ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِۦ وَقَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy285. መልዕክተኛው (ሙሐመድ) ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደለት (ቁርኣን) አምኗል:: አማኞችም እንደዚሁ አመኑ:: ሁሉም በአላህ፣ በመልዕክቱ፣ በመጽሐፉትና በመልዕክተኞቹ «ከእነርሱ በአንዱም መካከል አንለይም (አንክድም)» የሚሉ ሲሆኑ አመኑ:: «የአላህን ትዕዛዛትንም ሰማን ታዘዝንም። ጌታችን ሆይ! ምህረትህን እንሻለን :: የሁሉም መመለሻ ወደ አንተው ብቻ ነው። አሉም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም (እንደዚሁ)፡፡ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም፣ ከመልክተኞቹ «በአንድም መካከል አንለይም» (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ፡፡ «ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)፡፡ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው» አሉም፡: