فَإِن طَلَّقَهَا فَلَا تَحِلُّ لَهُۥ مِنۢ بَعْدُ حَتَّىٰ تَنكِحَ زَوْجًا غَيْرَهُۥ فَإِن طَلَّقَهَا فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَآ أَن يَتَرَاجَعَآ إِن ظَنَّآ أَن يُقِيمَا حُدُودَ ٱللَّهِ وَتِلْكَ حُدُودُ ٱللَّهِ يُبَيِّنُهَا لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy230. ከዚያም ለሶስተኛ ጊዜ ከፈታት በኋላ ሌላን ባል እስካላገባች (ከዚያም እስካልተፈታች ወይም እስካልሞተባት) ድረስ ለእርሱ አትፈቀደለትም:: ሁለተኛው ባል ከፈታት የአላህን ሕግጋት እንደሚጠብቁ ተስፋ ካደረጉ በመማለሳቸው በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለባቸውም:: እነኚህ የአላህ ሕግጋት ናቸው:: ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ ያብራራላቸዋል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ሦስተኛ) ቢፈታትም ከዚህ በኋላ ሌላን ባል እስከምታገባ ድረስ ለርሱ አትፈቀድለትም፡፡ (ሁለተኛው ባል) ቢፈታትም የአላህን ሕግጋት መጠበቃቸውን ቢያውቁ በመማለሳቸው በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለባቸውም፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት ለሚያውቁ ሕዝቦች ያብራራታል፡፡