وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّى جَاعِلٌ فِى ٱلْأَرْضِ خَلِيفَةً قَالُوٓا۟ أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ ٱلدِّمَآءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ قَالَ إِنِّىٓ أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ለመላዕክት «እኔ በምድር ላይ (ምትክ) ወኪል ላደርግ ነው።» ባለ ጊዜ (የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ)። «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ፤ የምናሞግስህ ስንሆን በምድር ውስጥ የሚያጠፉትንና ደሞችንም የሚያፈሱትን ታደርጋለህን?» አሉ:: አላህም «እኔ እናንተ የማታውቁትን ነገር ሁሉ አውቃለሁ» አላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ሙሐመድ ሆይ) ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ፤ እነርሱም) «በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን?» አሉ፡፡ (አላህ) «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