فَمَنْ خَافَ مِن مُّوصٍ جَنَفًا أَوْ إِثْمًا فَأَصْلَحَ بَيْنَهُمْ فَلَآ إِثْمَ عَلَيْهِ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy182. ከተናዛዥም በኩል (ከእውነት) መዘንበልን ወይም (ከሲሶ የመጨመር) ኃጢአትን የፈራ (ያወቀ) ከዚያም በመካከላቸው ያስታረቀ በእርሱ ላይ ምንም ኃጢአት የለበትም:: አላህ በጣም መሀሪና በጣም አዛኝ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከተናዛዢም በኩል (ከውነት) መዘንበልን ወይም (ከሢሶ በመጨመር) ኃጢኣትን ያወቀና በመካከላቸው ያስታረቀ ሰው በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፡፡ አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