caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 74

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:74

ثُمَّ قَسَتْ قُلُوبُكُم مِّنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ فَهِىَ كَٱلْحِجَارَةِ أَوْ أَشَدُّ قَسْوَةً وَإِنَّ مِنَ ٱلْحِجَارَةِ لَمَا يَتَفَجَّرُ مِنْهُ ٱلْأَنْهَٰرُ وَإِنَّ مِنْهَا لَمَا يَشَّقَّقُ فَيَخْرُجُ مِنْهُ ٱلْمَآءُ وَإِنَّ مِنْهَا لَمَا يَهْبِطُ مِنْ خَشْيَةِ ٱللَّهِ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy74. ከዚያም ልቦቻቸው ከዚህ (ትዕይንት) በኋላ ደረቁ:: እርሷም በድርቅና እንደ አለት ድንጋዩች ወይም ከእርሱ ይበልጥ የበረቱ ናቸው:: ምክንያቱም ከድንጋዩች መካከል ጅረቶች (ወንዞች) የሚፈሱበት፤ ከእነርሱም የሚሰነጥቅና ከእርሱ ውሃ ምንጭ የሚወጣው፤ ከእነርሱም አላህን ከመፍራቱ የተነሳ ወደ ታች የሚወርድ አለና:: አላህ ከምትሰሩት ነገር ሁሉ ከአንዱም ዘንጊ አይደለም፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከዚያም ከዚህ በኋላ ልቦቻችሁ ደረቁ፤ እርሷም እንደ ድንጋዮች ወይም በድርቅና ይበልጥ የበረታች ናት፡፡ ከድንጋዮችም ከርሱ ጂረቶች የሚፈሱለት አልለ፡፡ ከነርሱም በእርግጥ የሚሰነጠቅና ከርሱ ውሃ (ምንጭ) የሚወጣው አልለ፡፡ ከነርሱም አላህን ከመፍራት የተነሳ ወደ ታች የሚወርድ አልለ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ነገር ዘንጊ አይደለም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70