يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْخَمْرِ وَٱلْمَيْسِرِ قُلْ فِيهِمَآ إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَٰفِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَآ أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا وَيَسْـَٔلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ ٱلْعَفْوَ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy219. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዕምሮን ስለሚያሰክር መጠጥና ስለ ቁማር ይጠይቁሃል:: «በሁለቱም ትልቅ ኃጢአትነትና ለሰዎችም ጥቅም አለባቸው:: ኃጢአታቸው ግን ከጥቅማቸው በጣም የገዘፈ ነው።» በላቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምንን እንደሚመጸውቱም (መጠኑን) ይጠይቁሀል:: «የተረፋችሁን መጽውቱ።» በላቸው:: እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአእምሮን ከሚቃወም መጠጥና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው፡፡ ምንን እንደሚመጸውቱም (መጠኑን) ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን (መጽውቱ)» በላቸው፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