يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْأَهِلَّةِ قُلْ هِىَ مَوَٰقِيتُ لِلنَّاسِ وَٱلْحَجِّ وَلَيْسَ ٱلْبِرُّ بِأَن تَأْتُوا۟ ٱلْبُيُوتَ مِن ظُهُورِهَا وَلَٰكِنَّ ٱلْبِرَّ مَنِ ٱتَّقَىٰ وَأْتُوا۟ ٱلْبُيُوتَ مِنْ أَبْوَٰبِهَا وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy189. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለለጋ ጨረቃ መለዋወጥ ይጠይቁሃል። «ይህ ክስተት ሰዎች ጊዜን ለመለካት የሚጠቀሙበትና የሐጅንም ወቅት ለማወቅ የሚረዳ ምልክት ነው:: መልካም ስራ ቤቶችን ከጀርባዎቻቸው መግባታችሁ አይደለም:: ይልቁንም የመልካም ስራ ባለቤት አላህን የሚፈራው ነው:: ቤቶችንም በፊት በሮቻቸው በኩል ግቡ:: አላህንም ፍሩ ከጀሀነም ቅጣት ልትድኑ ዘንድ።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ሙሐመድ ሆይ!) ከለጋ ጨረቃዎች (መለዋወጥ) ይጠየቁሃል፡፡ እነርሱ ለሰዎች (ጥቅም) ለሐጅም (ማወቂያ) ጊዜያቶች (ምልክቶች) ናቸው በላቸው፡፡ መልካም ሥራም ቤቶችን ከጀርባዎቻቸው በመምጣታችሁ አይደለም፡፡ ግን የመልካም ሥራ ባለቤት የተጠነቀቀ ሰው ነው፡፡ ቤቶችንም ከደጃፎቻቸው በኩል ግቡ፤ አላህንም ፍሩ ልትድኑ ይከጀላልና (በላቸው)፡፡