽሐፉም ውስጥ ግልጽ የሆኑ አናቅጽ አሉ:: እነርሱም የመጽሐፉ መሰረቶች ናቸው። ሌሎች ደግሞ አሻሚ ትርጉም ያላቸው አሉ:: እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሌሎችን ለማሳሳት በማሰብና ትርጉሙን በሻቸው ለመለወጥ ሲሉ አሻሚ ትርጉም (ተመሳሳይነት) ያሏቸውን አናቅጽ ብቻ ይከታተላሉ። ትክክለኛ ትርጉማቸውን አላህ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም አያውቀዉም:: እነዚያ በእውቀት የጠለቁት ግን «በእርሱ አምነናል። ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው።» ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶች እንጂ አይገሰጽም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً إِنَّكَ أَنتَ ٱلْوَهَّابُ

Amharic Translation - Africa Academy8. (እነርሱም የሚሉ ናቸው:) «ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን ወደ መጥፎ አታዘንብልብን:: ካንተ ዘንድ የሆነን ችሮታ ስጠን:: አንተ በጣም ለጋስ ነህና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبَّنَآ إِنَّكَ جَامِعُ ٱلنَّاسِ لِيَوْمٍ لَّا رَيْبَ فِيهِ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُخْلِفُ ٱلْمِيعَادَ

Amharic Translation - Africa Academy9. «ጌታችን ሆይ! አንተ በዚያ ለመምጣቱ ጥርጥር በሌለበት ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ:: ምን ጊዜም አላህ ቀጠሮን አያፈርስምና»::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَن تُغْنِىَ عَنْهُمْ أَمْوَٰلُهُمْ وَلَآ أَوْلَٰدُهُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمْ وَقُودُ ٱلنَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy10. እነዚያ የካዱትን ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ (ቅጣት) አያስጥሏቸዉም። እነዚያም እነርሱ የእሳት ማገዶዎች ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَدَأْبِ ءَالِ فِرْعَوْنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمْ وَٱللَّهُ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy11. ምሳሊያቸው ልክ እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደነዚያ ከበፊታቸዉም እንደነበሩት ሕዝቦች ልማድ ነው:: በአናቅጻችን አስተባበሉ:: እናም አላህ በኃጢአቶቻቸው ቀጣቸው:: አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُوا۟ سَتُغْلَبُونَ وَتُحْشَرُونَ إِلَىٰ جَهَنَّمَ وَبِئْسَ ٱلْمِهَادُ

Amharic Translation - Africa Academy12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ለካዱ ሰዎች «በቅርብ ጊዜ ትሸነፋላችሁ:: ከዚያም በገሀነም ትሰበሰባላችሁ:: ምንጣፊቱም (ገሀነም) ምን ትከፋ!» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَدْ كَانَ لَكُمْ ءَايَةٌ فِى فِئَتَيْنِ ٱلْتَقَتَا فِئَةٌ تُقَٰتِلُ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَأُخْرَىٰ كَافِرَةٌ يَرَوْنَهُم مِّثْلَيْهِمْ رَأْىَ ٱلْعَيْنِ وَٱللَّهُ يُؤَيِّدُ بِنَصْرِهِۦ مَن يَشَآءُ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَعِبْرَةً لِّأُو۟لِى ٱلْأَبْصَٰرِ

Amharic Translation - Africa Academy13. በእነዚያ (የበድር) ቀን በተጋጠሙት ሁለት ቡድኖች ለእናንተ ብዙ ተዓምራት አሉ:: አንደኛዋ ቡድን በአላህ መንገድ ትጋደላለች:: ሌላይቱ ቡድን ደግሞ ከሓዲ ናት። በዓይን አስተያየት እጥፋቸው ሆነው ያዩዋቸዋል (በቁጥር የነርሱ እጥፍ ሁነው በአይናቸው ተመለከቷቸው)። አላህ በእርዳታው የሚሻውን ሁሉ ያበረታልና። በዚህ ውስጥ ለማስተዋል ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ መገሰጫ አለበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

زُيِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ ٱلشَّهَوَٰتِ مِنَ ٱلنِّسَآءِ وَٱلْبَنِينَ وَٱلْقَنَٰطِيرِ ٱلْمُقَنطَرَةِ مِنَ ٱلذَّهَبِ وَٱلْفِضَّةِ وَٱلْخَيْلِ ٱلْمُسَوَّمَةِ وَٱلْأَنْعَٰمِ وَٱلْحَرْثِ ذَٰلِكَ مَتَٰعُ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَٱللَّهُ عِندَهُۥ حُسْنُ ٱلْمَـَٔابِ

Amharic Translation - Africa Academy14. ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆች፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከተከማቹ ገንዘቦች፣ ከተሰማሩ ፈረሶች፣ ከግመል ከከብትና ከፍየል፣ ከአዝመራም የሆኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመላቸው (ሰዎች ዘንድ የተወደዱ ተደረገላቸው)። ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው:: አላህ ግን እርሱ ዘንድ መልካም የሆነ መመለሻ (ገነት) አለው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَٰلِكُمْ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّٰتٌ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَٰجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَٰنٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ بَصِيرٌۢ بِٱلْعِبَادِ

Amharic Translation - Africa Academy15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከዚህ ከተዋበላችሁ ጉዳይ የሚበልጥን ልንገራችሁን? እርሱም ለእነዚያ አላህን ለሚፈሩ ሁሉ በጌታቸው ዘንድ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲሆኑ ንጹህ ሚስቶችና ከአላህ የሆነ ውዴታም አለላቸው:: አላህም ባርያዎቹን ተመልካች ነው።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَآ إِنَّنَآ ءَامَنَّا فَٱغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy16. (እነርሱም) እነዚያ «ጌታችን ሆይ! እኛ ባንተ አመንን። ኃጢአቶቻችንን ማርልን። የእሳትን ቅጣት ጠብቀን።» የሚሉ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلصَّٰبِرِينَ وَٱلصَّٰدِقِينَ وَٱلْقَٰنِتِينَ وَٱلْمُنفِقِينَ وَٱلْمُسْتَغْفِرِينَ بِٱلْأَسْحَارِ

Amharic Translation - Africa Academy17. እነርሱም ታጋሾች፤ እውነተኞች፤ ታዛዦች፤ ለጋሾችና በሌሊት መጨረሻዎች ሰዓታት ላይ አላህን ምህረት የሚለምኑ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

شَهِدَ ٱللَّهُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَأُو۟لُوا۟ ٱلْعِلْمِ قَآئِمًۢا بِٱلْقِسْطِ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy18. አላህ (በማስተካከል) ቀጥ ያለ ሲሆን ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የሌለ መሆኑን መሰከረ። መላዕክትና የእውቀት ባለቤቶችም መሰከሩ። ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም:: እርሱ ሁሉን አሸናፊውና ጥበበኛው ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ وَمَا ٱخْتَلَفَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلْعِلْمُ بَغْيًۢا بَيْنَهُمْ وَمَن يَكْفُرْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ

Amharic Translation - Africa Academy19. አላህ ዘንድ የተወደደው ሀይማኖት ኢስላም ብቻ ነው:: እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎች በመካከላቸው ባለው ምቀኝነት እውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም:: በአላህ አናቅጽ ለሚክድ ሁሉ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنْ حَآجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِىَ لِلَّهِ وَمَنِ ٱتَّبَعَنِ وَقُل لِّلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْأُمِّيِّـۧنَ ءَأَسْلَمْتُمْ فَإِنْ أَسْلَمُوا۟ فَقَدِ ٱهْتَدَوا۟ وَّإِن تَوَلَّوْا۟ فَإِنَّمَا عَلَيْكَ ٱلْبَلَٰغُ وَٱللَّهُ بَصِيرٌۢ بِٱلْعِبَادِ

Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህም «ፊቴን ለአላህ ብቻ ሰጠሁ። የተከተሉኝም እንደዚሁ ለአላህ ብቻ ሰጡ።» በላቸው:: ለእነዚያም መጽሐፉን ለተሰጡ ሰዎችና ለመሃይማኑ (ዐረቦች)፡- «ሰለማችሁን?» በላቸው:: ቢሰልሙም በእርግጥ ወደቀናው መንገድ ተመሩ:: እምቢ ቢሉ ግን ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትን ማድረስ ብቻ ነው:: አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكْفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَيَقْتُلُونَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ بِغَيْرِ حَقٍّ وَيَقْتُلُونَ ٱلَّذِينَ يَأْمُرُونَ بِٱلْقِسْطِ مِنَ ٱلنَّاسِ فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ አናቅጽ የሚክዱ፤ ነብያትንም ያለ አግባብ የሚገድሉ፤ ከሰዎችም ውስጥ እነዚያን በትክክለኛነት የሚያዙትን የሚገድሉ በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ حَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy22. እነዚያ በቅርቢቱም ሆን በመጨረሻይቱ ዓለም ስራዎቻቸው የተበላሹ ናቸው:: ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ نَصِيبًا مِّنَ ٱلْكِتَٰبِ يُدْعَوْنَ إِلَىٰ كِتَٰبِ ٱللَّهِ لِيَحْكُمَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ يَتَوَلَّىٰ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ وَهُم مُّعْرِضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፍ (ትምህርት) ድረሻን ወደ ተሰጡት ሰዎች አላየህምን? ወደ አላህ መጽሐፍ በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ይጠራሉ:: ከዚያ ከእነርሱ ገሚሶቹ (ከፊሎቹ) እውነቱን ወደ ጎን የተው ሆነው ይሸሻሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَالُوا۟ لَن تَمَسَّنَا ٱلنَّارُ إِلَّآ أَيَّامًا مَّعْدُودَٰتٍ وَغَرَّهُمْ فِى دِينِهِم مَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy24. ይህም እነርሱ «የገሀነም እሳት የተቆጠሩ ቀናትን ብቻ እንጂ አትነካንም።» በማለታቸው ነው:: በሀይማኖታቸዉም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር አታለላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَيْفَ إِذَا جَمَعْنَٰهُمْ لِيَوْمٍ لَّا رَيْبَ فِيهِ وَوُفِّيَتْ كُلُّ نَفْسٍ مَّا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy25. በእርሱ መምጣት ጥርጥር የሌለበት በሆነው ቀን በሰበሰብናቸውና ነፍስ ሁሉ የሰራችውን ስራ በተሞላች ጊዜ እንዴት ይሆናሉ? እነርሱም ቅንጣትንም አይበደሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلِ ٱللَّهُمَّ مَٰلِكَ ٱلْمُلْكِ تُؤْتِى ٱلْمُلْكَ مَن تَشَآءُ وَتَنزِعُ ٱلْمُلْكَ مِمَّن تَشَآءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَآءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَآءُ بِيَدِكَ ٱلْخَيْرُ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል: «የንግስና ባለቤት የሆንከው አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግስናን ትሰጣለህ:: ከምትሻዉም ሰው ንግስናን ትገፋለህ:: የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ:: የምትሻውንም ሰው ደግሞ ታዋርዳለህ:: መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ብቻ ነው:: አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تُولِجُ ٱلَّيْلَ فِى ٱلنَّهَارِ وَتُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِى ٱلَّيْلِ وَتُخْرِجُ ٱلْحَىَّ مِنَ ٱلْمَيِّتِ وَتُخْرِجُ ٱلْمَيِّتَ مِنَ ٱلْحَىِّ وَتَرْزُقُ مَن تَشَآءُ بِغَيْرِ حِسَابٍ

Amharic Translation - Africa Academy27. «ሌሊቱን በቀን ውስጥ ታስገባለህ:: ቀኑንም በሌሊት ውስጥ ታስገባለህ:: ሕያውንም ከሙት ታወጣለህ:: ሙታንንም ከሕያው ታወጣለህ፤ ለምትሻውም ሁሉ መጠን የለሽ ሲሳይ ትሰጣለህ።» በል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا يَتَّخِذِ ٱلْمُؤْمِنُونَ ٱلْكَٰفِرِينَ أَوْلِيَآءَ مِن دُونِ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَلَيْسَ مِنَ ٱللَّهِ فِى شَىْءٍ إِلَّآ أَن تَتَّقُوا۟ مِنْهُمْ تُقَىٰةً وَيُحَذِّرُكُمُ ٱللَّهُ نَفْسَهُۥ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy28. አማኞች ከሓዲያንን ከአማኞች ሌላ ረዳቶች አድርገው አይያዙ። ይህንን የሚሰራ ከአላህ ሀይማኖት በምንም ውስጥ አይደለም:: ከእነርሱ መጠበቅን ብትጠበቁ እንጂ:: አላህ ከእርሱው ያስጠነቅቃችኋል:: መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ إِن تُخْفُوا۟ مَا فِى صُدُورِكُمْ أَوْ تُبْدُوهُ يَعْلَمْهُ ٱللَّهُ وَيَعْلَمُ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ብትደብቁት ወይም ብትገልጹት አላህ ያውቀዋል:: በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።» በል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ تَجِدُ كُلُّ نَفْسٍ مَّا عَمِلَتْ مِنْ خَيْرٍ مُّحْضَرًا وَمَا عَمِلَتْ مِن سُوٓءٍ تَوَدُّ لَوْ أَنَّ بَيْنَهَا وَبَيْنَهُۥٓ أَمَدًۢا بَعِيدًا وَيُحَذِّرُكُمُ ٱللَّهُ نَفْسَهُۥ وَٱللَّهُ رَءُوفٌۢ بِٱلْعِبَادِ

Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ነፍስ ሁሉ ከመልካም ነገር የሰራችውን የቀረበ ሆኖ የምታገኝበትን ቀን (አስታውስ):: ከመጥፎም የሰራችው በእርሷና በኃጢአቱ መካከል በጣም የሰፋ ርቀት ቢኖር ትመኛለች:: አላህ እራሱን ያስጠነቅቃችኋል:: አላህ ለባሮቹ ሩህሩህ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ እኔን ተከተሉኝ:: አላህም ይወዳችኋል፤ ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ أَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ። ብሸሹም አላህ ከሓዲያንን አይወድም» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰٓ ءَادَمَ وَنُوحًا وَءَالَ إِبْرَٰهِيمَ وَءَالَ عِمْرَٰنَ عَلَى ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy33. አላህ (ነብዩ) አደምን፣(ነብዩ) ኑህን፣(የነብዩ) ኢብራሂምን ቤተሰብ እና የዒምራንን ቤተሰብ ከአለማት አበለጣቸው (መረጣቸው)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذُرِّيَّةًۢ بَعْضُهَا مِنۢ بَعْضٍ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy34. እኒህን ቤተሰቦች ከፊሉ ከከፊሉ የሆነ ዝርያ አድርጎ መረጣቸው። አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَتِ ٱمْرَأَتُ عِمْرَٰنَ رَبِّ إِنِّى نَذَرْتُ لَكَ مَا فِى بَطْنِى مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّىٓ إِنَّكَ أَنتَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዒምራን ባለቤት (ሀና) «ጌታዬ ሆይ! በሆዴ ውስጥ ያለውን ጽንስ ከሥራ ነፃ የተደረገ ሲሆን ላንተ አገልግሎት ይውል ዘንድ ተሳልኩ:: እናም ተቀበለኝ:: አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና።» ባለች ጊዜ የሆነውን አስታውሱ በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا وَضَعَتْهَا قَالَتْ رَبِّ إِنِّى وَضَعْتُهَآ أُنثَىٰ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا وَضَعَتْ وَلَيْسَ ٱلذَّكَرُ كَٱلْأُنثَىٰ وَإِنِّى سَمَّيْتُهَا مَرْيَمَ وَإِنِّىٓ أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ ٱلشَّيْطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy36. በወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! ሴት ሆና ወለድኳት።» አለች። አላህ የወለደችውን ምንነት አዋቂ ነው:: የተመኘችው ወንድ እንደ ወለደቻት ሴት የሚሆን አልነበረም:: «መርየምም ብዬ ስም አወጣሁላት:: እኔም እርሷንና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን ተንኮል ባንተ እጠብቃቸዋለሁ።» አለች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتَقَبَّلَهَا رَبُّهَا بِقَبُولٍ حَسَنٍ وَأَنۢبَتَهَا نَبَاتًا حَسَنًا وَكَفَّلَهَا زَكَرِيَّا كُلَّمَا دَخَلَ عَلَيْهَا زَكَرِيَّا ٱلْمِحْرَابَ وَجَدَ عِندَهَا رِزْقًا قَالَ يَٰمَرْيَمُ أَنَّىٰ لَكِ هَٰذَا قَالَتْ هُوَ مِنْ عِندِ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ يَرْزُقُ مَن يَشَآءُ بِغَيْرِ حِسَابٍ

Amharic Translation - Africa Academy37. ጌታዋም በመልካም አቀባበል ተቀበላት:: በመልካም አስተዳደግም አፋፋት:: ከዚያም ዘከርያ አሳደጋት:: ዘከርያም ወደ ምኩራቧ በሷ ላይ በገባ ቁጥርም እርሷ ዘንድ ሲሳይን አገኘ:: «መርየም ሆይ! ይህ ለአንቺ ከየት ነው የሚመጣልሽ?» አላት። «እርሱ የሚመጣልኝ ከአላህ ዘንድ ነው:: አላህ እኮ ለሚሻው ሁሉ ሲሳዩን ያለ ሂሳብ ይሰጣል።» አለችው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُنَالِكَ دَعَا زَكَرِيَّا رَبَّهُۥ قَالَ رَبِّ هَبْ لِى مِن لَّدُنكَ ذُرِّيَّةً طَيِّبَةً إِنَّكَ سَمِيعُ ٱلدُّعَآءِ

Amharic Translation - Africa Academy38. እዚያ ዘንድም ዘከርያ ጌታውን እንደዚህ በማለት ለመነ: «ጌታዬ ሆይ! ካንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለእኔ ስጠኝ:: አንተ ጸሎትን ሰሚ ነህና» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَنَادَتْهُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَهُوَ قَآئِمٌ يُصَلِّى فِى ٱلْمِحْرَابِ أَنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًۢا بِكَلِمَةٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy39. እርሱም በዱዓ ማድረጊያ ክፍል ቆሞ ዱዓ ሲያደርግ መላዕክት:- «አላህ በየህያ: ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ፣ በላጭ፣ ከሴት ጋር የማይገናኝ ድንግልና ከደጋጎቹም አንዱ ሲሆን ያበስርሃል።» በማለት መላዕክት ጠሩት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى غُلَٰمٌ وَقَدْ بَلَغَنِىَ ٱلْكِبَرُ وَٱمْرَأَتِى عَاقِرٌ قَالَ كَذَٰلِكَ ٱللَّهُ يَفْعَلُ مَا يَشَآءُ

Amharic Translation - Africa Academy40. ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና የደረሰብኝ ሚስቴም መካን ስትሆን እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለ። መልአኩም: «ልክ እንደዚሁ ነው። አላህ የሚሻውን ነገር ሁሉ ይሰራልና።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ ٱجْعَل لِّىٓ ءَايَةً قَالَ ءَايَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ ٱلنَّاسَ ثَلَٰثَةَ أَيَّامٍ إِلَّا رَمْزًا وَٱذْكُر رَّبَّكَ كَثِيرًا وَسَبِّحْ بِٱلْعَشِىِّ وَٱلْإِبْكَٰرِ

Amharic Translation - Africa Academy41. ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! ለእዚህ ነገር ምልክትን አድርግልኝ።» አለ:: «ምልክትህ ሶስት ቀን በጥቅሻ እንጂ ሰዎችን አለማናገርህ ነው:: በዚያ ጊዜ ጌታህን በብዙ አውሳ:: በማታና በጠዋትም አወድሰው።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ قَالَتِ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ يَٰمَرْيَمُ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰكِ وَطَهَّرَكِ وَٱصْطَفَىٰكِ عَلَىٰ نِسَآءِ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላእክትም ባሉ ጊዜ: «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ:: ከነውሮች ሁሉ አጸዳሸ:: ከዓለማት ሴቶችም መካከል መረጠሸ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰمَرْيَمُ ٱقْنُتِى لِرَبِّكِ وَٱسْجُدِى وَٱرْكَعِى مَعَ ٱلرَّٰكِعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy43. «መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ:: ስገጂም:: ከአጎንባሾች ጋርም ሁነሽ አጎንብሺ።» (ያለበትን ታሪክ ለህዝቦችህ አውሳ።)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلْغَيْبِ نُوحِيهِ إِلَيْكَ وَمَا كُنتَ لَدَيْهِمْ إِذْ يُلْقُونَ أَقْلَٰمَهُمْ أَيُّهُمْ يَكْفُلُ مَرْيَمَ وَمَا كُنتَ لَدَيْهِمْ إِذْ يَخْتَصِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy44.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ታሪክ ወደ አንተ ከምናወርደው ከሩቅ ወሬ ነው:: መርየምን ማን እንደሚያሳድግ ብዕሮቻቸውን ለዕጣ በጣሉ ጊዜ አንተ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም:: በሚከራከሩም ጊዜ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَتِ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ يَٰمَرْيَمُ إِنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ ٱسْمُهُ ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَمِنَ ٱلْمُقَرَّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትም «መርየም ሆይ! አላህ ከእርሱ በሆነው ቃል የሚፈጠር ስሙ አል መሲህ ዒሳ የመርየም ልጅ በሚባል፤ በዚህ ዓለምም ሆነ በመጨረሻው ዓለም የተከበረና ከባለሟሎቹ አንዱ በሆነ ልጅ ያበስርሻል። (ባላት ጊዜ እዚያ ቦታ አልነበርክም) ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُكَلِّمُ ٱلنَّاسَ فِى ٱلْمَهْدِ وَكَهْلًا وَمِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. «እርሱም ገና በህፃንነቱ ካደገም በኋላ ሰዎችን ያነጋግራል:: ከመልካሞቹም አንዱ ነው።» (አላት)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌ قَالَ كَذَٰلِكِ ٱللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ إِذَا قَضَىٰٓ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

Amharic Translation - Africa Academy47. እርሷም «ጌታዬ ሆይ! ማንም ሰው በትዳርም ሆነ በዝሙት ሳይነካኝ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች:: መልአኩ ጅብሪልም አላት: «እነደዚሁ ነው። አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል። የአንድን ነገር መሆን በፈለገ ጊዜ የሚለው ‹ሁን› ብቻ ነው። ወዲያውኑም ያ ነገር ይሆናል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُعَلِّمُهُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy48. «ጽሕፈትንና ጥበብን፤ ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ أَنِّى قَدْ جِئْتُكُم بِـَٔايَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ أَنِّىٓ أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ ٱلطِّينِ كَهَيْـَٔةِ ٱلطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًۢا بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَأُبْرِئُ ٱلْأَكْمَهَ وَٱلْأَبْرَصَ وَأُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِى بُيُوتِكُمْ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy49.«ወደ ኢስራኢል ልጆችም መልዕክተኛ ያደርገዋል። ይላልም: ›, ‹እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዐምር መጣሁላችሁ:: እኔ ለእናንተ ከጭቃ የወፍ ቅርጽ አይነት እፈጥራለሁ:: በእርሱም እተነፍስበታለሁ:: ከዚያም በአላህ ፈቃድ ወፍ ይሆናል:: እውር ሆኖ የተወለደንም ለምጸኛንም በአላህ ፈቃድ አድናለሁ:: ሙታንንም በአላህ ፍቃድ አስነሳለሁ:: የምትበሉትንና በየቤቶቻችሁ የምታደልቡትን ሁሉ እነግራችኋለሁ:: (መረጃዎችን አገናዝባችሁ) የምታምኑ እንደሆናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ ግልጽ ተዐምር አለበት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَىَّ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَلِأُحِلَّ لَكُم بَعْضَ ٱلَّذِى حُرِّمَ عَلَيْكُمْ وَجِئْتُكُم بِـَٔايَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy50.«‹ከእኔ በፊት የነበረውን ተውራትን ያረጋገጥኩ ስሆን ያንም በእናንተ ላይ እርም የተደረገውን ነገር ከፊሉን ለእናንተ እፈቅድ ዘንድ መጣሁላችሁ:: ከጌታችሁም በሆነ ተዐምር መጣሁላችሁ:: አላህን ፍሩ:: እኔንም ታዘዙኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ هَٰذَا صِرَٰطٌ مُّسْتَقِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy51.«‹አላህ ጌታዬ የእናንተም ጌታችሁ ነው:: ስለዚህ በብቸኝነት ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛው መንገድ ነው።› ይላቸዋል»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy52. ዒሳ ከእነርሱ ክህደት በተሰማው ጊዜ፡- «ወደ አላህ የእኔ ረዳቶች የሚሆኑ እነማን ናቸው?» አለ:: ሀዋርያትም አሉ፡- «ዒሳ ሆይ! እኛ የአላህ ረዳቶች ነን:: በአላህ አምነናል:: ትክክለኛና ታዛዦች መሆናችንን መስክር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبَّنَآ ءَامَنَّا بِمَآ أَنزَلْتَ وَٱتَّبَعْنَا ٱلرَّسُولَ فَٱكْتُبْنَا مَعَ ٱلشَّٰهِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy53. («ጌታችን ሆይ! ባወረድከው አምነን መልዕክተኛውን ተከትለናል::( እኛንም ባንተ ብቸኛ አምላክነት በነብያት መልዕክተኛነት) ከመስካሪዎች ጋራ መዝግበን።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَكَرُوا۟ وَمَكَرَ ٱللَّهُ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy54.አይሁድም በዒሳ ላይ አደሙ:: አላህ ግን አድማቸውን አከሸፈባቸው። አላህ የአድመኞችን ሴራ በማክሸፍ ከሁሉ የበለጠ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَىَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَجَاعِلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوكَ فَوْقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ ثُمَّ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡- «ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጅህና ከምድር ወደ እኔ አንሽህ ነኝ:: ከነዚያም በእኔ ከካዱ ሰዎች (ተንኮል) አጥሪህ ነኝ። እነዚያ የተከተሉህንም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ:: ከዚያ የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ያን ትለያዩበት በነበራችሁበት ነገርም በመካከላችሁ እፈርዳለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَأُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy56.«እነዚያማ የካዱትን በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱ ቅጣትን እቀጣቸዋለሁ:: ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَيُوَفِّيهِمْ أُجُورَهُمْ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy57. እነዚያማ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩትን አላህ ምንዳቸውን ይሞላላቸዋል:: አላህም በዳዮችን አይወድምና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ نَتْلُوهُ عَلَيْكَ مِنَ ٱلْـَٔايَٰتِ وَٱلذِّكْرِ ٱلْحَكِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy58.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ተዓምራትና ጥበብን ከያዘው ተግሳጽ በአንተ ላይ የምናነበው ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

