فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِٱلْجُنُودِ قَالَ إِنَّ ٱللَّهَ مُبْتَلِيكُم بِنَهَرٍ فَمَن شَرِبَ مِنْهُ فَلَيْسَ مِنِّى وَمَن لَّمْ يَطْعَمْهُ فَإِنَّهُۥ مِنِّىٓ إِلَّا مَنِ ٱغْتَرَفَ غُرْفَةًۢ بِيَدِهِۦ فَشَرِبُوا۟ مِنْهُ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ فَلَمَّا جَاوَزَهُۥ هُوَ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ قَالُوا۟ لَا طَاقَةَ لَنَا ٱلْيَوْمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِۦ قَالَ ٱلَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَٰقُوا۟ ٱللَّهِ كَم مِّن فِئَةٍ قَلِيلَةٍ غَلَبَتْ فِئَةً كَثِيرَةًۢ بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy249. ጧሉትም በሰራዊቱ ታጅቦ በመጣ ጊዜ ‹‹አላህ በወንዝ ውሃ ይፈትናችኃል:: እናም ከእርሱ የጠጣ ሰው ሁሉ ከእኔ አይደለም:: እሱን ያልቀመሰው ሰው ግን በእጁ አንድ እፍኝ ያህል የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው›› አለ:: ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች ሲቀሩ ከእርሱ ጠጡ:: እርሱና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሉትን (ጎልያድን) እና ሰራዊቱን ለመዋጋት በቂ ችሎታና ጥንካሬ የለንም።» አሉት:: እነዚያ ከአላህ ጋር እንደሚገናኙ የሚያረጋግጡትም «ጥቂት ቡድን በአላህ ፈቃድ ብዙውን ቡድን ያሸነፈበት አጋጣሚ ብዙ ነው:: አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና።» አሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጧሉትም በሠራዊቱ (ታጅቦ) በወጣ ጊዜ፡- «አላህ በወንዝ (ውሃ) ፈታኛችሁ ነው ከርሱም የጠጣ ሰው ከእኔ አይደለም፡፡ ያልቀመሰው ሰው እርሱ ከኔ ነው በእጁ መዝገንን የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር » አለ፡፡ ከእነርሱም ጥቂቶች ሲቀሩ ከርሱ ጠጡ፡፡ እርሱና እነዚያም ከእርሱ ጋር ያመኑት (ወንዙን) ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሎትንና ሠራዊቱን በመዋጋት ለኛ ዛሬ ችሎታ የለንም» አሉት፡፡ እነዚያ እነርሱ አላህን ተገናኝዎች መኾናቸው የሚያረጋግጡት፡- «ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህ ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ፡፡