وَءَامِنُوا۟ بِمَآ أَنزَلْتُ مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَكُمْ وَلَا تَكُونُوٓا۟ أَوَّلَ كَافِرٍۭ بِهِۦ وَلَا تَشْتَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِى ثَمَنًا قَلِيلًا وَإِيَّٰىَ فَٱتَّقُونِ
Amharic Translation - Africa Academy41. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከናንተ ጋር ያለውን መጽሐፍ እውቅና የሚሰጥ ሆኖ ባወረድኩት (ቁርኣን) እመኑ:: በእርሱም የመጀመሪያ ከሓዲያን አትሁኑ:: በአንቃጾቼ ጥቂት ገንዘብ አትለውጡ:: እኔንም ብቻ ፍሩኝ፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከናንተ ጋር ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም (ቁርኣን) እመኑ፡፡ በርሱም የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ፡፡ በአንቀጾቼም ጥቂትን ዋጋ አትለውጡ፡፡ እኔንም ብቻ ተጠንቀቁ፡፡