Amharic Translation - Africa Academy59. አላህ ዘንድ የዒሳ (ያለ አባት መፈጠሩ) ምሳሌው ልክ እንደ (ያለ አባትና ያለ እናት እንደተፈጠሩት አባታችን) አደም ቢጤ ነው:: አላህ ከአፈር ፈጠረውና ከዚያም «ሁን» አለው። ከዚያ ሰው ሆነ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْمُمْتَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy60.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነታው ከጌታህ ዘንድ የመጣልህ እውነት ነው። እናም ከተጠራጣሪዎች አትሁን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَنْ حَآجَّكَ فِيهِ مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ فَقُلْ تَعَالَوْا۟ نَدْعُ أَبْنَآءَنَا وَأَبْنَآءَكُمْ وَنِسَآءَنَا وَنِسَآءَكُمْ وَأَنفُسَنَا وَأَنفُسَكُمْ ثُمَّ نَبْتَهِلْ فَنَجْعَل لَّعْنَتَ ٱللَّهِ عَلَى ٱلْكَٰذِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy61.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውቀት ከመጣልህ በኋላ በእርሱ (በዒሳ) የተከራከሩህን «ኑ ልጆቻችንንና ልጆቻችሁን፣ ሴቶቻችንንና (ሚስቶቻችንና) ሴቶቻችሁን (ሚስቶቻችሁን)፣ ነፍሶቻችንንና ነፍሶቻችሁን እንጥራና ከዚያ አላህን እንለምን:: የአላህንም ቁጣ በውሸታሞች ላይ እናድርግ።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْقَصَصُ ٱلْحَقُّ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy62.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ እውነተኛው ታሪክ ነው:: ትክክለኛ አምላክም ከአላህ በስተቀር የለም። አላህም አሸናፊውና ጥበበኛው አምላክ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۢ بِٱلْمُفْسِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy63. (ከማመን) እምቢ ቢሉም (አጥፊዎቹ እነርሱ ናቸው።) አላህ አጥፊዎቹን (ከደህናዎቹ) ለይቶ አዋቂ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ تَعَالَوْا۟ إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَآءٍۭ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِۦ شَيْـًٔا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ ٱللَّهِ فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُولُوا۟ ٱشْهَدُوا۟ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy64.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ሆነችው ቃል ኑ። (እርሷም) ‹አላህን ብቻ እንጂ ሌላን ላንገዛ፤ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፤ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይዝ› ነው።» በላቸው። (ሙስሊሞች ሆይ!) እምቢ ካሉም «እኛ ሙስሊሞች መሆናችንን መስክሩ።» በሏቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تُحَآجُّونَ فِىٓ إِبْرَٰهِيمَ وَمَآ أُنزِلَتِ ٱلتَّوْرَىٰةُ وَٱلْإِنجِيلُ إِلَّا مِنۢ بَعْدِهِۦٓ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy65. እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በኢብራሂም (ዙሪያ) ለምን ትከራከራላችሁ? ተውራትና ኢንጂል ከእርሱ በኋላ እንጂ አልተወረዱ። ልብ አትሉምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰٓأَنتُمْ هَٰٓؤُلَآءِ حَٰجَجْتُمْ فِيمَا لَكُم بِهِۦ عِلْمٌ فَلِمَ تُحَآجُّونَ فِيمَا لَيْسَ لَكُم بِهِۦ عِلْمٌ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy66 እናንተ እነዚያ እውቀት ባላችሁ ነገር የተከራከራችሁ ናችሁ፡፡ ታዲያ እውቀት በሌላቸሁ ነገር ላይ ለምን ትከራከራላችሁ? አላህ ሁሉን ነገር ያውቃል። እናንተ ግን አታውቁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا كَانَ إِبْرَٰهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy67. ኢብራሂም አይሁድም ሆነ ክርስቲያን አልነበረም:: ግን በቀጥተኛው ሃይማኖት ቀጥ ያለ ሙስሊም ነበር:: ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ أَوْلَى ٱلنَّاسِ بِإِبْرَٰهِيمَ لَلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ وَهَٰذَا ٱلنَّبِىُّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَٱللَّهُ وَلِىُّ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy68.በኢብራሂም ይበልጥ ተገቢዎቹ እነዚያ የተከተሉት፤ ይህ ነብይ (ነብዩ ሙሐመድ) እና እነዚያ ያመኑት ብቻ ናቸው፡፡ አላህ የአማኞች ወዳጅ ነው፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَدَّت طَّآئِفَةٌ مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ لَوْ يُضِلُّونَكُمْ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy69. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከመጽሐፉ ባለቤቶች የተወሰኑት ነፍሶቻቸውን እንጂ የማያሳስቱ ሲሆኑ እናንተን ሊያሳስቷችሁ ተመኙ:: እራሳቸውን እንጂ ማንንም አያሳሳስቱም፡፡ እነርሱ ግን ይህንን እውነታ አያውቁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَكْفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَأَنتُمْ تَشْهَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! እናንተ የምታውቁ ስትሆኑ በአላህ አናቅጽ ለምን ትክዳላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy71. እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! እውነትን ከውሸት ጋር ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም የምታውቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَت طَّآئِفَةٌ مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ ءَامِنُوا۟ بِٱلَّذِىٓ أُنزِلَ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَجْهَ ٱلنَّهَارِ وَٱكْفُرُوٓا۟ ءَاخِرَهُۥ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy72. ከመጽሐፉ ባለቤቶች የሆኑ ቡድኖችም በዚያ ባመኑት ላይ በተወረደው ቁርኣን «በቀኑ መጀመሪያ ላይ እመኑበትና በቀኑ መጨረሻ ላይ ካዱ። እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تُؤْمِنُوٓا۟ إِلَّا لِمَن تَبِعَ دِينَكُمْ قُلْ إِنَّ ٱلْهُدَىٰ هُدَى ٱللَّهِ أَن يُؤْتَىٰٓ أَحَدٌ مِّثْلَ مَآ أُوتِيتُمْ أَوْ يُحَآجُّوكُمْ عِندَ رَبِّكُمْ قُلْ إِنَّ ٱلْفَضْلَ بِيَدِ ٱللَّهِ يُؤْتِيهِ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy73. (አሉም) «ሃይማኖታችሁን ለተከተለ እንጂ አትመኑም።» (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ትክክለኛው መመሪያ የአላህ መመሪያ ብቻ ነው። እናንተ ያገኛችሁትን እድል እንዳያገኙ ወይም በእርሱ ከጌታችሁ ፊት እንዳይሞግቷችሁ በመፍራት ነውን?» በላቸው። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ችሮታ በአላህ እጅ ብቻ ነው። ለሚፈልገውም ይሰጠዋል። አላህም ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነው።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِۦ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ ذُو ٱلْفَضْلِ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy74. በችሮታው የሚሻውን ይመርጣል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ مَنْ إِن تَأْمَنْهُ بِقِنطَارٍ يُؤَدِّهِۦٓ إِلَيْكَ وَمِنْهُم مَّنْ إِن تَأْمَنْهُ بِدِينَارٍ لَّا يُؤَدِّهِۦٓ إِلَيْكَ إِلَّا مَا دُمْتَ عَلَيْهِ قَآئِمًا ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَالُوا۟ لَيْسَ عَلَيْنَا فِى ٱلْأُمِّيِّـۧنَ سَبِيلٌ وَيَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy75. ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል በብዙ ገንዘብ ላይ ብታምነው ቅንጣት ሳያጎድል የሚመልስልህ አለ:: ከእነርሱም መካከል በአንድ ዲናር እንኳን ብታምነው ሁል ጊዜም እሱ ላይ የምትጠባበቅ ካልሆንክ በስተቀር የማይመልስልህም አለ:: ይህ «በመሀይማን ህዝቦች ላይ በምናደርገው በደል በእኛ ላይ የምንጠየቅበት መንገድ የለብንም።» ስለሚሉና እነርሱም እያወቁ በአላህ ላይ ውሸትን ስለሚናገሩ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلَىٰ مَنْ أَوْفَىٰ بِعَهْدِهِۦ وَٱتَّقَىٰ فَإِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy76 ጉዳዩ እነርሱ እንዳሉት አይደለም (ተጠያቂነት አለባቸው)። ያ በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀን ሁሉ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَشْتَرُونَ بِعَهْدِ ٱللَّهِ وَأَيْمَٰنِهِمْ ثَمَنًا قَلِيلًا أُو۟لَٰٓئِكَ لَا خَلَٰقَ لَهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ ٱللَّهُ وَلَا يَنظُرُ إِلَيْهِمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy77. እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሀላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋን የሚለውጡ ሁሉ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም እድል የላቸዉም:: በትንሳኤም ቀን አላህ አያነጋግራቸዉም:: ወደ እነርሱም አይመለከትም:: አያጸዳቸዉምም:: ከቶውንም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُۥنَ أَلْسِنَتَهُم بِٱلْكِتَٰبِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمَا هُوَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ ٱللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ ٱللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy78. ከእነርሱም መካከል ከመጽሐፉ ያልሆነን ነገር ከመጽሐፉ አካል መሆኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙም አሉ:: እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልመጣ (ያልወረደ) ሲሆን «ከአላህ ዘንድ የመጣ (የወረደ) ነው።» ይላሉ። የሚያውቁ ሲሆኑ በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ ٱللَّهُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحُكْمَ وَٱلنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا۟ عِبَادًا لِّى مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن كُونُوا۟ رَبَّٰنِيِّـۧنَ بِمَا كُنتُمْ تُعَلِّمُونَ ٱلْكِتَٰبَ وَبِمَا كُنتُمْ تَدْرُسُونَ

Amharic Translation - Africa Academy79. ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍን፣ ጥበብንና ነብይነትን ሰጥቶት ከዚያ ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሁኑ።» ሊል አይገባዉም:: ይልቁንም «መጽሐፉን የምታስተምሩና የምታጠኑ በነበራችሁበት በእውቀታችሁ ለራሳችሁ ተግባሪዎች ሁኑ።» ይላቸዋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يَأْمُرَكُمْ أَن تَتَّخِذُوا۟ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ أَرْبَابًا أَيَأْمُرُكُم بِٱلْكُفْرِ بَعْدَ إِذْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy80. መላዕክትንና ነብያትንም አማልክት አድርጋችሁ እንድትይዙ ሊያዛችሁ አይገባም:: (እናንተ) ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክህደት ያዛችኋልን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ لَمَآ ءَاتَيْتُكُم مِّن كِتَٰبٍ وَحِكْمَةٍ ثُمَّ جَآءَكُمْ رَسُولٌ مُّصَدِّقٌ لِّمَا مَعَكُمْ لَتُؤْمِنُنَّ بِهِۦ وَلَتَنصُرُنَّهُۥ قَالَ ءَأَقْرَرْتُمْ وَأَخَذْتُمْ عَلَىٰ ذَٰلِكُمْ إِصْرِى قَالُوٓا۟ أَقْرَرْنَا قَالَ فَٱشْهَدُوا۟ وَأَنَا۠ مَعَكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ

