وَإِذْ قَالَ إِبْرَٰهِـۧمُ رَبِّ أَرِنِى كَيْفَ تُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ قَالَ أَوَلَمْ تُؤْمِن قَالَ بَلَىٰ وَلَٰكِن لِّيَطْمَئِنَّ قَلْبِى قَالَ فَخُذْ أَرْبَعَةً مِّنَ ٱلطَّيْرِ فَصُرْهُنَّ إِلَيْكَ ثُمَّ ٱجْعَلْ عَلَىٰ كُلِّ جَبَلٍ مِّنْهُنَّ جُزْءًا ثُمَّ ٱدْعُهُنَّ يَأْتِينَكَ سَعْيًا وَٱعْلَمْ أَنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy260. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ እስቲ አሳየኝ» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውስ:: አላህ፡- «አላመንክምን?» አለው:: ኢብራሂምም «በፍጹም (አይደለም) አምኛለሁ:: ግን ልቤ ሙሉ በሙሉ እንዲረጋጋ ነው።» አለው:: አላህም፡- «አራት ወፎችን ያዝና ወደ አንተ ሰብስባቸው:: ከዚያ ቆራርጣቸው:: ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከእነርሱ ቁራጭ ቁራጭ አካላቸውን አስቀምጥ:: ከዚያም ጥራቸው በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ:: አላህ አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቅ።» አለው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqኢብራሂምም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ አሳየኝ» ባለ ጊዜ (አስታውስ፡፡) አላህ ፡- «አላመንክምን» አለው፡፡ «አይደለም (አምኛለሁ)፤ ግን ልቤ እንዲረጋ» ነው አለ፡፡ (አላህም)፡- «ከበራሪዎች (ከወፎች) አራትን ያዝ፡፡ ወደ አንተም ሰብስባቸው፡፡ (ቆራርጣቸውም)፤ ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከነርሱ ቁራጭን አድርግ፡፡ ከዚያም ጥራቸው፤ ፈጥነው ይመጡሃልና፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ መኾኑን ዕወቅ» አለው፡፡