أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلْمَلَإِ مِنۢ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ مِنۢ بَعْدِ مُوسَىٰٓ إِذْ قَالُوا۟ لِنَبِىٍّ لَّهُمُ ٱبْعَثْ لَنَا مَلِكًا نُّقَٰتِلْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ قَالَ هَلْ عَسَيْتُمْ إِن كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلْقِتَالُ أَلَّا تُقَٰتِلُوا۟ قَالُوا۟ وَمَا لَنَآ أَلَّا نُقَٰتِلَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَقَدْ أُخْرِجْنَا مِن دِيَٰرِنَا وَأَبْنَآئِنَا فَلَمَّا كُتِبَ عَلَيْهِمُ ٱلْقِتَالُ تَوَلَّوْا۟ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌۢ بِٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy246. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስራኢል ልጆች ከሙሳ ዘመን በኋላ ወደ ነበሩት የቤተ-ኢስራኢል ቅምጥሎች ተልኮላቸው ለነበረው ለነብያቸው «ለእኛ ንጉስን ሹምልን እና በአላህ መንገድ እንዋጋ።» ባሉ ጊዜ የሆነውን አላየህምን? እሱም «መዋጋት ቢፃፍባችሁ አትዋጉ ይሆናል።» አላቸው:: እነርሱም «ከአገሮቻችንና ከልጆቻችን ተባረን ሳለ በአላህ መንገድ የማንዋጋበት ምን ምክንያት አለን?» አሉ:: በእነርሱ ላይ መዋጋት በተፃፈባቸው ጊዜ ግን ከእነርሱ ጥቂቶች ሲቀሩ ከመዋጋት አፈገፈጉ:: አላህ አጥፊዎችን ሁሉ በሚገባ ያውቃቸዋል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከእስራኤል ልጆች ከሙሳ በኋላ ወደ ነበሩት ጭፍሮች ለነቢያቸው (ለሳሙኤል)፡- «ለእኛ ንጉሥን አስነሳልን በአላህ መንገድ እንዋጋለን፤» ባሉ ጊዜ አላየህምን? (አላወቅህምን?)፡-«መዋጋት ቢጻፍባችሁ አትዋጉም ይኾናል» አላቸው፡፡ «ከሀገሮቻችንና ከልጆቻችን የተባረርን ስንኾን በአላህ መንገድ የማንዋጋ ለእኛ ምን አለን?» አሉ፡፡ በእነርሱ ላይ መዋጋት በተጻፈባቸውም ጊዜ ከእነርሱ ጥቂቶች ሲቀሩ አፈገፈጉ፡፡ አላህም በዳዮቹን ዐዋቂ ነው፡፡