Amharic Translation - Africa Academy81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «መጽሐፍንና ጥበብን ሰጥቻችሁ ከዚያ ከናንተ ጋር ላለው መጽሀፍ የሚያረጋግጥ መልዕክተኛ ቢመጣላችሁ በእርሱ እንድታምኑበት እንድትረዱትም።» ሲል አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን በያዘ ጊዜ (የነበረውን ክስተት ለህዝቦችህ አስታውስ)። «አረጋገጣችሁን? በዚህስ ላይ ቃል ኪዳኔን ያዛችሁን?» አላቸው። እነርሱም «አዎ አረጋገጥን» አሉ። «እንግዲያውስ መስክሩ:: እኔም ከናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَن تَوَلَّىٰ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy82. እናም ከዚህ በኋላ የሸሹ አመጸኞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَغَيْرَ دِينِ ٱللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُۥٓ أَسْلَمَ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy83. በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለእርሱ የታዘዙና ወደ እርሱ የሚመለሱ ሲሆኑ (ከሓዲያን) ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَآ أُنزِلَ عَلَىٰٓ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطِ وَمَآ أُوتِىَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በአላህ አምነናል በእኛም ላይ በተወረደው በቁርኣን (በነብዩ) ኢብራሂም፣ (በነብዩ) ኢስማኢል፣ (በነብዩ) ኢስሀቅ፣ (በነብዩ) የዕቆብና በነገዶች ላይ በተወረደው፣ ለነብዩ ሙሳ ለነብዩ ዒሳና ለነብያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው ሁሉ አምነናል:: በእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም:: እኛ ለእርሱ ብቻ ታዛዦች ነን።» በል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy85. ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሁሉ ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይነት የለዉም:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ አንዱ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَيْفَ يَهْدِى ٱللَّهُ قَوْمًا كَفَرُوا۟ بَعْدَ إِيمَٰنِهِمْ وَشَهِدُوٓا۟ أَنَّ ٱلرَّسُولَ حَقٌّ وَجَآءَهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy86. ከእምነታቸውና መልዕክተኛዉም እውነት መሆኑን ከመሰከሩ፤ የተብራሩ አናቅጽም ከመጡላቸው በኋላ የካዱ ሕዝቦችን አላህ እንዴት ያቀናል? አላህ በዳዮችን ሕዝቦች አያቀናምና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ جَزَآؤُهُمْ أَنَّ عَلَيْهِمْ لَعْنَةَ ٱللَّهِ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلنَّاسِ أَجْمَعِينَ

Amharic Translation - Africa Academy87. እነዚያን መሰሎች ቅጣታቸው የአላህ፣ የመላዕክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በእነርሱ ላይ መውረዱ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يُخَفَّفُ عَنْهُمُ ٱلْعَذَابُ وَلَا هُمْ يُنظَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy88. በውስጧ ዘወታሪዎች ሲሆኑ ቅጣቱም ከእነርሱ ላይ አይቃለልላቸዉም:: ጊዜም አይሰጡም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُوا۟ مِنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy89. እነዚያ ከዚያ በኋላ ንስሀ የገቡና ስራቸውን ያሳመሩ ሁሉ ሲቀሩ፤ (አላህ እነዚህንማ ይምራቸዋል።) አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بَعْدَ إِيمَٰنِهِمْ ثُمَّ ٱزْدَادُوا۟ كُفْرًا لَّن تُقْبَلَ تَوْبَتُهُمْ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلضَّآلُّونَ

Amharic Translation - Africa Academy90. እነዚያ ከእምነታቸው በኋላ የካዱና ከዚያ ክህደትን በክህደት ላይ የጨመሩ ንሰሃቸው ፈጽሞ ተቀባይነት የለዉም:: የተሳሳቱ ማለት እነርሱው ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَمَاتُوا۟ وَهُمْ كُفَّارٌ فَلَن يُقْبَلَ مِنْ أَحَدِهِم مِّلْءُ ٱلْأَرْضِ ذَهَبًا وَلَوِ ٱفْتَدَىٰ بِهِۦٓ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy91. እነዚያ የካዱና በክህደታቸው ላይ እንዳሉ የሞቱ፤ ከእነርሱ አንዳቸው ምድርን የሞላ ወርቅ ቤዛ ቢያቀርብም እንኳ ፈጽሞ ተቀባይነት አያገኝም:: እነዚያ ለእነርሱ የሚያሰቃይ ቅጣት አለባቸው:: ለእነርሱም (ከዚህ ቅጣት) የሚያድኗቸው ምንም ረዳቶች የሏቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَن تَنَالُوا۟ ٱلْبِرَّ حَتَّىٰ تُنفِقُوا۟ مِمَّا تُحِبُّونَ وَمَا تُنفِقُوا۟ مِن شَىْءٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِهِۦ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy92. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከምትወዱት ነገር እስከምትለግሱ ድረስ የበጎ ስራን ዋጋ (ገነትን) አታገኙም:: ከምንም ነገር ብትለግሱም አላህ ያውቀዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كُلُّ ٱلطَّعَامِ كَانَ حِلًّا لِّبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ إِلَّا مَا حَرَّمَ إِسْرَٰٓءِيلُ عَلَىٰ نَفْسِهِۦ مِن قَبْلِ أَن تُنَزَّلَ ٱلتَّوْرَىٰةُ قُلْ فَأْتُوا۟ بِٱلتَّوْرَىٰةِ فَٱتْلُوهَآ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተውራት ከመውረዱ በፊት ኢስራኢል በራሱ ላይ እርም ካደረገው ነገር በስተቀር ምግብ ሁሉ ለኢስራኢል ልጆች የተፈቀደ ነበር። «እውነተኞች ከሆናችሁ እስኪ ተውራትን አምጡና አንብቡት።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ مِنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy94. ከዚህ በኋላ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጣጠፉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ብቻ በዳዮች (በደለኞች) ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ صَدَقَ ٱللَّهُ فَٱتَّبِعُوا۟ مِلَّةَ إِبْرَٰهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ እውነትን ተናገረ። (ትክክለኛ የኢብራሂም ወዳጆች ከሆናችሁ) የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን ተከተሉ። ከአጋሪዎችም አልነበረም።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِى بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy96. ለሰዎች (ማምለኪያ ይሆን ዘንድ በመሬት ላይ) በመጀመሪያ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ቤት (ካዕባ) ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهِ ءَايَٰتٌۢ بَيِّنَٰتٌ مَّقَامُ إِبْرَٰهِيمَ وَمَن دَخَلَهُۥ كَانَ ءَامِنًا وَلِلَّهِ عَلَى ٱلنَّاسِ حِجُّ ٱلْبَيْتِ مَنِ ٱسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِىٌّ عَنِ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy97. በውስጡ ግልጽ የሆኑ ተዐምራት አሉበት:: የኢብራሂምም መቆሚያ (የነበረው በዉስጡ አለ::) ወደ እርሱ የገባም ሁሉ ሰላም ይሆናል። በሰዎች ላይ ወደ እርሱ የመሄድን ጣጣ በቻለ ሁሉ ግዴታቸው ሲሆን ቤቱን ሊጎብኙት ለአላህ መብት አለው። በአላህ የካደ (ግን እራሱን እንጂ ማንንም አይጎዳም።) አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَكْفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ شَهِيدٌ عَلَىٰ مَا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy98.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! አላህ በምትሰሩት ሁሉ ላይ አዋቂ ሲሆን በአላህ ተዐምራቱ ለምን ትክዳላችሁ?» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ مَنْ ءَامَنَ تَبْغُونَهَا عِوَجًا وَأَنتُمْ شُهَدَآءُ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እናንተ መስካሪዎች ሆናችሁ ከአላህ መንገድ መጥመሟን የምትፈልጉ ስትሆኑ ያመነን ሰው ለምን ትከለክላላችሁ? አላህም ከምትሰሩት ነገር ላይ ሁሉ ዘንጊ አይደለም።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن تُطِيعُوا۟ فَرِيقًا مِّنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ يَرُدُّوكُم بَعْدَ إِيمَٰنِكُمْ كَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy100. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ መጽሐፍትን ከተሰጡ መካከል ከፊሎቹን ብትታዘዙ ከእምነታችሁ በኋላ ወደ ክህደት ይመልሷችኋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَيْفَ تَكْفُرُونَ وَأَنتُمْ تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ وَفِيكُمْ رَسُولُهُۥ وَمَن يَعْتَصِم بِٱللَّهِ فَقَدْ هُدِىَ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy101. የአላህ አናቅጽ በእናንተ ላይ እየተነበቡና መልዕክተኛዉም በመካከላችሁ እያለ እንዴት ትክዳላችሁ? በአላህ የሚጠበቅ ሰው ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ተመራ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِۦ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy102. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ትክክለኛውን ፍራቻ ፍሩት። እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ አትሙቱ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱعْتَصِمُوا۟ بِحَبْلِ ٱللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا۟ وَٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَآءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِۦٓ إِخْوَٰنًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ ٱلنَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy103. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የአላህን ጠንካራ የእምነት ገመድም ሁላችሁም ያዙ:: አትለያዩም። ጠበኞች በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋም አስታውሱ:: ይሀውም በልቦቻችሁ መካከል አስማማ በጸጋዉም ወንድማማቾች ሆናችሁ:: በእሳት ጉድጓድ አፋፍ ላይ የነበራችሁ ስትሆኑ ከእርሷም አዳናችሁ:: ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አናቅጽን እንደዚሁ ያብራራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلْتَكُن مِّنكُمْ أُمَّةٌ يَدْعُونَ إِلَى ٱلْخَيْرِ وَيَأْمُرُونَ بِٱلْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy104. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር የሚጠሩና በመልካም ስራ የሚያዙ፤ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ቡድኖች ይኑሩ:: እነዚያ ከእሳት የሚድኑ እነርሱው ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَكُونُوا۟ كَٱلَّذِينَ تَفَرَّقُوا۟ وَٱخْتَلَفُوا۟ مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ وَأُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy105. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እንደነዚያ ግልጽ ተዐምራት ከመጣላቸው በኋላ እንደተለያዩትና እንደተጨቃጨቁት የመጽሐፉ ባለቤት ሰዎች አትሁኑ:: እነዚያም ለነርሱ ታላቅ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ تَبْيَضُّ وُجُوهٌ وَتَسْوَدُّ وُجُوهٌ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ٱسْوَدَّتْ وُجُوهُهُمْ أَكَفَرْتُم بَعْدَ إِيمَٰنِكُمْ فَذُوقُوا۟ ٱلْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy106.ያን ፊቶች የሚያበሩበትና ፊቶች የሚጠቁሩበትን የትንሳኤን ቀን አስታውሱ። እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩት ወገኖች «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን? እግዲያዉስ ትክዱ የነበራችሁትን ነገር ቅጣቱን ቅመሱ።» ይባላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ ٱبْيَضَّتْ وُجُوهُهُمْ فَفِى رَحْمَةِ ٱللَّهِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy107. እነዚያ ፊቶቻቸው ያበሩት ወገኖች ደግሞ በአላህ ችሮታ ገነት ውስጥ ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘወታሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِٱلْحَقِّ وَمَا ٱللَّهُ يُرِيدُ ظُلْمًا لِّلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy108. እነኚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የአላህ አናቅጽ ናቸው:: አላህም ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرْجَعُ ٱلْأُمُورُ

Amharic Translation - Africa Academy109. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለ ሁሉ የአላህ ነው:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كُنتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ أُخْرِجَتْ لِلنَّاسِ تَأْمُرُونَ بِٱلْمَعْرُوفِ وَتَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَتُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَلَوْ ءَامَنَ أَهْلُ ٱلْكِتَٰبِ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُم مِّنْهُمُ ٱلْمُؤْمِنُونَ وَأَكْثَرُهُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy110. (ሙስሊሞች ሆይ!) ለሰው ልጆች ከተገለፁት ሕዝቦች ሁሉ በላጭ ሆናችሁ:: ይኸዉም በመልካም ነገር ታዛላችሁ:: ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ:: በአላህም አንድነት ታምናላችሁና ነው:: የመጽሐፉ ሰዎችም ልክ እንደናንተው ባመኑ ኑሮ ለእነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር። ከእነርሱ መካከል ትክክለኛ አማኞችም አሉ:: አብዛሀኞቻቸው ግን አመጸኞች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَن يَضُرُّوكُمْ إِلَّآ أَذًى وَإِن يُقَٰتِلُوكُمْ يُوَلُّوكُمُ ٱلْأَدْبَارَ ثُمَّ لَا يُنصَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy111 (ሙስሊሞች ሆይ!) ማስከፋትን እንጂ ፈጽሞ አይጎዷችሁም:: ቢዋጓችሁም ጀርባዎችን ያዞሩላችኋል (ይሸሻሉ)። ከዚያም በምንም ረዳት አያገኙም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ضُرِبَتْ عَلَيْهِمُ ٱلذِّلَّةُ أَيْنَ مَا ثُقِفُوٓا۟ إِلَّا بِحَبْلٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَحَبْلٍ مِّنَ ٱلنَّاسِ وَبَآءُو بِغَضَبٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَضُرِبَتْ عَلَيْهِمُ ٱلْمَسْكَنَةُ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَانُوا۟ يَكْفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَيَقْتُلُونَ ٱلْأَنۢبِيَآءَ بِغَيْرِ حَقٍّ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَوا۟ وَّكَانُوا۟ يَعْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy112. በየተገኙበት ስፍራ ከአላህ በሆነ ቃልኪዳን ወይም ከሰዎች በሆነ ቃል ኪዳን የተጠበቁ ካልሆኑ በስተቀር በእነርሱ ላይ ውርደት ተጽፎባቸዋል። ከአላህ በሆነ ቁጣ ተመለሱ። ድህነትም በእነርሱ ላይ ተፅፎባቸዋል። ይህ የሆነውም በአላህ ተዐምራት (አናቅጽ) ይክዱ፤ ነቢያትንም ያላ አግባብ ይገድሉ ስለነበሩ ነው:: ይህም የሆነው በማመፃቸውና ወሰንን ይተላለፉ ስለነበሩ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَيْسُوا۟ سَوَآءً مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ أُمَّةٌ قَآئِمَةٌ يَتْلُونَ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ ءَانَآءَ ٱلَّيْلِ وَهُمْ يَسْجُدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy113. የመጽሐፉ ባለቤቶች ሁሉ እኩል አይደሉም:: ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል ቀጥ ያሉና በሌሊት ሰዓቶች እየሰገዱ የአላህን አናቅጽ የሚያነቡ ሕዝቦችም አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَيَأْمُرُونَ بِٱلْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَيُسَٰرِعُونَ فِى ٱلْخَيْرَٰتِ وَأُو۟لَٰٓئِكَ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy114. በአላህና በመጨረሻዉም ቀን ያምናሉ:: በጽድቅም ነገር ያዛሉ:: ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ:: ለበጎ ስራዎችም ይጣደፋሉ:: እነርሱ ከደጋግ ሰዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا يَفْعَلُوا۟ مِنْ خَيْرٍ فَلَن يُكْفَرُوهُ وَٱللَّهُ عَلِيمٌۢ بِٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy115. ከበጎ የሚሰሩትን አይካዱም። (ውድቅ አይደረግባቸዉም::) አላህ ጥንቁቆቹን ሁሉ አዋቂ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَن تُغْنِىَ عَنْهُمْ أَمْوَٰلُهُمْ وَلَآ أَوْلَٰدُهُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا وَأُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy116. እነዚያ በአላህ የካዱት ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ ቅጣት ምንንም አያድኗቸዉም:: እነዚያም የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَثَلُ مَا يُنفِقُونَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا كَمَثَلِ رِيحٍ فِيهَا صِرٌّ أَصَابَتْ حَرْثَ قَوْمٍ ظَلَمُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ فَأَهْلَكَتْهُ وَمَا ظَلَمَهُمُ ٱللَّهُ وَلَٰكِنْ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy117. በዚህች በቅርቢቱ ሕይወት የሚለግሱት ነገር ምሳሌው በውስጧ ውርጭ ያለባት ነፋስ ነፍሶቻቸውን የበደሉን ሕዝቦች አዝመራ እንደነካችና እንዳጠፋች ብጤ ነው። አላህም አልበደላቸዉም። ግን እነርሱ ነፍሶቻቸውን በእራሳቸው የሚበድሉ ናቸው እንጂ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا۟ مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ ٱلْبَغْضَآءُ مِنْ أَفْوَٰهِهِمْ وَمَا تُخْفِى صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy118. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሚስጥረኛን (የልብ ወዳጅ) ከእናንተ ሌላ ከሆኑት አታድርጉ። የእናንተን ጉዳይ ከማበላሸት አይቦዝኑላችሁምና። ጉዳታችሁን ይወዳሉና (ይመኛሉ)። ለእናንተ ያላቸው ጥላቻ ከአፎቻቸው ላይ እንኳ ተገለጸ:: በልቦቻቸው የሚደብቁት ደግሞ ከዚህ ይበልጥ የከፋ ነው:: ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰٓأَنتُمْ أُو۟لَآءِ تُحِبُّونَهُمْ وَلَا يُحِبُّونَكُمْ وَتُؤْمِنُونَ بِٱلْكِتَٰبِ كُلِّهِۦ وَإِذَا لَقُوكُمْ قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَوْا۟ عَضُّوا۟ عَلَيْكُمُ ٱلْأَنَامِلَ مِنَ ٱلْغَيْظِ قُلْ مُوتُوا۟ بِغَيْظِكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

Amharic Translation - Africa Academy119. እናንተ ትወዷቸዋላችሁ:: እነርሱ ግን በፍጹም አይወዷችሁም:: እናንተ በሁሉም መጽሐፍት ታምናላችሁ:: እነርሱ ግን ባገኟችሁ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ:: ከናንተ ባገለሉ ጊዜ ግን ከቁጭታቸው የተነሳ በእናንተ ላይ ዐጥቆቻቸውን (ጣቶቻቸውን) ይነክሳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቁጭታችሁ ሙቱ። አላህ ልቦች የቋጠሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن تَمْسَسْكُمْ حَسَنَةٌ تَسُؤْهُمْ وَإِن تُصِبْكُمْ سَيِّئَةٌ يَفْرَحُوا۟ بِهَا وَإِن تَصْبِرُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ لَا يَضُرُّكُمْ كَيْدُهُمْ شَيْـًٔا إِنَّ ٱللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطٌ

