قُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَآ أُنزِلَ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطِ وَمَآ أُوتِىَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَآ أُوتِىَ ٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy136. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) «በአላህና ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሀቅም፣ ወደ የዕቁብና ወደ ነገዶችም በተወረደው መለኮታዊ መልዕክት ሁሉ በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት፤ በዚያም ነብያት ሁሉ ከጌታቸው በተለገሱት ከእነርሱ አንዱን ከሌላው የማንለይ ስንሆን አመንን:: እኛም (ለአላህ) ፍጹም ታዛዦች ነን።» በሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርኣን) ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ (ለአላህ) ታዛዦች ነን» በሉ፡፡