Amharic Translation - Africa Academy120. ደግ ነገር ብታገኙ ይከፋቸዋል:: መጥፎ ነገር ቢደርስባችሁ ግን በሷ ይደሰታሉ:: ከታገሳችሁና አላህን ከፈራችሁ ተንኮላቸው ምንም አይጎዳችሁም:: አላህ ለሚሰሩት ሁሉ በዕውቀቱ ከባቢ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ غَدَوْتَ مِنْ أَهْلِكَ تُبَوِّئُ ٱلْمُؤْمِنِينَ مَقَٰعِدَ لِلْقِتَالِ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy121. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችን ለውጊያ ስፍራዎች የምታዘጋጅ ሆነህ ከቤተሰብህ በጧት በወጣህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ هَمَّت طَّآئِفَتَانِ مِنكُمْ أَن تَفْشَلَا وَٱللَّهُ وَلِيُّهُمَا وَعَلَى ٱللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy122. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ረዳታቸው ሲሆን ከእናንተ መካከል ሁለት ቡድኖች (ወገኖች) ለመፍራት ባሰቡ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በአላህ ላይ ብቻ አማኞች ይመኩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ نَصَرَكُمُ ٱللَّهُ بِبَدْرٍ وَأَنتُمْ أَذِلَّةٌ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy123. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በበድር ዘመቻ ዕለት እናንተ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ:: አላህን ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ تَقُولُ لِلْمُؤْمِنِينَ أَلَن يَكْفِيَكُمْ أَن يُمِدَّكُمْ رَبُّكُم بِثَلَٰثَةِ ءَالَٰفٍ مِّنَ ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ مُنزَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአማኞች (እንዲህ) በምትል ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «ጌታችሁ በሶስት ሺ መላዕክት የተወረዱ ሲሆኑ ቢረዳችሁ አይበቃችሁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلَىٰٓ إِن تَصْبِرُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ وَيَأْتُوكُم مِّن فَوْرِهِمْ هَٰذَا يُمْدِدْكُمْ رَبُّكُم بِخَمْسَةِ ءَالَٰفٍ مِّنَ ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ مُسَوِّمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy125. «አዎን! ብትታገሱና ብትጠነቀቁ አሁኑኑ በፍጥነት ጠላቶቻችሁ ቢመጡባችሁም ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላዕክት ይረዳችኋል።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا جَعَلَهُ ٱللَّهُ إِلَّا بُشْرَىٰ لَكُمْ وَلِتَطْمَئِنَّ قُلُوبُكُم بِهِۦ وَمَا ٱلنَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَكِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy126. አላህ ለእናንተ ብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ እንዲረኩ እንጂ እርዳታውን ለምንም አላደረገዉም:: ድልም አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ዘንድ ብቻ እንጂ ከሌላ ከማንም የሚገኝ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِيَقْطَعَ طَرَفًا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَوْ يَكْبِتَهُمْ فَيَنقَلِبُوا۟ خَآئِبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy127. (ድልን ያጎናፀፋችሁ) ከእነዚያ ከካዱት ከፊልን ሊቆርጥ (ሊያጠፋ) ወይም ሊያዋርዳቸውና ያፈሩ ሁነው እንዲመለሱ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَيْسَ لَكَ مِنَ ٱلْأَمْرِ شَىْءٌ أَوْ يَتُوبَ عَلَيْهِمْ أَوْ يُعَذِّبَهُمْ فَإِنَّهُمْ ظَٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ ራሳቸውን በዳዮች ናቸውና አላህ በእነርሱ ላይ ከፈለገም ይቅርታ ቢያደርግ ወይም በጥፋታቸው ቢቀጣቸውም ላንተ በነገሩ ላይ ምንም የለህም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ يَغْفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy129. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: ለፈለገው ሰው ይምራል:: የሚፈለገውን ሰው ይቀጣል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَأْكُلُوا۟ ٱلرِّبَوٰٓا۟ أَضْعَٰفًا مُّضَٰعَفَةً وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy130. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አራጣን የተነባበሩ እጥፎች ሲሆኑ አትብሉ:: ከገሀነም እሳት ትድኑም ዘንድ (አራጣን በመተው) አላህን ፍሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتَّقُوا۟ ٱلنَّارَ ٱلَّتِىٓ أُعِدَّتْ لِلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy131. ያችን ለከሓዲያን የተደገሰችውን የገሀነም እሳት ተጠንቀቁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy132.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَسَارِعُوٓا۟ إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy133. ወደ ጌታችሁ ምህረትና ስፋቷ ሰባቱ ሰማያትንና ምድርን ያክል ወደ ሆነችው ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትሆን ተቻኮሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِى ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلْكَٰظِمِينَ ٱلْغَيْظَ وَٱلْعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy134. ለእነዚያ በድሎትም ሆነ በችግር ጊዜ ለሚለግሱት፤ ቁጭትንም ገቺዎች፤ ለሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት፤ አላህ በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا۟ فَٰحِشَةً أَوْ ظَلَمُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا۟ ٱللَّهَ فَٱسْتَغْفَرُوا۟ لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ ٱلذُّنُوبَ إِلَّا ٱللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلُوا۟ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy135. ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኃጢአቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት ተደግሳለች:: ከአላህ ሌላ ኃጢአቶችን የሚምር ማን ነው? (አንድም የለም::) በስህተት በሰሩት ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት ሁሉ ተደግሳለች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ جَزَآؤُهُم مَّغْفِرَةٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَجَنَّٰتٌ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَنِعْمَ أَجْرُ ٱلْعَٰمِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy136. እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምህረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው:: የመልካም ሰሪዎች ሁሉ ምንዳ የሆነችው ገነት ምንኛ አማረች!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِكُمْ سُنَنٌ فَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَٱنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلْمُكَذِّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy137. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከእናንተ በፊት በእርግጥ ብዙ አልፈዋል። በምድር ላይ ሂዱና ያስተባባዮች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰذَا بَيَانٌ لِّلنَّاسِ وَهُدًى وَمَوْعِظَةٌ لِّلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy138. ይህ ቁርኣን ለሰዎች ሁሉ ማብራርያ፤ ለጥንቁቆችም መመሪያና ገሳጭ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَهِنُوا۟ وَلَا تَحْزَنُوا۟ وَأَنتُمُ ٱلْأَعْلَوْنَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy139. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ የበላዮች ናችሁና ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ አትድከሙ (አትስነፉ)። አትዘኑም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ ٱلْقَوْمَ قَرْحٌ مِّثْلُهُۥ وَتِلْكَ ٱلْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ ٱلنَّاسِ وَلِيَعْلَمَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَيَتَّخِذَ مِنكُمْ شُهَدَآءَ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy140. አማኞች ሆይ! የመቁስል ጉዳት ቢያገኛችሁ ሌሎች ህዝቦችም መሰሉ የመቁሰል ጉዳት አግኝቷቸዋል። እንዲሁ ቀናትን በሰዎች መካከል እናፈራርቃቸዋለን:: አላህ እነዚያን በትክክል በሱ ያመኑትን ሊለይና ከእናንተም መካከል ሰማዕታትን ሊመርጥ እንዲህ አይነት ቀናት እንዲፈራረቁ ያደርጋል:: አላህም በዳዮችን ሁሉ አይወድምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِيُمَحِّصَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَيَمْحَقَ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy141. አላህ እነዚያን በትክክል በእርሱ ያመኑትን ከኃጢአት ሊያጸዳና ከሓዲያንንም ሊያጠፋ ይህንን አደረገ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا۟ ٱلْجَنَّةَ وَلَمَّا يَعْلَمِ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ جَٰهَدُوا۟ مِنكُمْ وَيَعْلَمَ ٱلصَّٰبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy142. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) አላህ ከናንተ መካከል እነዚያን የታገሉትንና ታጋሾችን ሳይለይ ገነትን የምትገቡ መሰላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ كُنتُمْ تَمَنَّوْنَ ٱلْمَوْتَ مِن قَبْلِ أَن تَلْقَوْهُ فَقَدْ رَأَيْتُمُوهُ وَأَنتُمْ تَنظُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy143. በጦርነት ላይ መሞትን ሳታገኙት በፊት የምትመኙት ነበራችሁ:: እናንተም በአይናችሁ የምትመለከቱ ስትሆኑ በእርግጥ አያችሁት። (ታዲያ ለምን ሸሻችሁት?)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ أَفَإِي۟ن مَّاتَ أَوْ قُتِلَ ٱنقَلَبْتُمْ عَلَىٰٓ أَعْقَٰبِكُمْ وَمَن يَنقَلِبْ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ فَلَن يَضُرَّ ٱللَّهَ شَيْـًٔا وَسَيَجْزِى ٱللَّهُ ٱلشَّٰكِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy144. (መልዕክተኛችን) ሙሐመድ ከበፊቱ ብዙ መልዕክተኞች እንዳለፉት የሆነ መልዕክተኛ እንጂ አይደለም:: ታዲያ እሱ ቢሞት ወይ ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደ ኋላው የሚቀለበስም አላህን ምንም አይጎዳም:: አላህ አመስጋኞቹን ተገቢዉን ይመነዳልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ كِتَٰبًا مُّؤَجَّلًا وَمَن يُرِدْ ثَوَابَ ٱلدُّنْيَا نُؤْتِهِۦ مِنْهَا وَمَن يُرِدْ ثَوَابَ ٱلْـَٔاخِرَةِ نُؤْتِهِۦ مِنْهَا وَسَنَجْزِى ٱلشَّٰكِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy145. ማንኛዋም ነፍስ በተወሰነላት ጊዜ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትሞትም። የቅርቢቱን ዓለም ምንዳ የሚፈልግን ሁሉ ከእርሷ እንሰጠዋለን:: የመጨረሻይቱን ዓለም ምንዳ የሚፈልግንም ከእርሷ እንሰጠዋለን:: አመስጋኞችንም በእርግጥ ተገቢውን እንመነዳለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَأَيِّن مِّن نَّبِىٍّ قَٰتَلَ مَعَهُۥ رِبِّيُّونَ كَثِيرٌ فَمَا وَهَنُوا۟ لِمَآ أَصَابَهُمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَمَا ضَعُفُوا۟ وَمَا ٱسْتَكَانُوا۟ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلصَّٰبِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy146. ከነብያት ሊቃውንት ከእነሱ ጋር ሆነው የተዋጉ ብዙ አሉ። እናም በአላህ መንገድ ለሚደርስባቸው ነገር ምንም አልፈሩም:: አልደከሙም:: ለጠላት አልተዋረዱም:: አላህም ትዕግስተኞቹን ይወዳል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ قَوْلَهُمْ إِلَّآ أَن قَالُوا۟ رَبَّنَا ٱغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَإِسْرَافَنَا فِىٓ أَمْرِنَا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَٱنصُرْنَا عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy147. ንግግራቸዉም «ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንና በነገራችን ሁሉ ወሰን ማለፋችንን ማርልን። ጫማዎቻችንንም አደላድል:: በከሓዲያን ሕዝቦች ላይም እርዳን።» ማለታቸው እንጂ ሌላ አልነበረም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَـَٔاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ ثَوَابَ ٱلدُّنْيَا وَحُسْنَ ثَوَابِ ٱلْـَٔاخِرَةِ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy148. አላህ የቅርቢቱን ዓለም ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸው:: አላህ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ ይወዳልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن تُطِيعُوا۟ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يَرُدُّوكُمْ عَلَىٰٓ أَعْقَٰبِكُمْ فَتَنقَلِبُوا۟ خَٰسِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy149. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአላህ የካዱትን ብትታዘዙ ወደ ኋላችሁ ይመልሷችኋል። ከከሳሪዎቹም ትሆናላችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلِ ٱللَّهُ مَوْلَىٰكُمْ وَهُوَ خَيْرُ ٱلنَّٰصِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy150. ይልቁን አላህ ብቻ ረዳታችሁ ነው:: እርሱ ከረዳቶች ሁሉ በላጭ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَنُلْقِى فِى قُلُوبِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلرُّعْبَ بِمَآ أَشْرَكُوا۟ بِٱللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِۦ سُلْطَٰنًا وَمَأْوَىٰهُمُ ٱلنَّارُ وَبِئْسَ مَثْوَى ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy151. በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ አላህ በእሱ አስረጂ ያላወረደበትን ነገር በአላህ በማጋራታቸው ምክንያት ፍርሃትን እንጥላለን:: መኖሪያቸዉም የገሀነም እሳት ናት:: የበዳዮች መኖሪያ የሆነችው ገሀነምም መኖሪያነቷ ምን ትከፋ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ صَدَقَكُمُ ٱللَّهُ وَعْدَهُۥٓ إِذْ تَحُسُّونَهُم بِإِذْنِهِۦ حَتَّىٰٓ إِذَا فَشِلْتُمْ وَتَنَٰزَعْتُمْ فِى ٱلْأَمْرِ وَعَصَيْتُم مِّنۢ بَعْدِ مَآ أَرَىٰكُم مَّا تُحِبُّونَ مِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلدُّنْيَا وَمِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلْـَٔاخِرَةَ ثُمَّ صَرَفَكُمْ عَنْهُمْ لِيَبْتَلِيَكُمْ وَلَقَدْ عَفَا عَنكُمْ وَٱللَّهُ ذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy152. በእርግጥ አላህ በፈቃዱ ጠላቶቻችሁን በምትጨፈጭፏቸው ጊዜ ቃልኪዳንን በእርግጥ አረጋገጠላችሁ:: የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ፣ በትዕዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባመፃችሁም ጊዜ (ግን እርዳታውን ከለከላችሁ):: ከናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከናንተም ውስጥ የመጨርሻይቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከዚያም ሊሞክራችሁ ከእነርሱ አዞራችሁ:: በእርግጥም ለእናንተ ይቅርታ አደረገላችሁ:: አላህ ሁልጊዜም በአማኞች ላይ የችሮታ ባለቤት ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ تُصْعِدُونَ وَلَا تَلْوُۥنَ عَلَىٰٓ أَحَدٍ وَٱلرَّسُولُ يَدْعُوكُمْ فِىٓ أُخْرَىٰكُمْ فَأَثَٰبَكُمْ غَمًّۢا بِغَمٍّ لِّكَيْلَا تَحْزَنُوا۟ عَلَىٰ مَا فَاتَكُمْ وَلَا مَآ أَصَٰبَكُمْ وَٱللَّهُ خَبِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy153. (የመልዕክተኛችን ሙሐመድ ባልደረቦች ሆይ!) መልዕክተኛው ከኋላችሁ ሁኖ እየጠራችሁ የማትዞሩ ሆናችሁ በርቀት በምትሸሹ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: ባመለጣችሁ እድልና በደረሰባችሁም ነገር አለማዘንን ሊያስተምራችሁ በሀሳብ ላይ ሀሳብን አደረሰባችሁ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውሰጠ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَنزَلَ عَلَيْكُم مِّنۢ بَعْدِ ٱلْغَمِّ أَمَنَةً نُّعَاسًا يَغْشَىٰ طَآئِفَةً مِّنكُمْ وَطَآئِفَةٌ قَدْ أَهَمَّتْهُمْ أَنفُسُهُمْ يَظُنُّونَ بِٱللَّهِ غَيْرَ ٱلْحَقِّ ظَنَّ ٱلْجَٰهِلِيَّةِ يَقُولُونَ هَل لَّنَا مِنَ ٱلْأَمْرِ مِن شَىْءٍ قُلْ إِنَّ ٱلْأَمْرَ كُلَّهُۥ لِلَّهِ يُخْفُونَ فِىٓ أَنفُسِهِم مَّا لَا يُبْدُونَ لَكَ يَقُولُونَ لَوْ كَانَ لَنَا مِنَ ٱلْأَمْرِ شَىْءٌ مَّا قُتِلْنَا هَٰهُنَا قُل لَّوْ كُنتُمْ فِى بُيُوتِكُمْ لَبَرَزَ ٱلَّذِينَ كُتِبَ عَلَيْهِمُ ٱلْقَتْلُ إِلَىٰ مَضَاجِعِهِمْ وَلِيَبْتَلِىَ ٱللَّهُ مَا فِى صُدُورِكُمْ وَلِيُمَحِّصَ مَا فِى قُلُوبِكُمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

Amharic Translation - Africa Academy154. ከዚያም ከጭንቅ በኋላ ጸጥታን ከናንተ ከፊሎችን የሚሸፍንን እንቅልፍ በእናንተ ላይ አወረደ:: ከፊሎችንም ነፍሶቻቸው በእርግጥ አሳሰቧቸው:: እውነት ያልሆነውን የመሀይምነትን መጠራጠር በአላህ ላይ ይጠራጠራሉ:: «በነገሩ ላይ ምንም የመወሰን መብት አለን? (የለንም።») ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመወሰን መብት ሁሉ የአላህ ብቻ ነው።» በላቸው:: ላንተ ግልጽ የማያደርጉትን በልቦቻቸው ውስጥ ይደብቃሉ:: «የመወሰን መብት ቢኖረን ኖሮ በዚህ ቦታ ላይ ባልተገደልን ነበር» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቤታችሁ ውስጥ በሆናችሁም ኖሮ እነዚያ በእነርሱ ላይ መገደል የተጸፈባቸው ወደየመውደቂያቸው በወጡ ነበር።» በላቸው:: አላህ ፍርዱን ሊፈጽምና በደረቶቻችሁም ውስጥ ያለውን ሊፈትን በልቦቻችሁም ውስጥ ያለውን ነገር ሊገልጽ ይህንን ሰራ:: አላህ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር ሳይቀር አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ تَوَلَّوْا۟ مِنكُمْ يَوْمَ ٱلْتَقَى ٱلْجَمْعَانِ إِنَّمَا ٱسْتَزَلَّهُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ بِبَعْضِ مَا كَسَبُوا۟ وَلَقَدْ عَفَا ٱللَّهُ عَنْهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy155.(የመልዕክተኛችን ባልደረቦች ሆይ!) እነዚያ ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙ ቀን ከናንተ የሸሹትን ሰዎች በዚያ በሰሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸው ሰይጣን ነው:: አላህ ከእነርሱ በእርግጥ ይቅር ብሏል:: አላህ መሀሪና ለቅጣት የማይቸኩል ታጋሽ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَكُونُوا۟ كَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَقَالُوا۟ لِإِخْوَٰنِهِمْ إِذَا ضَرَبُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ أَوْ كَانُوا۟ غُزًّى لَّوْ كَانُوا۟ عِندَنَا مَا مَاتُوا۟ وَمَا قُتِلُوا۟ لِيَجْعَلَ ٱللَّهُ ذَٰلِكَ حَسْرَةً فِى قُلُوبِهِمْ وَٱللَّهُ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy156. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እነደነዚያ በአላህ እንደካዱትና ስለ ወንድሞቻቸው በምድር ላይ በተጓዙና ወይም ዘማቾች በሆኑ ጊዜ እኛ ዘንድ በነበሩ ኖሮ ባልሞቱ ባልተገደሉም ነበር እንደሚሉት ሰዎች አትሁኑ:: አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ጸጸት ያደርግባቸው ዘንድ ይህንን አሉ:: አላህ የፈለገውን ሕያው ያደርጋል:: የፈለገውን ይገድላልም:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَئِن قُتِلْتُمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ أَوْ مُتُّمْ لَمَغْفِرَةٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَرَحْمَةٌ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy157. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ስትዋጉ ብትገደሉ ወይም ብትሞቱ ከአላህ የሆነው ምህረትና እዝነት እነርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት ሁሉ የእናንተ ምንዳ በላጭ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَئِن مُّتُّمْ أَوْ قُتِلْتُمْ لَإِلَى ٱللَّهِ تُحْشَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy158. በጂሃድ ብትሞቱ ወይም ብትገደሉ ወደ አላህ ብቻ ትሰበሰባላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِمَا رَحْمَةٍ مِّنَ ٱللَّهِ لِنتَ لَهُمْ وَلَوْ كُنتَ فَظًّا غَلِيظَ ٱلْقَلْبِ لَٱنفَضُّوا۟ مِنْ حَوْلِكَ فَٱعْفُ عَنْهُمْ وَٱسْتَغْفِرْ لَهُمْ وَشَاوِرْهُمْ فِى ٱلْأَمْرِ فَإِذَا عَزَمْتَ فَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُتَوَكِّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy159. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ችሮታ ለዘብክላቸው:: አመለ መጥፎና ልበ ደረቅ በሆንክ ኖሮ ከአጠገብህ በተበተኑ ነበር:: ከእነርሱም ጥፋት ይቅር በል:: ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው:: በሁሉም ነገር ላይ አማክራቸው:: ከዚያ ቁርጥ ሀሳብ ባደረገክ ጊዜ በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: አላህ በእርሱ ላይ ብቻ ተመኪዎችን ይወዳልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن يَنصُرْكُمُ ٱللَّهُ فَلَا غَالِبَ لَكُمْ وَإِن يَخْذُلْكُمْ فَمَن ذَا ٱلَّذِى يَنصُرُكُم مِّنۢ بَعْدِهِۦ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy160. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከረዳችሁ እናንተን የሚያሸንፍ የለም:: እርሱ ካዋረዳቸሁ ደግሞ ከእርሱ ማዋረድ በኋላ የሚረዳችሁ ያ ማን ነው? አማኞች በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ لِنَبِىٍّ أَن يَغُلَّ وَمَن يَغْلُلْ يَأْتِ بِمَا غَلَّ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ ثُمَّ تُوَفَّىٰ كُلُّ نَفْسٍ مَّا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy161. የምርኮን ገንዘብ መደበቅ ከነብይ የሚሆን አይደለም። የምርኮን ገንዘብ የሚደብቅም በትንሳኤ ቀን የደበቀውን ነገር ተሸክሞ ይመጣል:: ከዚያ ነፍስ ሁሉ የስራዋን ዋጋ ትመነዳለች:: እነርሱም አይበደሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَمَنِ ٱتَّبَعَ رِضْوَٰنَ ٱللَّهِ كَمَنۢ بَآءَ بِسَخَطٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَمَأْوَىٰهُ جَهَنَّمُ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy162. የአላህን ውዴታ የተከተለ ሁሉ የአላህን ቁጣ እንዳተረፈና መኖሪያውም ገሀነም እንደሆነው ነውን? ገሀነም ማረፊያነቱ እጅግ ከፋ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُمْ دَرَجَٰتٌ عِندَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ بَصِيرٌۢ بِمَا يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy163. ሁሉም በአላህ ዘንድ ባለ ልዩ ልዩ ደረጃዎች ናቸው:: አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ يَتْلُوا۟ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِهِۦ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا۟ مِن قَبْلُ لَفِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy164. አላህ በአማኞች ላይ ከመካከላቸው የሆነን፤ በእነርሱም ላይ አናቅጽን የሚያነብ፤ ከርክሰት የሚያጠራቸው፤ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን መልዕክተኛ በላከላቸው ጊዜ በእርግጥ ለገሰላቸው:: እነርሱም ከዚያ በፊት ግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمَّآ أَصَٰبَتْكُم مُّصِيبَةٌ قَدْ أَصَبْتُم مِّثْلَيْهَا قُلْتُمْ أَنَّىٰ هَٰذَا قُلْ هُوَ مِنْ عِندِ أَنفُسِكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy165. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ያደረሳችሁትን ጥቃት ግማሽ በአገኛችሁ (በደረሰባችሁ) ጊዜ ይህ ከየት ነው የመጣብን አላችሁን? እርሱ ከነፍሶቻችሁ ዘንድ ነው:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَصَٰبَكُمْ يَوْمَ ٱلْتَقَى ٱلْجَمْعَانِ فَبِإِذْنِ ٱللَّهِ وَلِيَعْلَمَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy166. (የመልዕክተኛችን ባልደረቦች ሆይ!) ያ ሁለት ቡድኖች በተጋጠሙ ቀን የደረሰባችሁ በአላህ ፈቃድ ብቻ ነው:: የአማኞችን አቋም ሊፈትንና ማንነታቸውን ሊገልጽ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِيَعْلَمَ ٱلَّذِينَ نَافَقُوا۟ وَقِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا۟ قَٰتِلُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ أَوِ ٱدْفَعُوا۟ قَالُوا۟ لَوْ نَعْلَمُ قِتَالًا لَّٱتَّبَعْنَٰكُمْ هُمْ لِلْكُفْرِ يَوْمَئِذٍ أَقْرَبُ مِنْهُمْ لِلْإِيمَٰنِ يَقُولُونَ بِأَفْوَٰهِهِم مَّا لَيْسَ فِى قُلُوبِهِمْ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يَكْتُمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy167. እነዚያንም የነፈቁትንና «ኑ በአላህ መንገድ ተጋደሉ ወይም ተከላከሉ።» የተባሉትን ሊገልጽ ነው ይህን ያደረገው። አስመሳዮቹም «ውጊያን ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር።» አሉ:: እነርሱም ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው:: በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ። አላህም የሚደብቁትን ሁሉ አዋቂ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ قَالُوا۟ لِإِخْوَٰنِهِمْ وَقَعَدُوا۟ لَوْ أَطَاعُونَا مَا قُتِلُوا۟ قُلْ فَٱدْرَءُوا۟ عَنْ أَنفُسِكُمُ ٱلْمَوْتَ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy168. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ከትግል ወደ ኋላ የቀሩ ሲሆኑ ለወንድሞቻቸው «እኛን በታዘዙን ኖሮ ባልተገደሉ ነበር።» ያሉ ናቸው:: «እውነተኞችም ከሆናችሁ እስቲ ከነፍሶቻችሁ ላይ ሞትን ገፍትሩ።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَحْسَبَنَّ ٱلَّذِينَ قُتِلُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ أَمْوَٰتًۢا بَلْ أَحْيَآءٌ عِندَ رَبِّهِمْ يُرْزَقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy169. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሰማዕታት ሙታን አድርገህ አትገምታቸው:: በእርግጥ እነርሱ ጌታቸው ዘንድ ሕያው ናቸውና:: ከጌታቸው ዘንድም ሲሳይ ይለገሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَرِحِينَ بِمَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ وَيَسْتَبْشِرُونَ بِٱلَّذِينَ لَمْ يَلْحَقُوا۟ بِهِم مِّنْ خَلْفِهِمْ أَلَّا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy170. አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ተደሳቾች (ሲሆኑ ይመገባሉ):: በእነዚያም ከኋላቸው ገና ባልተከተሏቸውም (ባልሞቱትም እንደነርሱው ከተሰው) በእነርሱ ላይ ስጋትም ትካዜም የሌለባቸው ለመሆናቸው ይደሰታሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْتَبْشِرُونَ بِنِعْمَةٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَفَضْلٍ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy171. በአላህ ጸጋ፤ ችሮታና የአማኞችን ምንዳ የማያጠፋ በመሆኑም ይደሰታሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ ٱسْتَجَابُوا۟ لِلَّهِ وَٱلرَّسُولِ مِنۢ بَعْدِ مَآ أَصَابَهُمُ ٱلْقَرْحُ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا۟ مِنْهُمْ وَٱتَّقَوْا۟ أَجْرٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy172. እነዚያን የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው በኋላ ለአላህና ለመልዕክተኛው የታዘዙት ከእነርሱ መካከል በጎ ተግባርን ለሰሩና አላህንም ለፈሩት ሁሉ ታላቅ ምንዳ አለላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ قَالَ لَهُمُ ٱلنَّاسُ إِنَّ ٱلنَّاسَ قَدْ جَمَعُوا۟ لَكُمْ فَٱخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَٰنًا وَقَالُوا۟ حَسْبُنَا ٱللَّهُ وَنِعْمَ ٱلْوَكِيلُ

Amharic Translation - Africa Academy173. እነዚያም ሰዎች ለእነርሱ «ጠላቶች ለእናንተ ጦርን እንደገና አከማችተዋልና ፍሯቸው።» ያሏቸውና ይህም በእምነት ላይ እምነትን የጨመረላቸው ቃላቸዉም «በቂያችን አላህ ነው፤ እርሱም ምን ያምር መጠጊያ ነው!» ያሉ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱنقَلَبُوا۟ بِنِعْمَةٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَفَضْلٍ لَّمْ يَمْسَسْهُمْ سُوٓءٌ وَٱتَّبَعُوا۟ رِضْوَٰنَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ ذُو فَضْلٍ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy174. ከዚያም የአላህን ጸጋና ችሮታ ይዘው ምንም ክፉ ነገር ሳይነካቸው በሰላም ተመለሱ:: የአላህን ውዴታም ተከተሉ:: አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا ذَٰلِكُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ يُخَوِّفُ أَوْلِيَآءَهُۥ فَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy175. ይህ የሚያስፈራራችሁ ሰይጣን ብቻ ነው። ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል። (አማኞች ሆይ!) የሰይጣንን ወዳጆችን አትፍሯቸው:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁም እኔን ብቻ ፍሩኝ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يَحْزُنكَ ٱلَّذِينَ يُسَٰرِعُونَ فِى ٱلْكُفْرِ إِنَّهُمْ لَن يَضُرُّوا۟ ٱللَّهَ شَيْـًٔا يُرِيدُ ٱللَّهُ أَلَّا يَجْعَلَ لَهُمْ حَظًّا فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy176. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የእነዚያ ወደ ክህደት የሚቻኮሉ ሰዎች አድራጎት (ተግባር) አያሳዝንህ:: እነርሱ ፈጽሞ አላህን በምንም አይጎዱትምና:: አላህ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ እድልን ላያደርግ ይሻልና:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱشْتَرَوُا۟ ٱلْكُفْرَ بِٱلْإِيمَٰنِ لَن يَضُرُّوا۟ ٱللَّهَ شَيْـًٔا وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy177. እነዚያ ክህደትን በእምነት የለወጡ ክፍሎች ሁሉ አላህን በምንም ነገር ፈጽሞ አይጎዱትም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يَحْسَبَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَنَّمَا نُمْلِى لَهُمْ خَيْرٌ لِّأَنفُسِهِمْ إِنَّمَا نُمْلِى لَهُمْ لِيَزْدَادُوٓا۟ إِثْمًا وَلَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy178. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች ሁሉ እነርሱን ማዘግየታችንን ለነፍሶቻችን ደግ ነገር ነው ብለው አያስቡ:: እነርሱን የምናዘገያቸው ኃጢአትን እንዲጨምሩ ብቻ ነውና:: ለእነርሱም አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّا كَانَ ٱللَّهُ لِيَذَرَ ٱلْمُؤْمِنِينَ عَلَىٰ مَآ أَنتُمْ عَلَيْهِ حَتَّىٰ يَمِيزَ ٱلْخَبِيثَ مِنَ ٱلطَّيِّبِ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُطْلِعَكُمْ عَلَى ٱلْغَيْبِ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَجْتَبِى مِن رُّسُلِهِۦ مَن يَشَآءُ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَإِن تُؤْمِنُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ فَلَكُمْ أَجْرٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy179. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) አላህ መጥፎውን ከመልካሙ እስከሚለይ ድረስ አማኞችን እናንተ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ የሚተዋቸው አይደለም:: አላህም ሩቁን ነገር የሚያሳውቃችሁ አይደለም:: ግን አላህ ከመልዕክተኞቹ የሚሻውን ይመርጣል:: እናም በአላህና በመልዕክተኞቹም እመኑ:: ብታምኑና ብትጠነቀቁ ለእናንተ ታላቅ ምንዳ አለላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا يَحْسَبَنَّ ٱلَّذِينَ يَبْخَلُونَ بِمَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ هُوَ خَيْرًا لَّهُم بَلْ هُوَ شَرٌّ لَّهُمْ سَيُطَوَّقُونَ مَا بَخِلُوا۟ بِهِۦ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَلِلَّهِ مِيرَٰثُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy180. እነዚያ አላህ ከችሮታው ከሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ ሰዎች ንፉግነት ደግ ተግባር አይምሰላቸው:: ይልቁንም እርሱ ለእነርሱ መጥፎ ባህሪ ነው:: ያንን በእርሱ የነፈጉበት ገንዘብ በትንሳኤ ቀን (እባብ ሆኖ) በአንገታቸው ይጠለቃሉ:: የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّقَدْ سَمِعَ ٱللَّهُ قَوْلَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ فَقِيرٌ وَنَحْنُ أَغْنِيَآءُ سَنَكْتُبُ مَا قَالُوا۟ وَقَتْلَهُمُ ٱلْأَنۢبِيَآءَ بِغَيْرِ حَقٍّ وَنَقُولُ ذُوقُوا۟ عَذَابَ ٱلْحَرِيقِ

Amharic Translation - Africa Academy181. አላህ የእነዚያን «አላህ ድሃ ነው እኛ ግን ከበርቴዎች ነን።» ያሉትን ሰዎች ቃል በእርግጥ ሰማ:: ያንን ያሉትንና ነብያትን ያለ ህግ መግደላቸውንም በእርግጥ እንጽፋለን:: «የማቃጠልንም ስቃይ ቅመሱ።» እንላቸዋለን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيكُمْ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيْسَ بِظَلَّامٍ لِّلْعَبِيدِ

Amharic Translation - Africa Academy182. ያ ስቃይ እጃችሁ ባሳለፉት ስራና አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ عَهِدَ إِلَيْنَآ أَلَّا نُؤْمِنَ لِرَسُولٍ حَتَّىٰ يَأْتِيَنَا بِقُرْبَانٍ تَأْكُلُهُ ٱلنَّارُ قُلْ قَدْ جَآءَكُمْ رُسُلٌ مِّن قَبْلِى بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَبِٱلَّذِى قُلْتُمْ فَلِمَ قَتَلْتُمُوهُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy183. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ይህን ቃል የተናገሩት: «ለማንኛዉም መልዕክተኛ እሳት የምትበላው ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ በሱ እንዳናምን አላህ ወደ እኛ አዝዟል።» ያሉ ናቸው:: «ብዙ መልዕክተኞች ከእኔ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በዚያ ባላችሁት ቁርባን በእርግጥ መጥተውላችኋል:: እውነተኞች ከሆናችሁ ታዲያ ለምን ገደላቸኃቸው?» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِن كَذَّبُوكَ فَقَدْ كُذِّبَ رُسُلٌ مِّن قَبْلِكَ جَآءُو بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلْمُنِيرِ

Amharic Translation - Africa Academy184. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊትም በግልጽ ተዐምራት፣ በጽሁፎች፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡ መልዕክተኞችም በእርግጥ (በእነርሱ መሰሎች) ተስተባብለዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كُلُّ نَفْسٍ ذَآئِقَةُ ٱلْمَوْتِ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ ٱلنَّارِ وَأُدْخِلَ ٱلْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ وَمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَآ إِلَّا مَتَٰعُ ٱلْغُرُورِ

Amharic Translation - Africa Academy185. ነፍስ ሁሉ ሞትን በእርግጥ ቀማሽ ናት:: ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሳኤ ቀን ብቻ ነው:: ከእሳት እንዲርቅ ተደርጎ ገነት እንዲገባ የተደረገም በእርግጥ ምኞቱን አገኘ:: የቅርቢቱ ሕይወት ማታለያ እንጂ ሌላ አይደለችም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَتُبْلَوُنَّ فِىٓ أَمْوَٰلِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ وَلَتَسْمَعُنَّ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ وَمِنَ ٱلَّذِينَ أَشْرَكُوٓا۟ أَذًى كَثِيرًا وَإِن تَصْبِرُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ فَإِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ ٱلْأُمُورِ

Amharic Translation - Africa Academy186. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ትፈተናላችሁ:: ከእነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትም ከእነዚያ በአላህ ካጋሩትም ቡድኖች ብዙ መጥፎ ነገሮችን ትሰማላችሁ:: ብትታገሱና ብትጠነቀቁ (በጣም ጥሩ ነው።) ይህ ተግባር ከታላላቅ ነገሮች አንዱ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ لَتُبَيِّنُنَّهُۥ لِلنَّاسِ وَلَا تَكْتُمُونَهُۥ فَنَبَذُوهُ وَرَآءَ ظُهُورِهِمْ وَٱشْتَرَوْا۟ بِهِۦ ثَمَنًا قَلِيلًا فَبِئْسَ مَا يَشْتَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy187. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የእነዚያ መጽሐፍን የተሰጡትን ለሰዎች በእርግጥ «ልታብራሩት እንጂ ላትደብቁት» በማለት የያዘባቸውን ቃል ኪዳን አስታውስ:: እናም በጀርባዎቻቸው በኋላ ወረወሩት:: በእርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙበት:: የሚገዙትም ነገር ከፋ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا تَحْسَبَنَّ ٱلَّذِينَ يَفْرَحُونَ بِمَآ أَتَوا۟ وَّيُحِبُّونَ أَن يُحْمَدُوا۟ بِمَا لَمْ يَفْعَلُوا۟ فَلَا تَحْسَبَنَّهُم بِمَفَازَةٍ مِّنَ ٱلْعَذَابِ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy188. እነዚያን በሰሩት ነገር የሚደሰቱና ባልሰሩትም መመስገንን የሚወዱ ሰዎችን ከቅጣት በመዳን ላይ ናቸው ብለህ አታስባቸው:: ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy189. የሰማያትና የምድር ንግስና ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى خَلْقِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفِ ٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ لَـَٔايَٰتٍ لِّأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ

Amharic Translation - Africa Academy190. በሰማያትና በምድር መፈጠር፤ በሌሊትና በቀንም መተካካት ለባለ አእምሮዎች ሁሉ ታላላቅ ምልክቶች አሉት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَذْكُرُونَ ٱللَّهَ قِيَٰمًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِى خَلْقِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَٰذَا بَٰطِلًا سُبْحَٰنَكَ فَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy191. እነርሱም እነዚያ ቆመው ተቀምጠዉም በጎኖቻቸው ተጋድመዉም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑና (እንዲህም) የሚሉ ናቸው: «ጌታችን ሆይ! ይህን በከንቱ አልፈጠርከዉም ጥራት ይገባህ:: ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبَّنَآ إِنَّكَ مَن تُدْخِلِ ٱلنَّارَ فَقَدْ أَخْزَيْتَهُۥ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

Amharic Translation - Africa Academy192. «ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታስገባው ሰው ሁሉ በእርግጥ አዋረድከው:: ለበደለኞች ምንም ረዳቶች የሏቸዉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَّبَّنَآ إِنَّنَا سَمِعْنَا مُنَادِيًا يُنَادِى لِلْإِيمَٰنِ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِرَبِّكُمْ فَـَٔامَنَّا رَبَّنَا فَٱغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّـَٔاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ ٱلْأَبْرَارِ

Amharic Translation - Africa Academy193. «ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማንና ወዲያዉኑ አመንም::ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ማርልን ክፉ ስራዎቻችንንም አብስልን:: ከንጹሆች ሰዎች ጋርም ግደለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبَّنَا وَءَاتِنَا مَا وَعَدتَّنَا عَلَىٰ رُسُلِكَ وَلَا تُخْزِنَا يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ إِنَّكَ لَا تُخْلِفُ ٱلْمِيعَادَ

Amharic Translation - Africa Academy194. «ጌታችን ሆይ! በመልዕክተኞቹ አማካኝነት የሰጠኸንን፤ የገባህልንን የተስፋ ቃል ስጠን:: በትንሳኤ ቀንም አታዋርደን:: (አታሳፍረን::) አንተ ቀጠሮን አታፈርስምና።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱسْتَجَابَ لَهُمْ رَبُّهُمْ أَنِّى لَآ أُضِيعُ عَمَلَ عَٰمِلٍ مِّنكُم مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ بَعْضُكُم مِّنۢ بَعْضٍ فَٱلَّذِينَ هَاجَرُوا۟ وَأُخْرِجُوا۟ مِن دِيَٰرِهِمْ وَأُوذُوا۟ فِى سَبِيلِى وَقَٰتَلُوا۟ وَقُتِلُوا۟ لَأُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّـَٔاتِهِمْ وَلَأُدْخِلَنَّهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ ثَوَابًا مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ عِندَهُۥ حُسْنُ ٱلثَّوَابِ

Amharic Translation - Africa Academy195. እናም ጌታቸው «እኔ ከናንተ ውስጥ የወንድንም ሆነ የሴትን መልካም ስራ ወሮታ አላጠፋም:: ከፊላችሁ የከፊሉ አካል ነው።» በማለት ልመናቸውን ተቀበላቸው:: እነዚያ ለዲን ሲሉ የተሰደዱ፣ ከአገሮቻቸዉም በግፍ የተባረሩ፣ በመንገዴም (ሁከት የደረሰባቸው)፣ የተጠቁ፣ የተጋደሉ እና የተገደሉም ክፉ ስራዎቻቸውን አብስላቸዋለሁ:: በስሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሰባቸውን ገነቶች አስገባቸዋለሁ:: እነርሱም ከአላህ ዘንድ የሆነን ከፍተኛ ምንዳ ይመነዳሉ:: አላህ እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አለና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَغُرَّنَّكَ تَقَلُّبُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فِى ٱلْبِلَٰدِ

Amharic Translation - Africa Academy196. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የእነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች በየአገሮች መንፈላሰስ አያታልህ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَتَٰعٌ قَلِيلٌ ثُمَّ مَأْوَىٰهُمْ جَهَنَّمُ وَبِئْسَ ٱلْمِهَادُ

Amharic Translation - Africa Academy197. አነስተኛ ጥቅም ነው። ከዚያ መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ገሀነም ደግሞ ማረፊያነቷ ምን ትከፋ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَٰكِنِ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ رَبَّهُمْ لَهُمْ جَنَّٰتٌ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا نُزُلًا مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيْرٌ لِّلْأَبْرَارِ

Amharic Translation - Africa Academy198. እነዚያ ጌታቸውን የፈሩት ግን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ዘወታሪዎች ሲሆኑ አላህ ዘንድ የተሰጡ መስተንግዶዎች አሏቸው:: አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለበጎ ሰሪዎች ሁሉ በላጭ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ لَمَن يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِمْ خَٰشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ

Amharic Translation - Africa Academy199. ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል አላህን ፈሪዎችና በአላህ አናቅጽም ጥቂትን ዋጋ የማይለውጡ ሲሆኑ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው ቁርኣን በዚያም ወደ እነርሱ በተወረዱት ልዩ ልዩ መጽሐፍት የሚያምኑ ሰዎች አሉ:: እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ተገቢው ምንዳቸው አለላቸው አላህ ምርመራው ፈጣን ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱصْبِرُوا۟ وَصَابِرُوا۟ وَرَابِطُوا۟ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy200. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእሳት ቅጣት ትድኑ ዘንድ ታገሱ፣ ተበራቱም፣ በጦር ኬላ ላይ ሆናችሁም ሶላትን ተጠባበቁ:: አላህንም በትክክል ፍሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70